www.maledatimes.com የሰማያዊ ፓርቲ የመስክ ጉብኝት የመንግስታዊ ሽብር አሜኬላዎች እየገጠሙት ነው:: - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሰማያዊ ፓርቲ የመስክ ጉብኝት የመንግስታዊ ሽብር አሜኬላዎች እየገጠሙት ነው::

By   /   March 5, 2014  /   Comments Off on የሰማያዊ ፓርቲ የመስክ ጉብኝት የመንግስታዊ ሽብር አሜኬላዎች እየገጠሙት ነው::

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 48 Second

ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ ሰማያዊ ፓርቲ የጀመረውን ሰላማዊ ትግለ ለማጎልበትና የፓረቲውን መዋቅር የስራ እንቅሰቃሴ ለመገምገምና ለማጠናከር እነዲሁም መዋቅሩ ያለበትን ችግር መፍትሄ ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ የመስክ ጉብኝት እንዲያደርጉ በሶስት ቡድን የተከፈለ ልኡካን በሃገሪቱ ማሰማራቱ ይታወቃል:: እነዚህ የልኡካን ቡድን አባላት የመስክ ጉበኝት በአጠቃላይ በ14 ዞኖችን የሚያካትት ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ ወረዳዎች ላይ ያሉ የሰማያዊን የፓርቲ እንቅስቃሴ ከሚመሩ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት እያደረጉ በተግባራዊ ስራ ላይ ይገኛሉ::

በዚህም መሰረት በሚከተለው የመስክ ጉብኝት ምደባ መሰረት በሃገሪት የተለያዩ መስመሮች የተጓዙ የሰማያዊ ፓርቲ የመስክ ጉብኝት የሚያደርጉ አመራሮች …
ጉዞ መስመር አንድ ፡- ደ/ብርሀን ፤ ሸዋሮቢት ፤ ደሴ ፤ ወልዲያ
1. አቶ ስለሺ ፈይሳ – ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ዮናታን ተሰፋዬ – የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ
3. አቶ ሔኖክ መለሰ – በአደረጃጀት ጉዳይ የጥናትና የትግል ስልት ስልጠና ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ሸዋ ሮቢት ጨምሮ በደሴ መስመር ላይ ያሉ የሰሜን ሸዋ የፓርቲው የዞን/የቀጠና አመራሮችን በማወያየት ጉዞውን ወደ ወልዲያ እና ደሴ ያቀና ሲሆን ……

ጉዞ መስመር ሁለት – ደብረማርቆስ ፤ ባህርዳር ፤ ወረታ ፤ ጎንደር
1. አቶ በቃሉ አዳነ – አደረጃጀት ጉዳይ ም/ኃላፊ
2. አቶ ይድነቃቸው ከበደ – የህግ ጉዳይ ኃላፊ
3. ወ/ሮ ሃና ዋለልኝ የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ የያዘ የጉዞ መስመር 2 ልዑክ ቡድን የካቲት 24 እና 25 ቀን 2006 ዓ.ም ከምስራቅ ጎጃም የዞን አስተባባሪዎች ጋር በደብር ማርቆስ ከተማ ውይይት አካሄደ፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን 18 (አስራ ስምንት) ወረዳዎች የሚገኝ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ በ10 (አስሩ) ወረዳዎች ማለትም፡-
1ኛ. አነደድ 2ኛ. ደ/ማርቆስ ከተማ ወረዳ 3ኛ. ጎዛአምን 4ኛ. ማቻከል 5ኛ. ደብረ ኤሊያስ 6ኛ.ባሶ ሊበን
7ኛ. እናርጅ እናውጋ 8ኛ. ጎንቻ ሲሶእነሴ 9ኛ. እነብሴ ሳርምድርጉዞ መስመር ሁለት – ደብረማርቆስ ፤ ባህርዳር ፤ ወረታ ፤ ጎንደር/መርጦ ለማርያም 10ኛ. ሁለት እጁ እነሴ
ከላይ በተገለፁት ወረዳዎች የሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር ተዘርግቶ ስራዎች እየተሩ ሲሆን ወደቦታው ያቀናው የልዑክ ቡድን እነዚህን ወረዳዎች ከሚያስተባብረው የዞን አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በቀጣይ ቀናት በባህር ዳር፣ ወረታ (ደቡብ ጐንደር) እና ጐንደር በተመሳሳይ ሁኔታ የሰሜን ኢትዮጵያ ልዕካን ቡድን የሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡

ጉዞ መስመር ሶስት – ሆሳዕና ፤ ሶዶ ፤ አርባ ምንጭ ፤ ባድዋቾ ፤ አዋሳ
1. አቶ ጌታነህ ባልቻ – የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. አቶ ይሁን ዓለሙ – የአደረጃጀት ጉዳይ የክትትልና ግምገማ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የያዘው የመስክ ጉብኝት ቡድን ሶዶ ላይ ካለው መዋቅር ጋር አሰፈለጊውን ስብሰባና ግምገማ ካካሄዱ ቦሀላ ወደ ቀጣይ ከተማ ወደሆነችው አርባ ምንጭ ጉዞ ሲጀምሩ በሰዶ ፖሊሶች ተይዘው በአሁኑ ሰአት በእስር ላይ ይገኛሉ::

ከማንኛውም ሰው ጋር እንዳይገናኙ እና ምግብ እንዳይትገባላቸው የተደረጉት የመስክ ጉብኝት ቡድን ሶስት አባላት የመንግስታዊ ሽብር አሜኬላዎች የሆኑ ያልተማሩ ካድረዎች በበላይ ትእዛዝ በሚል ህገመንግስቱን በረገጠ መልኩ ሰላማዊ ትግልን መርጦ በመንግስት ተመዝግቦ በሚገኝ ፓርቲ እና አመራሮች ላይ የእስር እርምጃ መውሰዳቸው የዲሞክራሲ እሾዎች ማበባቸውን ያመለክታል::
በጉዞ ላይ ካሉት የሠማያዊ ፓርቲ ሉኡካን ስራቸውን በጥሩ ሁኔታ እያካሄዱ ሲሆን ቀደም ብለን እንደነገርናችሁ በጉዞ መስመር 3 ላይ ያሉት ትላንትና ከወላይታ ስብሰባቸውን ጨርሰው 10፡00 ሰዓት ላይ ወደ አርባምንጭ ለመሄድ ሚኒባስ ተሳፍረው ሚኒባሱ ሶዶ ከተማ ለቆ ሊወጣ ሲል ከተሳፋሪው ጋር ተቀላቅለው በገቡ ፖሊሶች ተገዶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄድ ታዘዘ ፡፡ ሹፌሩ መኪናውን ፖሊስ ጣቢያ á‹­á‹ž እንደ ደረሰ የ3ቱን የሠማያዊ ፓርቲ አመራሮች ከመኪና እንዲወርዱ ቢጠየቁም “ፖሊስ እኛን ከመኪና እሚያስወርድበት የሚችል ምንም አይነት የህግ አግባብ የለውም” ብለው በመግለጽ ከመኪና አንወርድም ቢሉም መኪናው በታጠቁ ፖሊሶች ተከቦ በግድ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሌሊሼ ኦላ መጥተው “ወደ ወላይታ ከተማ ስትገቡ አላሳወቃችሁም ወይም አላስፈቀዳችሁንም፡፡ በዛ ላይ በጦር መሳሪያ እና በሽብርተኝነት ስለተጠረጠራችሁ መነጋገር ስላለብን ውረዱ!” ብለዋቸው ከወረዱ በኋላ ፐሊሶቹም ሻንጣዎቻቸው ፈትሸዋቸዋል፡፡ ምንም አይነት መሳሪያ ሳያገኙም ቀርተዋል፡፡ “ወላይታ ለመግባት ምንም አይነት ፈቃድ ከማንም አንጠብቅም ምክንያቱም አገራችን ነው” በማለት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ቢመልሱም “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር ድረስ መጥታችሁ ቅስቀሳ ለማካሄድ መሞከራችሁ በጣም ደፋሮች ናችሁ! ከዚህ በኋላም ወላይታ ላይ እንዲህ አይነት ነገር እንዳትሞክሩ!” የሚል ዛቻና ማስፈራሪያ ያደረሱባቸው ሲሆን ማምሻውን በወላይታ ዝናብ እየዘነበ ያመሸ የነበረ ሲሆን ከተያዙበት ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ውጭ ዝናብ ላይ እየተደበደቡ እንዲያመሹ አድርገዋቸዋል!
የወላይታ አስተባባሪ የሆኑትን ወጨፎ ሳዳሞ እና ታደመ የሚባሉት አብረዋቸው የታሰሩ ሲሆን ማታ ከ5፡00 ሰዓት በኋላ አንድ ክፍል ውስጥ አስገብተዋቸው አሳደሩዋቸዋል፡፡ በማግሰቱም ዛሬ የካቲት 26 2006 “አሁን መሄድ ትችላላችሁ” ብለው ከአዲስ አበባ የሄዱትን ሶስቱን የሰማዊ ፓረቲ አመራሮች 1ኛ/ አቶ ጌታነህ ባልቻ 2ኛ/ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ 3ኛ/ አቶ ይሁን አለሙ ሲለቁዋቸው ከሀዲያ ጀምረው የሰሯቸውን ስራዎች የያዙበትን ሰነዶች፤ቃለ ጉባኤዎች እና ሁለቱን የወላይታ ተወካዮችን /አስተባባሪዎችን/ እስካሁን ያለቀቋቸው ሲሆን ስለ ንበረታችሁ የምናውቀው ነገር የለም በማለታቸው አሁንም በመከራከር ላይ ይገኛሉ፡፡
ምንሊክ ሳልሳዊ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 5, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 5, 2014 @ 9:20 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar