www.maledatimes.com 8ኛው የመፅሐፍ ዓውደ ርዕይ በአ/አበባ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

8ኛው የመፅሐፍ ዓውደ ርዕይ በአ/አበባ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው

By   /   March 5, 2014  /   Comments Off on 8ኛው የመፅሐፍ ዓውደ ርዕይ በአ/አበባ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 6 Second
8ኛው የመፅሐፍ ዓውደ ርዕይ በአ/አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ እየተካሄደ ነው፡፡ በአ/አበባ ያሉ መፅሐፍት ቤቶች ሁሉ “አለን” የሚሉትን መፅሐፎች ይዘው አንባቢያንን እያስደመሙ ነው፡፡
የጥንት እና ከገበያ የጠፉ፤ እንዲሁም አዳዲስ መፅሐፎች ሁሉ በአንድ ማዕድ ተሰትረው የአንባቢያን ያለህ እያሉ ነው፡፡ የመፅሐፍት ነጋዴዎች እንደነገሩኝ ከሆነ የዘንድሮው ዓውደርእይ ከባለፈው አመት የተሻለ የመፅሐፍ “ቀበኞች” የታደሙበት ነው፡፡

እኔም የታዘብኩት ይህንኑ ነው፡፡ በግሌ እጅግ የምፈልገውን የጄ/ል አቢይ አበበን “አውቀን እንታረም” በማግኘቴ የተደሰትኩበት አጋጣሚ ነው፡፡

እንግዲህ “ይህንን መፅሐፍ አጣን፤ ይህ ዓይነት መፅሐፍ ያላችሁ” ስትሉ የነበራችሁ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጎራ ብትሉ ያሻችሁትን መፅሐፍ ልታገኙ እንደምትችሉ ነው የምነግራችሁ፡፡

በነገራችን ላይ በጆን ክሪስቶፈር ራፋ ተደርሶ የፕሪክስ ሜዴትራኒ እና የፕሪክስ ጎንኬርት ሽልማቶችን አሸናፊነት የተጎናፀፈውና በአያሌው ምትኩ ብሩ የተተረጎመው በ550 ገፅ የተሸከፈው “አበሻው” ረዥም ልብ ወለድ በ60 ብር (10 ብር ቅናሽ) ዋጋ ለገበያ ቀርቧል

እንደገና በነገራችን ላይ የህይወት ተፈራ TOWER IN THE SKY በ80 ብር ዋጋ እየተሸጠ (10 ብር ቅናሽ) መሆኑን ልጠቁማችሁ፡፡ ሌሎች መፅሐፍትንም በቅናሽ ታገኛላችሁ፡፡
ወዳጆቼ የመፅሐፍት ዓውደ ርዕዩ የሚጠናቀቀው የካቲት 30 ቀን 2006 ዓም ነውና ጎራ ብላችሁ እዩአቸው፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 5, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 5, 2014 @ 9:01 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar