www.maledatimes.com የአቶ አለማየሁ አቶምሳ ስርአተ ቀብር በቅድስት ስላሴ መፈጸሙ በመላ አገሪቱ አነጋጋሪ ሆኖአል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአቶ አለማየሁ አቶምሳ ስርአተ ቀብር በቅድስት ስላሴ መፈጸሙ በመላ አገሪቱ አነጋጋሪ ሆኖአል

By   /   March 10, 2014  /   Comments Off on የአቶ አለማየሁ አቶምሳ ስርአተ ቀብር በቅድስት ስላሴ መፈጸሙ በመላ አገሪቱ አነጋጋሪ ሆኖአል

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 24 Second

የኦሮሚያው አመራር የነበሩት የአቶ አለማየሁ አቶምሳ ስርአተ ቀብር በቅድስት ስላሴ ካቴድራል በመፈጸሙ የብዙሃኑን ክርስቲያን ስሜት የጎዳ እና ለቁጣ የቀሰቀሰ ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ህግጋትን የሚጥስ መሆኑን የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም  መነጋገሪያ እና ስሜታቸውንም የሚጎዳ ሃይማኖታቸውንም የሚገድል ነው ሲሉ ጠቁመዋል ።

አቶ አለማየሁ አቶምሳ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሆነው ሳለ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን መቀበራቸው ህዝብን እና እምነቱን እንደመናቅ ይቆጠራል ያሉት አንዳንድ የቤተክርስቲያን ካህናት እንደዚህ አይነት የከፋ ወንጀል እና አሳፋሪ ድርጊት በሃገራችን ኢትዮጵያ ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው ሲሉ ለማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል በላኩት አጭር ደብዳቤ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ህግጋት አንድ ሰው በቤተክርስቲያኗ እምነት እና ህግጋት መሰረት ካልተዳደረ እና እምነቷን ያልተከተለ ከሆነ በቤተክርስትቲያኒቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊቀበር እንደማይችል ከቀድሞ ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ህግ እንደሆነ ጠቁመው ማንኛውንም ህብረተሰብ በድንገትም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች ህይወቱ ቢያልፍ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ብቻ ያለ ቤተክርስቲያኗ ቅኑና እና የቅዳሴ ስራት ብቻ አስከሬኑ በቅጥር ግቢው እንዲያርፍ የተፈቀደ እንደነበር አስታውሰዋል

ሆኖም ግን በቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ሊደረግ የማይገባው እና ሆኖም የማያውቀው ድርጊት ለእምነቱ ተካፋይ እና የእምነቱ ባለቤት ያልሆነን ሰው የእኔ እምነት ይህ አይደለም እኔን ሊወክለኝ አይገባም ብሎ የራሱን እምነት ላደራጀ እና እምነቱን ለቀየረ ሰው ማንኛምንም ስርአት ቤተክርስቲያኒቱ ለመስጠት ፍቃደኛ እንዳልሆነች የጠቆሙ ሲሆን  በስልጣን ትምከተኝነት ተነስቶ በቤትክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ መቅበሩ አሳፋሪም ድርጊት ከመሆኑም በላይ እምነቱን ያዋርዳል ሲሉ ጠቅሰዋል ። ይህም ማለት ህዝበ ምእመናኑን ከምንም እንዳልቆጠሯቸው እና ለራሳቸው ግልጋሎትን የሰጧቸውን ብቻ በማግዘፍ የሃገሪቱን ታሪክ እና ቅርስ ህግ ፣ወግ እና ማእረግ እየገፈፉአት ነው ሲሉ ገልጸዋል ።

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar