www.maledatimes.com ሶስተኛ ዙር የእሳት ቃጠሎ የሸዋ በሩ የላይኛው ታይዋን እንዳታስተናግድ ተፈርቷል። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሶስተኛ ዙር የእሳት ቃጠሎ የሸዋ በሩ የላይኛው ታይዋን እንዳታስተናግድ ተፈርቷል።

By   /   March 16, 2014  /   Comments Off on ሶስተኛ ዙር የእሳት ቃጠሎ የሸዋ በሩ የላይኛው ታይዋን እንዳታስተናግድ ተፈርቷል።

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 15 Second
ሃረር እና ሃረሮች በከፍተኛ ስጋት ተውጠዋል። ‪

ምንሊክ ሳልሳዊ = በሃረር ከተማ በተከታታይ በመብራት ሃይል እና በሲጃራ ተራ የደረሱትን የእሳት ቃጠሎዎች ተከትሎ የንግዱ ህብረተሰብ በከፍተኛ ስጋት መዋጡን የተሰበሰቡ መረጃዎች ጠቁመዋል። በዛረው እለት የምንሊክ ሳልሳዊ የሃረር የመረጃ ምንጮች ባደረሱት ሪፖርት እንደሚያስረዳው ሃረርን በእሳት በማጋየት ነጋደውን ከስራ ውጪ በማድረግ ጥቂት የስርአቱ ሰዎች እና አጫፋሪዎቻቸው ንግዱን እና የአከባቢውን አየር ለመቆጣጠር እንዲሁም ቦታውን በመሸጥ በሙስና ለመከፋፈል ያለሙት ደባ ነው ብለዋል።

በሃረር ሸዋ በር አከባቢ ሰብሰብ ብሎ መቆም አልያም የሚንቀሳቀሱ ከባባድ ተሽከርካሪዎችን አተኩሮ መመልከት እንደማይቻል እና ከአከባቢው ሰዎችን በማባረር ስራ ላይ የተሰማሩት የፈደራል ፖሊሶች ህዝቡን እያንገላቱት መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል። በዛረው እለት በሸዋ በር መንገድ ለትራፊክ ዝግ ሆኖ የዋለ ሲሆን ለ እግረኛ እስከ በላይነህ ህንጻ ድረስ ክፍት የነበረ ሲሆን ከዛ በኋላ ያለው ለእግረኛም ዝግ እንደነበር መረጃዎች ጠቁመዋል። በከባድ መኪና የተጫኑ የነዳጅ ጀሪካኖች እና በርመሎች በስፋት በየገበያ ማእከሉ ውስጥ ባሉ መጋእኖች እየተቀመጡ መሆኑ ለላው የህዝቡ ስጋት ሲሆን በመብራት ሃይል እና በሰልባጅ /ሲጃራ ተራ ከመቃጠሉ በፊት እንዲሁ አይነት የነዳጅ ጀሪካኖችን/በርመሎችን በባት ከነነዳጃቸው በገበያ ማእከሉ ውስጥ በማስቀመጥ ለእሳቱ መባባስ እና ለንብረት መውደም የሃረር ነዋሪዎች መንግስትን ተጠያቂ አድርገውታል።

መረጃዎቹ አያይዘው እንደጠቆሙት በሸዋ በር ውስጥ አንድ የገበያ ቦታ ጀጎልን አስታኮ የተሰራ “የላይኛው ታይዋን ” ተብሎ የሚታወቀው የንግድ ማእከል እጣ ፈንታ የሃረርን ህዝብ ያሳሰበው ሲሆን ይህንን የገበያ ቦታ እንዳያቃጥሉት ከፍተኛ ስጋት አለ። ይህ የገበያ ቦታ በአለም በቅርስነት ከተመዘገበው የጀጎል ግንብን አስታኮ የተሰራ ስለሆነ የገበያውን ቦታ ቢያቃጥሉት የታሪክ ቅርሶች ውድመት ይከተላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አለ ። የጀጎል ግንብን እንዳያጠቁረው ምናልባት እንዲፈርስ ትእዛዝ ሊሰጥበት ወይንም ጨለማን ተገን በማድረግ በፖሊስ የታጀበ ዘረፋ ሊያደርጉበት እና ነጋደውን ከገበያ ውጪ ሊያደርጉት ይችላል ሲሉ አንዳንድ የከተማው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዛረው እለት ዋና መወያያ የሆነው ይህ የገበያ ማእከል እጣ ፈንታ ህዝዝቡን ስጋት ላይ የጣለ ሲሆን የፈደራል ፖሊስ በበኩሉ በህዝቡ ደህንነት ላይ ተጽዕኖ ሲያደርግ ውሏል።

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 16, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 16, 2014 @ 9:39 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar