www.maledatimes.com በሃረር መብራት ሃይል ሰፈር ከ400 በላይ ቤቶች በእሳት ወደሙ ፣ቤቶቹን እና ንብረቶቻችንን እንዳናድን በፖሊስ ተከልክለናል የሃረር ነዋሪዎች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በሃረር መብራት ሃይል ሰፈር ከ400 በላይ ቤቶች በእሳት ወደሙ ፣ቤቶቹን እና ንብረቶቻችንን እንዳናድን በፖሊስ ተከልክለናል የሃረር ነዋሪዎች

By   /   March 10, 2014  /   Comments Off on በሃረር መብራት ሃይል ሰፈር ከ400 በላይ ቤቶች በእሳት ወደሙ ፣ቤቶቹን እና ንብረቶቻችንን እንዳናድን በፖሊስ ተከልክለናል የሃረር ነዋሪዎች

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 31 Second

ትናንትና የካቲት 30 ምሽት በሐረር መብራት ኃይል ተብሎ የሚታወቀው የገበያ ስፍራ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በቦታው የሚገኙ የንግድ ሱቆችን ሙሉ በሙሉ አውድሟል፡፡ ሸገር 102.1 አሁን (መጋቢት 1.2006) የ12 ሠዓት ባስተላለፈው ዜና የወደሙት ሱቆች 400 ይሆናሉ ብሏል፡፡

ሸገር በዜናው ከስፍራው ነዋሪዎችን አነጋግሮ ” እሳቱን እንዳናጠፋ በፖሊስ ተከልክለናል” ሲሉ አስደምጦናል፡፡ “ይህ ደግሞ የገበያ ማዕከሉ ሆን ተብሎ እንዲቃጠል መደረጉን ያሳያል” ብለዋል ነዋሪዎቹ ከስፍራው፡፡

“ይህ መሆኑን ለመቃወም ዛሬ ድምፃችንን ለማሰማት ወጥተን ነበር፤ ፖሊስ በከፈተው ተኩስ ብዙ ሰዎች ቆስለዋል” ሲሉም አሰደምጦናል፡፡

ሸገር ያነጋገራቸው የአካባቢው ባለስልጣን “እሳቱን ያስነሱት ሰዎች በቁጥጥር ስር ለማድረግ እየተንቀሳቀስን ነው፤ እስካሁን የተጠረጠሩ 3 ሰዎችን ይዘናል” ብለዋል፡፡

ያም ሆነ ይህ በሐረር የሆነው ሁሉ ያሳዝናል፡፡ ፖሊስ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ተኩስ መክፈቱ እና ዜጎችን ማቁሰሉ በጣም ያበሳጫል፡፡

ንብረትና ሐብት መውደሙ አልበቃ ብሎ ዜጎችን በጥይት መደብደብ አውሬነት ነው፡፡

በዜጎች ላይ ይህንን ጉዳት ያደረሱ ለፍርድ ይቅረቡ!!!

ፍትህ በሐረር ለተጎዱ ወገኖች!!!! በወሰን ሰገድ ገብረ ኪዳን

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 10, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 10, 2014 @ 12:18 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar