www.maledatimes.com ተወጋዥ ( ገለልተኛ ማውገዝ ይችላልን) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ተወጋዥ ( ገለልተኛ ማውገዝ ይችላልን)

By   /   March 14, 2014  /   Comments Off on ተወጋዥ ( ገለልተኛ ማውገዝ ይችላልን)

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 30 Second

በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን
አትመለከትም ማቴዎስ ፯፥፫
አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን
ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ ማቴዎስ ፬፥ ፭
ሀገራችን ኢትዮጵያና ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ በደረስንበትና ባለንበት ዘመነ ወያኔ በከፍተኛ
ውድቀትና ዝቅተት በታሪኳ ገጥሟት በማያውቅ ፈተና ገብታ ትገኛለች ቅድስትቤተ ክርስቲያን
መሪዋ አንድ መንፈስ ቅዱስ ሆኖ ሳለ በአንድ ፓትርያርክ በሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ በሲኖዶስ
ስር ባለ ደግሞ መንበረፓ ትርያርክ ያላት ናት የምትተዳደርበትና የምትመራበት ደግሞ ቅዱስ
መጽሀፍን መሰረት ያደረገ ቃለ ዓዋዲ ነው
በዚህ ቃለ አዋዲ ህገ ደንብ መሰረት በፓትርያርክ የሚመራ ሲኖዶስ በሲኖዶስ ስር ደግሞ
መንበረ ፓትርያርክ በመንበረ ፓትርያርክ ደግሞ በሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ አህጉረ ስብከት ያላት
ከአህጉረ ስብከት ደግሞ በየደረጃውና በአውራጃ በወረዳ እንዲሁም በአጥቢያ አብያተ
ክርስቲያናት የተዋቀረች አንዲት ቤተ ክርስቲያን ናት
አመሰራረትዋና መዋቅርዋ ይህ ሆኖ ሳለ የትግራይን ነጻ አውጥቸ ሪፑብሊክ እመሰርታለሁ ብሎ
በጎሳ ተደራጅቶ የመጣውና ስልጣን ላይ የወጣው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የቤተ ክርስቲያኒቱን
አባት አባሮ የራሱን ፓትርያርክ በመሾሙ ምክንያት ቤተ ክርስቲያንን ለሁለት ከፍሎአታል
ይህም በመሆኑ በአንድ ወንበር ሁለት ፓትርያርክ እና ሁለት ሲኖዶስ ተፈጥሮአል ይህም
አልበቃ ብሎ ዛሬ አወግዘናል ብለው አደባባይ የወጡት ደግሞ ፫ኛው ቡድን ገለልተኞች ናቸው
የቤተ ክርስቲያን ለሁለት መከፈል ሲያሳዝነን ገለልተኛ ነን በማለት ሕገ ቤተክርስቲያን
የማይደግፋቸው በቀኖና ስር የሌሉ ምንደኞች ለስልጣንና ለገንዘብ የቆሙ ካህናት በሌለ
ስልጣናቸው አወገዝን ሲሉ አለማፍራቸው እጅግ ያስገርማል
ለመሆኑ እነዚህ ቄሶች በቤተ ክርስቲያን ቀኖና ስር ናቸውን ማውገዝስ ይችላሉ አወገዝነው
የሚሉት ቄስ ስሕተት ሰርቶ ሊሆን ይችላል ከአውጋዦቹ መካከል መወገዝ የሚሰራ ከሆነ ደግሞ
መካከል ቄስ አስተራየ በሀይማኖት ህጸጽ ምክንያት በአባ ማትያስ ተወግዘዋል አባ ኃይለ
ሚካኤል ተክለ ሃይማኖትም ለውግዘት ባይደርሱም ብዙ ነውር እንዳለበቸው ይወራል ይሁንና
ግርግር ለቀጣፊ ይበጃል እንደሚባለው በሁለት ቢላዋ የሚበሉ ካህናት እራሳቸውን ከቀኖና
ቤተ ክርስቲያን አግለው ስለ ቤተ ክርስቲያን ስርኣት ተቆርቋሪዎች ሊያደርጋቸው አይችልም
ምክንያቱም ከቀኖና ወጥተው በፕሮስቴንታዊ ልማድ ገለልተኛ ብለው ቆመዋልና ነው ስለዚህ
ውግዝታቸው ወፈ ገዝት እንጂ ነው ተቀባይነት የለውም ተድላ ጌትነት ከጀርመን

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 14, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 14, 2014 @ 3:23 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar