www.maledatimes.com አጣብቂኙ ከባድ ነው፡፡ ያደሩበት ጭቃ ከጭድ ይሞቃል :: - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አጣብቂኙ ከባድ ነው፡፡ ያደሩበት ጭቃ ከጭድ ይሞቃል ::

By   /   March 11, 2014  /   Comments Off on አጣብቂኙ ከባድ ነው፡፡ ያደሩበት ጭቃ ከጭድ ይሞቃል ::

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 15 Second

‪ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ህዝብ በኢኮኖሚ ሲጐሳቆል፣ በፖለቲካ በደል ሲሰማውና በማህበራዊ ህይወቱ ያልተረጋጋ ከሆነ ደግ አደለም፡፡ በጥንቱ ማርክሳዊ አካሄድ ፖለቲካ ማለት የተጠራቀመው የኢኮኖሚ ይዘት ነፀብራቅ/መገለጫ እንደማለት ነው፡፡ በግድ አራምደዋለሁ ካሉ አንገት መቀጨት፣ መሰበር፣ መውደቅ፣ አልጋ ላይ መቅረት ይከተላል ማለት ነው፡፡ ለማደግ አቅጣጫ ያስፈልጋል፡፡ ከመዓቱ ለማምለጥ መፍጠንም ያስፈልጋል፡፡ አቅጣጫ ማወቅ ብቻ ሳይሆን መሮጥና መፍጠን ያስፈልጋል ስንል ግን፣ ከምን አቅም? በምን ነፃነት? በምን ፍትሐዊ እርምጃ? በምን ዓይነት ቢሮክራሲያዊ ተቋም? በምን ዓይነት እርስበርስ መተማመን? በምን ዓይነት የገዢ ተገዢ ግንኙነት? ብሎ መጠየቅ ያባት ነው፡፡

የአስተዳደር ነገር መቼም ዋና ጉዳይ ነው፡፡ ኢኮኖሚያችን በኑሮ ውድነቱ መነጽር ሲታይ ዛሬ አሳሳቢ ነው፡፡ የሁሉም ነገር ዘዴው ተገኝቷል እንዴት እንደምንኖር መላው ከመጥፋቱ በስተቀር ፡፡ለፍቶ ለፍቶ፣ ዳክሮ ዳክሮ ኑሮ ጠብ አልል ያለው ሰው ከምሬት ሊወጣ አይችልም፡፡“እምዬ ኢትዮጵያ ሥራሽ ብዙ ፍራንክሽ ትንሽ” አለ አሉ አንድ ሠራተኛ! በእርግጥ በሊቀ – ሊቃውንት አስተሳሰብና ስሌት “ከአምስት አመት በኋላ ሠንጠረዡ ከፍ ይላል”፤ “በ2017 á‹“.ም አያሌ ፕሮጄክቶች ስለሚጠናቀቁ የተለየ ዓለም ይታያል” ወዘተ ይባላል፡፡ ምንሊክ ሳልሳዊ ችግሩ ህዝባችን “ሰብል በጥር ይታፈሳል” ቢሉት “ሆዴን እስከዚያ ለማን ላበድረው” አለ፤ የሚባለው ዓይነት ችግር ውስጥ ይገባል፡፡ አጣብቂኙ ከባድ ነው፡፡ ያለፈው ዘመን መሪ “የወረቀቱ ገብቶኛል፡፡ የገበያውን፣ የመሬት ያለውን ጉዳይ አስረዱኝ” አሉ አሉ፡፡ በግራፍ (ሠንጠረዡ ላይ) ሰብሉ ሰማይ ነክቶ፣ ከገበያው ግን ጠፍቶ ሲያዩት ቢጨንቃቸው ነው፡፡

የአመራራችንን ጉዳይ ችላ ብለን፣ የቢሮክራሲውን አካሄድ ወደጐን ትተን፣ ወደየትም የተሻለ ህይወት መዝለቅ አንችልም፡፡ በአካላችን እያወደስን በሆዳችን እየሰደብን የቱንም ወንዝ አንሻገርም፡፡ የምርጫችንን የዲሞክራሲያችንን ነገርም አደራ መባባል ያለብን ጊዜ ነው፡፡ መጽሐፍ ከመፃፍ፣ አዋጅ ከማወጅ፣ መመሪያ ከማውጣትና ጋዜጣዊ ጉባዔ ከማካሄድ አልፈን በቀናነት ለህዝባችን የሚበጀው ማንኛው መንገድ ነው? ማለት በጐ ነገር ነው፡፡

በኢኮኖሚያዊ ገቢያችን፣ በፖለቲካዊ መልካም አስተዳደራችን፣ በማህበራዊና ባህላዊ ማንነታችን የሚደርስብንን ጉስቁልና አሸንፈንና ድህነታችንን ታግለን በሁሉም አቅጣጫ ለውጥ እናመጣ ዘንድ፤ የህዝብ መነሳሳትን የሚያህል ካፒታል የለም፤ መነሳሳት ተገቢ ነው! አለበለዚያ ትላንት የነበርንበት ቦታ እንደተመቸን ቆጥረን መቀበል “ያደሩበት ጭቃ ከጭድ ይሞቃል” የሚለውን ተረት ከማረጋገጥ በቀር ፋይዳው በድን ነው፡፡

በትዕዛዝ እንግዳ ከመቀበል ይሰውረን፡፡ ባህላዊ እንግዳ – ተቀባይነታችንን ይባርክልን፡፡ ከጐረቤት ጋር ከመጣላት ይሰውረን፡፡ ተጣልተን ከታረቅንም ዕውነቱን የሚነግረን አያሳጣን፡፡ ስንጣላ መፈክር ከማስነገርና ከመራገም፤ ስንታረቅ ከማጨብጨብ ይሰውረን፡፡ የመንግስታችንን ልብና ልቦና እናውቅ ዘንድ የመረጃ ደሀ አያድርገን! የምንሰማውን በሌላ እንዳንተረጉም ንቃተ – ህሊናውን ያድለን ዘንድ፤ የሰላምና የማስተዋል ያድርግልን፡፡ ብሶት ሁሉ የፈጠራ፣ ጩኸት ሁሉ የሁከት፣ ሥጋት ሁሉ የትርምስ፤ እንዳያስመስልብን አስተዋይ ተመልካች ይሰጠን፡፡ ማየት – የተሳነው ተመሪ እንዳይሸበር ነገሩን ግልጥልጥ የሚያደርግ መሪ ይባርክልን፡፡ምንሊክ ሳልሳዊ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 11, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 11, 2014 @ 3:19 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar