www.maledatimes.com የሴቶች ንቁ ተሳትፎ ጉልህ ሚና ይኖረዋል። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሴቶች ንቁ ተሳትፎ ጉልህ ሚና ይኖረዋል።

By   /   March 11, 2014  /   Comments Off on የሴቶች ንቁ ተሳትፎ ጉልህ ሚና ይኖረዋል።

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 2 Second

 

ከኤደን መስፍን(ኖርዌይ)                          11-03-2014

           በአንድ ሃገር የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት የህዝብ ሙሉ ተሳትፎ  አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይደለም። ከህብረተሰቡ ክፈል ደግሞ የሴቶች ንቁ ተሳትፎ  ጉልህ ሚና ይኖረዋል። በሃገራችንም ይህን ከጥንት እስካሁን በተግባር እያያየነው እንገኛለን።የንግስት ሳባ፤ የንግስት እሌኒ፤የእቴጌ ጣይቱ፤በአስራዘጠኝ ስልሳዎቹ የፊውዳል ስርአት ግርሰሳ የነበረ የሴቶች ተሳትፎ በአጠቃላይ ሴቶች  ለሃገራችን  ያደጉረትን ንቁ ተሳትፎ ያሳያል።በሌላ በኩል ደግሞ በ አምባገነን ስርዓቶች በከፍተኛ ሁኔታ ከሚጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎች በአብዛኛው ሴቶች ናቸው።በአሁኑ ሰአትም በሃገራችን ያለው ዘረኛ እና ጨቋኝ መንግስትንም በከፍተኛ ሁኔታ ከሚያስጠይቁት እና ከሚያስኮንኑት አንዱይ ይኸው በሴቶች ላይ የሚያደርሰው ልክ ያጣ ጥቃት ነው።ይህንንም እውነታ ሃገር በቀል እና የውጭ ሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አያሳወቁ ይገኛሉ። በተግባርም እያየነው ነው። ለምሳሌ ያህል በአገዛዙ መልካም አስተዳደር እጦት የተነሳ በተፈጠረ የኑሮ አስከፊነት ወደ አረብ ሃገር እየተሰደዱ በባርነት የሚገዙ እና ወደረከሰ ስራ የሚሰማሩበት ሁኔታ፤በሃገር ውስጥም ገና በለጋ እድሜያቸው ጀምሮ ገላቸውን ሸጠው ኑሮን ለማሸነፍ መውጣታቸው፤በየእስር ቤቱ በአምባገነኑ መንግስት ወታደሮች እና ፖሊሶች የሚደርስባቸው የመደፈር ጥቃት፤ለነጻነት እና ለመብት በመቆማቸው እና በመጻፋቸው እነ ብርቱካን ሚደቅሳ ርዩተአለም አሰፋ አጠቃላይ ሁኔታ ስንመለከት በሃገራችን ያለውን የሴቶች ጥቃት እና እንግልት ጥልቀቱን እና ስፋቱን እናይበታለን።ለዚህ እና በአጠቃላይለዝብ ችግሮች ተጠያቂ የሆነው ይህ ጸረህዝብ እና ጸረኢትዮጰያ መንግስት ይህንንም ለማስተባበል  ዲሞክራሲ እና በልማት ለህዝብ ማጃጃያነት እንደሚጠበቅበት የሴቶችን መብቷ አስከብራለሁ አስከብሬያለሁ እያለ ከጽሁፍ ባላለፈ ለማጃጃያነት እየተጠቀመበት ይገኛል።

እነዚህን እና ሌሎችን ስንመለከት በአንድ በኩል በቁርጠኝነት እና በብልሃት የተካኑ ሴቶች እንዳሏት ከትንት ጀምሮ ያለውታሪካችን እስካሁን እንደቀጠለ እንማርበታለን።በሌላ በኩል የታላላቆቻችንን ፈለግ በመከተል በአሁን ሰአት ያለውን ችግር ትኩረት ሰትተን እንድናየው ያስገድደናልከሴቶች መብትም አልፈን በአጠቃላይ የሃገራችን እና የህዝባችንን ችግር ማለትም ኢትዮጵያችን እንደ ኢትዮጵያ እንድትቀጥል፤በህዝባችን እየተቀመረ ያለውን የእርስ በእርስ ግችት፤የአንድ ዘር የበላይነት፤አባቶቻችን ደማቸውን እና ህይወታቸም የገበሩለት መሬታቸን ለባእዳን እጅግ በረከሰ ዋጋ መቸብቸብ አልፎም ለጎረቤት ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ብቻ ለጎረቤት ሃገሮች አሳልፎ መስጠት፤የህዝባችን የኑሮ ሰቆቃ፤የመናገር የመጻፍ መብት ማጣት በመገንዘብ ያለውን ዘረኛ እና አምባገነን መንግስት እኩይ ሴራ በማወቅ እና ለለውጥ በሚደረገው ትግል እንደ ጥንቶቹ ሴቶች ከህብረተሰቡ ጎን በመቆም ልንሳተፍበት ይገባል።ሃገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እርዳታ ያሻታል እና እኛ ሴቶችም ፈጥነን እንድረስላት።ይህ ደግሞ እናቶቻችን እና እህቶቻችን ለሃገራችን የከፈሉትን መስዋዕትነትለመጠበቅ የጣሉብንንም አደራ እንዳንበላ ይረዳናል።ሃገራችንንም ከገባችበት አዘቅት ያወጣልናል።

ኢትዮጲያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

 

 

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 11, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 11, 2014 @ 9:57 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar