www.maledatimes.com UDJ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍት የድጋፍ መኃበር በስዊድን ወርኃዊ ስብሰባ !! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  AFRICA  >  Current Article

UDJ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍት የድጋፍ መኃበር በስዊድን ወርኃዊ ስብሰባ !!

By   /   March 9, 2014  /   Comments Off on UDJ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍት የድጋፍ መኃበር በስዊድን ወርኃዊ ስብሰባ !!

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 47 Second

 በኢሳ አብድሰመድ (By Issa Abdusemed)

በጣም የሚያስደስት እና የተሳካ ስብሰባ  በስዊዲን  አገር የሚገኙ  UDJ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ የድጋፍ መኃበር በስዊድን     ስብስብ  ስብሰባውም  በየወሩ  የሚደረግ ቢሆንም  የዚህን  ስብሰባ ለየት የሚያደርገው   በወቅቱ  እጅግ በርከት ያሉ  የ UDJ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ የድጋፍ መኃበር በስዊድን….   ኢትዮዽያዊና የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑ በርካታ  እና አዳዲስ ደጋፊዎች  መገኘታችው ነው። በወቅቱም በስብሰባዉ ላይ ከተችገኙት አዳዲስ ኣባሎቻችን በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከመቼዉም በላይ አስደሳችና ውጤታማ  ሆኖ አግኝተንዋል

አዳዲስ ሀሳቦችን  በማመንጨት ትግሉን በበለጠ ሁኔታ አጠናክሮ መቀጠልን የሚያስችል ሁኔታ ፈጥሮአል መንግስትን  እና ባለስልጣናቱን በተመለከተም ተመሳሳይ እጅግ ወሳኝ እና አፋጣኝ  ለውጥ ያስፈልጋል በሚል በተለይም  የወያኔ ኢህአዴግን ርዕዮተ አለም መራገፍ  የሚገባውና ያረጀ ያፈጀ ቅራቅንቦ  እንደሆነ ተራኪው ቢገልፁም የገዛ በተቃውሞው ፖለቲካ ሽፋን በሽብር ወንጀል የተከሰሰውና ጥፋተኛ ተብሎ የፍትህ እና የነጻነት ታጋያችንን አንዷለም አራጌ የመስመሩን ተሃድሶ በተመለከተ ያነሳውን ነጥብ ማስታወሱ ለውጡ የቱ ጋር መሆን እንዳለበት በቀላሉ ለመረዳት ያስችለናል; አሁን የወያኔ አገዛዝ ውስጡን ብል እንደበላው እንጨት ተቦርቡሮ ለይምሰል ቆሞ የሚታይበት ወቅት ነው።

ካፒቴን ኃይለመድህን አበራ ዙሪያም የተነሱ ኃሳቦችም ነበሩ በዓገር ውስጥም ሆነ በውጪው ዓለም አቶ ኃይለመድህን አበራ በሌላ በኩል የአይሮፕላኑ ጄኔቭ ላይ ማሳረፍ ተከትሎ በሀገር ቤት የተለያዩ ስሜቶች መፈጠራቸውን ከሀገርቤት የሚወጡ ዘገባዎች ያመላክታሉ።

ስሜቶቹ ”ኢትዮጵያን በዓለም አዋረደ” ከሚሉት የተወሰኑ በቅን ከሚሰነዘሩ  እስከ መንግስት ደጋፊዎች የሚሰሙ  ቢሆንም በአብዛኛው በውጭም ሆነ በሀገር ቤት ያለው ሕብረተሰብ ዘንድ ግን አንዳች አደጋ ካለመድረሱ እና የደንበኞችን ክብር ሳያዋርድ በሰላም ማከናወኑ ከሁሉም በላይ ደግሞ የሚልዮን ኢትዮጵያውያንን ብሶት ለማሰማት የቻለ ጀግና  ነው ሲሉም ይደመጣሉ።  ካፒቴን አቶ ኃይለመድህን አበራ  ዙሪያ በራሳቸው አንደበት መግለጫ እስካልሰጡ ድረስ  UDJ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ የድጋፍ መኃበር በስዊድን  ዓስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል ;;

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ሥራ ለመቀጠርም ሆነ ኃላፊነት ለማግኘት የግድ የአንድ ዘር አካል፤ አልያም ደግሞ የኢሕአዴግ አባል መሆን እንደሚያስፈልግ በተደጋጋሚ ከድርጅቱ የሚለቁ ወገኖች መግለጻቸውን የሚያስታውሱ የፖለቲካ ተንታኞች ምክትል አብራሪው  ደርሶበታል ተብሎ ከሚገመተው በደል አኳያ እንዲህ ያለውን እርምጃ መውሰዱ ላያስገርም ይችላል በማለት በስብሰባው ላይ አስተያየታቸውን  ሰጥዋል ። እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት የኢሕአዴግ መንግስት በዘር ላይ የሚያደርገውን አድልዎ፣ በደል እንዲሁም “እኔን ካልደገፋችሁኝ ምንም አታገኙም” የሚለውን አካሄዱን እንዲያቆም ካፒቴን አቶ ኃይለመድህን አበራ የወሰዱት እርምጃ   ትምህርት ሊሆነው ይገባል ይላሉ።

የተባበረ  ሕዝባዊ ሃይል ገርስሶ ሊጥለው የሚችልበት ሁኔታ ጎልቶ ይታያል; ስርዓቱ  በቀውስ ላይ ቀውስ እየተደራረበበት በውስጡም በውጩም እየተጋለጠ መጥቷል: የሕዝቡ ብሶትና ጩኸት ሰሚና ደጋፊ እያገኘ በመሄድ ላይ ነው። “

ብረትን  መቀጥቀጥ እንደጋለ ነው” ይባላልና የሕዝቡ ስሜት ሳይበርድና ሳይቀዘቅዝ መነሳሳቱን በአግባቡ መጠቀምና አገራችን  ወደባሰ የቀውስ ባህር ውስጥ እንዳትገባ አስቸኳይ መፍትሄ መፈጠር አለበት።

ያም መፍትሔ የተበታተነው የተቃዋሚ ጎራ በአንድነት ግንባር ሕዝቡን ለመምራት ሲወስንና በተግባር ሲገልጸው ነው። ለብቻ ለስልጣን የሚቋምጡበት፣በነጠላ ጉዞና ትግል አገርና ሕዝብ አድናለሁ፣የሌለ ሃይልና ጥበብ እኔ ብቻ አለኝ የሚሉበት፣የሕዝብን መከራና ችግር ለድርጅታዊ ዝናና ፕሮፓጋንዳ የሚጠቀሙበት ጊዜ አይደለም።

ምንም እንኳን ወያኔ በውጥረት ላይ ቢገኝም መዘንጋት የለለብንና ማመን ያለብን ተቃዋሚው ጎራ የተዳከመ መሆኑንና በያዘው የተዝረከረከ አካሄድ ከቀጠለበት የሚያረካ ስራ ሳይሰራ፣ይህን አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ተንገጫግጮ እንደሚቆምና ወያኔ የገጠመውን ችግር አሶግዶ መልሶ መቋቋም እንደሚችል ነው።

በገንዘብ፣ በወታደራዊ ሃይሉ፣በጸጥታው ሰንሰለቱ አሁንም ከተቃዋሚው የተሻለ ነው: ያንን ሃይሉን  ሰብሮ ለመጣል የሚቻለው በገሃድ በሚታይ በተባባረ ክንድ እንጂ ከፕሮፓጋንዳ መድረክ ከማያልፍ በነጠላ ድርጅት ነጭ ወሬ ዙሪያ ተጭበርብሮ በማጨብጨብ አይደለም። አልፎ አልፎም እንደ መስከረም ወፍ በአደባባይ ብቅ እያሉ  አገራችንን ወደ ሲኦል የለወጠ፣ሕዝቡን ለስደትና ለመከራ የዳረገ ዘረኛና በሙስና የተጨማለቀ ስርዓት በቃ ብለን በጋራ  እናሶግድ ሲሉም  ተደምጠዋል።

አንዳንድ አራጋቢ ፕሬሶቹም እነሱ በፈሰሱበት ቢፈሱ እንጂ ገዢውን የሚተቹትን (በተጨባጭ መረጃም ሆነ በምናብ) እነርሱን  ለመተቸትና ለመምከር ሲደፍሩ ማየትም ናፍቆናል። በሚልም ዙርያ በስብሰባቸውም ላይ አካተውታል

ዞሮ ዞሮ ፖለቲካውና ሙግቱ  ለህዝቡና ለሃገር  ከሆነ ይህ ደግሞ  ከፕሬሱም ሆነ ከተቃውሞው ጎራ የሚጠበቅ  ነበር  ነገር ግን ።  አልሆነም። ስላልሆነም  ይህ በቀናነትና በምክንያታዊነት ለሚመራ የተቃውሞ ፖለቲካ እና ፕሬስ UDJ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ የድጋፍ መኃበር በስዊድን   ምኞታችን ቢሆን  ተገቢነት አለው ብለን እናስባለን ሲሉ ገልፀውታል።

በመጨረሻም በአቶ አንዱአለም አራጌ ተጽፎ አሜሪካን  ውስጥ የሚታተመውን  መጽሀፍ  እንዲላክልን ጠይቀናል  በሚቀጥለው ስብሰባችን (መጋቢት)  march 29 / 2014.  ወር  መጨረሻ ወደኛ  ይደርሳል የሚል ግምት  አለን የዚህም መፅኃፍ ሽያጭ ገቢ ማሰባሰቢያ ለአቶ አንዷለም አራጌ እንደሚውልም ገልፀዋል !!

 

ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 9, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 9, 2014 @ 8:07 am
  • Filed Under: AFRICA

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar