www.maledatimes.com በጎንደር የቅማንት ብሔረሰብ አመራርና አባላት እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጎንደር የቅማንት ብሔረሰብ አመራርና አባላት እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው።

By   /   March 16, 2014  /   Comments Off on በጎንደር የቅማንት ብሔረሰብ አመራርና አባላት እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው።

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 9 Second
(ምንሊክ ሳልሳዊ)
ከ50 በላይ የሚሆኑ የቅማንት ብሔረሰብ አመራርና አባላት መታሰራቸው ተጠቆመ::
ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት እያቀረበ ባለው የማንነትና የራስ አስተዳዳርነት ጥያቄ ምክንያት፣ ከ50 በላይ የሚሆኑ አባላትና አመራሮቹ መታሰራቸውን የቅማንት ብሔረሰብ አመራር ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

የካቲት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. ‹‹ቅማንት የሚባል ሕዝብ የለም ያለ አካል ባይኖርም የራስ አስተዳደር ግን ሊፈቀድ አይችልም›› በሚል የክልሉ መንግሥት ተወካዮች ምክር ቤት ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም፣ በጎንደር ከተማ እስከ 300 ሺሕ የሚደርሱ ተወላጆች በተገኙበት ሰላማዊ ሠልፍ ማድረጉን ተከትሎ፣ በተለይ በአመራር ኮሚቴው ላይ ጫናና ወከባ ሲደርስበት መቆየቱን ገልጿል፡፡

በመሆኑም የክልሉ መንግሥት በተቀናጀ መንገድ በአባላቱና በአመራሩ ላይ በአድማ በታኝና ፖሊስ ሠራዊት በታገዘ ኃይል አማካይነት፣ ከየካቲት 28 ቀን 2006 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ በድምሩ 50 አመራርና አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው እንደታሰሩበት ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ በመተማ ወረዳ ሰላማዊ ሠልፍ አድርገው በሰላም ካጠናቀቁ በኋላም የታሰሩ አባላት እንዳሉም አክሏል፡፡

የክልሉ መንግሥት በምን ምክንያት እንዳሰራቸው ግልጽ ባያደርግም፣ የታሰሩ አባላቱ በቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዳይጠየቁ፣ ከጎንደር በ80 እና 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኙ ዳባትና ደባርቅ ወረዳዎች ተወስደው መታተሰራቸው የሰብዓዊ መብት ረገጣ መሆኑን ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

የቅማንት ብሔረሰብ ተወካይ ኮሚቴ በአባላቱና አመራሩ ላይ የአማራ ክልል መንግት ፈጽሞብኛል ስለሚለው እስራትና መንገላታት ማብራሪያ እንዲሰጥ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መምርያ ሲጠየቅ፣ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ኮማንደር ሰኢድ መሐመድ ምንም መረጃ እንደሌላቸው ገልጸው፣ የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምርያን ለማብራሪያ ጠቁመዋል፡፡ የሰሜን ጎንደር ፖሊስ መምርያ ፖሊስ ባልደረባ የሆኑትና ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ፖሊስ፣ ‹‹እኛ ቅማንት የሚባል ብሔረሰብ አናውቅም፤ የምናውቃቸው አማራ መሆናቸውን ነው፤›› ካሉ በኋላ፣ በበኩላቸው የሰሜን ጎደር ዞን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወደ ኮማንደር ዘመነ አመሸ ቢጠቁሙም፣ የቢሮም ሆነ የግል ስልካቸውን ሊያነሱ ባለመቻላቸው የኮማንደሩን ምላሽ ማካተት አልተቻለም፡፡ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ምንጭ ረፖርተር ጋዘጣ

Photo: በጎንደር የቅማንት ብሔረሰብ አመራርና አባላት እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው።
#Ethiopia #EPRDF #Gonder #Kimant #UDJ #Blueparty #Amhara
(ምንሊክ ሳልሳዊ) 
ከ50 በላይ የሚሆኑ የቅማንት ብሔረሰብ አመራርና አባላት መታሰራቸው ተጠቆመ::
ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት እያቀረበ ባለው የማንነትና የራስ አስተዳዳርነት ጥያቄ ምክንያት፣ ከ50 በላይ የሚሆኑ አባላትና አመራሮቹ መታሰራቸውን የቅማንት ብሔረሰብ አመራር ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

የካቲት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. ‹‹ቅማንት የሚባል ሕዝብ የለም ያለ አካል ባይኖርም የራስ አስተዳደር ግን ሊፈቀድ አይችልም›› በሚል የክልሉ መንግሥት ተወካዮች ምክር ቤት ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም፣ በጎንደር ከተማ እስከ 300 ሺሕ የሚደርሱ ተወላጆች በተገኙበት ሰላማዊ ሠልፍ  https://www.facebook.com/photo.php?fbid=10152263428834743&set=pb.639339742.-2207520000.1394976779.&type=3&theater  ማድረጉን ተከትሎ፣ በተለይ በአመራር ኮሚቴው ላይ ጫናና ወከባ ሲደርስበት መቆየቱን ገልጿል፡፡

በመሆኑም የክልሉ መንግሥት በተቀናጀ መንገድ በአባላቱና በአመራሩ ላይ በአድማ በታኝና ፖሊስ ሠራዊት በታገዘ ኃይል አማካይነት፣ ከየካቲት 28 ቀን 2006 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ በድምሩ 50 አመራርና አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው እንደታሰሩበት ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ በመተማ ወረዳ ሰላማዊ ሠልፍ አድርገው በሰላም ካጠናቀቁ በኋላም የታሰሩ አባላት እንዳሉም አክሏል፡፡

የክልሉ መንግሥት በምን ምክንያት እንዳሰራቸው ግልጽ ባያደርግም፣ የታሰሩ አባላቱ በቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዳይጠየቁ፣ ከጎንደር በ80 እና 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኙ ዳባትና ደባርቅ ወረዳዎች ተወስደው መታተሰራቸው የሰብዓዊ መብት ረገጣ መሆኑን ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

 የቅማንት ብሔረሰብ ተወካይ ኮሚቴ በአባላቱና አመራሩ ላይ የአማራ ክልል መንግት ፈጽሞብኛል ስለሚለው እስራትና መንገላታት ማብራሪያ እንዲሰጥ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መምርያ ሲጠየቅ፣ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ኮማንደር ሰኢድ መሐመድ ምንም መረጃ እንደሌላቸው ገልጸው፣ የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምርያን ለማብራሪያ ጠቁመዋል፡፡ የሰሜን ጎንደር ፖሊስ መምርያ ፖሊስ ባልደረባ የሆኑትና ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ፖሊስ፣ ‹‹እኛ ቅማንት የሚባል ብሔረሰብ አናውቅም፤ የምናውቃቸው አማራ መሆናቸውን ነው፤›› ካሉ በኋላ፣ በበኩላቸው የሰሜን ጎደር ዞን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወደ ኮማንደር ዘመነ አመሸ ቢጠቁሙም፣ የቢሮም ሆነ የግል ስልካቸውን ሊያነሱ ባለመቻላቸው የኮማንደሩን ምላሽ ማካተት አልተቻለም፡፡  Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ምንጭ ረፖርተር ጋዘጣ
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 16, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 16, 2014 @ 9:06 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar