www.maledatimes.com ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በሀሰተኛ ታፔላ ተወንጅሏል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በሀሰተኛ ታፔላ ተወንጅሏል

By   /   March 16, 2014  /   Comments Off on ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በሀሰተኛ ታፔላ ተወንጅሏል

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 52 Second
በግሩም ተ/ሀይማኖት
እናንት በስደት አረንቋ ውስጥ ያላችሁ….እናንተ በስደት ሰቆቃ ስር ስትማቅቁ ድምጽ ያሰማላችሁ፣ እናንተ ማንም አስታዋሽ አታችሁ በሳዑዲ ዓረቢያ እስር ቤት የምትማቅቁ 5.000 አካባቢ ኢትዮጵያዊያን…ስለ እናንተ ሲል ነብዩ መሰዋዕትነት አልከፈለ ይሆን? እናንተ ከስደት ተመልሳችሁ ዞራችሁ ስደት እየወጣችሁ ያላችሁ ወገኖች በሰላም ሀገራችሁ እንድትገቡ ነብዩ ጩኸታችሁን አልጮኸ ይሆን? ቁስላችሁን አልቆሰለ ይሆን? ስትደሙ አልደማ ይሆን? ስታለቅሱ አላለቀሰ ይሆን?….እውነታችሁ እውነት ከሆነ በእሱ ለሌላው ጆሮ ከደረሰ በኋላ ድምጽ የሆናችሁ á‹«-የስደተኛ ድምጽ ጋዜጠኛ የተለያየ ሰበብ ተሰጥቶት (ታፔላ ተለጥፎለት) እስር ቤት ሲገባ የተለጠፈለትን ታፔላ አንስታችሁ እናንተም ታራግባላችሁ እንዴ?…አንዳንዶች በወያኔ ጋሻ ጃግሬነታችሁ ስም ማጥፋቱን ስታራግቡት እውነት ቢሆን እንኳን ወያኔ ካልሆነችሁ በስተቀር ስም ማጥፋቱን ተቀብላችሁ ኡኡኡአ ማለት የለባችሁም ነበር፡፡
ብዙዎች ስለነብዩ ሲራክ የተባለው የሆነው እውነት ነው ወይ? ስትሉ በግል መልዕክት መቀበያዬ በኩል ጠይቃችሁኛል፡፡ ለመጣራት እንደ ሞክርኩት ውሸት እና በውሽት ላይ የተመረኮዘ ስም ማጥፋት መሆኑን ነው የደረስኩበት፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ አንድ እና አንድ ነው……
ትላንት የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ያን ያህል ዜጎቻችንን በአደባባይ ሲያዋርዱ…ዜጎቿ ዜጎቻችንን ጨፍጭፈው በአደባባይ ሲገድሉ ኡኡኡኡ ስንል የነበረው እኮ የመረጃ ምንጭ ካደረግናቸው ውስጥ የመረጃ ፍሰቱን ሲያንዶቆዱቅ የማይነጥፍ የመረጃ ምንጭ የነበረው ነብዩ ሲራክ ነው፡፡ የሚክድ ካለ ይካድ እኔ እውነቱን ከመናገር ወደኋላ አልልም፡፡ በዚህ ሰበብ በሳዑዲ ባለስልጣኖችም ሆነ በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በተለይ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ባለው የወያኔ ኤምባሲ ጥላቻን አትርፏል፡፡ የሳዑዲ አረቢያ ሰው ደግሞ ስቆ መጥለፍን ያውቅበታል፡፡ ትላንት አብሮ ሲበላ፣ አብሮ ሲጫወት የነበረውን የሀበሻ ህዝብ ለማረድ በሰከንድ ተለውጦ አውሬ ሆኖ አደባባይ ሲያርድ አይተነዋል፡፡ ትላንት ስደት ላይ ሆናችሁ ሳለ ቁስላችሁ የጮኸላችሁም ሆናችሁ አሁን ስደት ላይ ሆናችሁ የስደት ጅራፍ እየገረፋችሁ ያላችሁ ሁሉ ይህን ምስል ሼር በማድረግ እና ፕሮፋይል ፒክቸር በመባድረግ ድምጻችንን እንድናሰማ እለምናለሁ፡፡
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 16, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 16, 2014 @ 6:48 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar