www.maledatimes.com ሕወሀትና የኢዮጵያዊነት ገጽታው በናትናኤል ካብቲመር (ኦስሎ ኖርዌይ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሕወሀትና የኢዮጵያዊነት ገጽታው በናትናኤል ካብቲመር (ኦስሎ ኖርዌይ)

By   /   March 17, 2014  /   Comments Off on ሕወሀትና የኢዮጵያዊነት ገጽታው በናትናኤል ካብቲመር (ኦስሎ ኖርዌይ)

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 43 Second

 ባለፈው የካቲት 11 2006 የህወሃት ምስረታ በአል ሲከበር ጠ/ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ያደረጉትን ንግግር ሲጀምሩ የትግራይ ሀዝብ ከአስከፊው ብሄራዊ ጭቆናና ፋሽስታዊ ስርአት ጋር ተናንቀው ……. ብለው ነበር እናም በርግጥ የህወሀት የትግል መስመር እና አለማ ምን ነበር? አሁን እንደሚባለው ኢትዮጵያን ከአስከፊው የደርግ ስርዐት ለመታደግ ወይስ በአንድ ወቅት መለስ ዜናዊ እነደተናገሩት “የድህነት ጠበቃ የነበረውን ደርግ” አሸንፎ ብልጽግና ለማምጣት?

ሕወሐት የተመሰረተበትን አላማ የሚገልጽ የህወሀት ማኒፌስቶ (በ 1968 የታተመ መጸሔት) ለዚህ ጥሩ መልስ አለው ሰነዱ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው አጠቃላይ የህወሀት አላማ እና መድረሻ “የጨቋኟ አማራ ብኄርን” ጭቆና ለማስወገድ እና የትግራይ ሪፓብሊክ ማቋቋም ነው፡፡ ስለኢትዮጵያ እድገትም ሆነ የወደፊት አላማ ያስቀመጠው የልማት እቅድ ሳይሆን  የኢትየጵያን አንድነት በሚያፈራርሱ ዘረኛ አስተሳሰብ የታጨቀ ነው፡፡ ለዚህም ይመሰላል ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር የሚለውን ዘወትር በሸገር ራዲዮ የምንሰማውንና ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚወደውን አባባል የጎሪጥ የሚመለከቱት ብዙ የነበሩት፡፡ ስለዚህም የህዝቡን ስሜት ከዚህ ለማስለወጥ ብዙ ነገሮቸ ተብለዋል፡፡ ለምሳሌ የዚሁ ስርአት አጫፋሪ በሆነው ኢትዮ ቻናል  በተባለው ጋዜጣ ላይ (እትሙን አላስታውሰውም) ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር የሚለውን ክቡር ቃል አጅግ ተራ በሆነ አቀራረብ ምንም ነገር ለዘላለም አይኖርም ስለዚህ ይህ አባባል ስህተት ነው የሚል ትርጉም ሰጥቶ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳውን  ይዞ ብቅ ያለው፡፡ በነራችን ላይ ዘላለማዊ ክብር ለሰማዕታት የሚሉንም እነሱው ናቸው አናም ዘላለም የሚለው ቃል ትርጉም ሳይገባቸው ቀርቶ ሳይሆን ጠባቸው ከኢትዮጵያዊነት ጋር ስለሆነ ነው  ፡፡

አሁን ጠዋት ማታ የሚያደነቁረን የኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳ የሚነግረን የኢትዮጵያ አንድነት የሚረጋገጠው ኢህአዴግ ያመጣው  የዘር ፖለቲካ በነሱ አገላላጽ “የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ሲረጋጋጥ” መሆኑን ነው፡፡ የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ተረጋግጧል በሚሉት በዚህ ዘመን የትግራይ ተወላጅ (የህወሃት አባል) መሆን ብቻ ሁሉም በሮች እንዲከፈቱለት የሚያደርግ ልዩ የይለፍ ካርድ መሆኑን የምናየው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ እዚህ ላይ ሁል ጊዜ የሚያስገርመኝን አንድ ማሳያ ላስቀምጥ፤ ብዙ የትግርኛ ተናጋሪ ያልሆኑ ሰዎች (በተለይም የስርአቱ አጫፋሪዎች)ንግግር ሲኖር ወይም ትንሽ ጭቅጭቅ ሲኖር ልክ የትግራይ ተወላጆች እነደሚሉት ዋእ! ዋእ! ሲሉ እንሰማለን፡፡ ዘወትር ፈገግ ቢያሰኘኝም ለኔ የዚህ ትርጉሙ ብዙ ነው በጣም ብዙ።፡፡

እንደምናስታውሰው ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጀምሮ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ስለ ሀገር ፍቅር የሚናገሩ ነገሮች በሙሉ በመንግስት ሚዲያዎቸ በአዋጅ የተከለከሉ ይመስል አስከ ቅርብ አመታት ድረስ መስማት ብርቅ ነበር፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያዊነትን ከህዝቡ አእምሮ ለመነጠል በስውር አንዳንዴም በግልጽ የሚደረጉ ግፊቶች ነበሩ፡፡ አሁንም በተለይ ለዚህ ዘመን ትውልዶች ሀገራችን የረጀም ግዜ አኩሪ ታሪከ እንዳላት ሳይሆን ተራ የሆነ የዘር ፖለቲካ እንደ አኩሪ ታሪክ ይማራሉ፡፡ የሃገራችን ህፃናት ማንታቸውን ረስተው የፈረንጅ ቋንቋ የሚናገሩ ሆነው እየተቀረጹ ነው፡፡ በሃገራቸው ቋንቋ አንድ ዓረፍተ ነገር ተናግሮ መጨረስ ሲተናነቃቸው እያስተዋልን ነው። አንድ ሰው 12 አመት መሉ ተምሮ እንግሊዝኛ መናገር የዕውቀት ጣሪያ እስኪመስል ድረስ ዛሬ በሀገራችን በተለይም በአዲስ አበባ የልጆች የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንግሊዝኛ መሆን ከጀመረ ቆይቷል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ በክልሎች አካባቢ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህረተ ከመሰጠቱ ጋር ተያይዞ (በነገራችን ላይ በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር በራሱ ችግር የለውም) እነዚህ ተማሪዎች ሌሎች ቋንቋዎችን  በተለይም አማርኛን እንዲጠሉ በመደረጋቸው የሀገራቸውን ብሄራዊ ቋንቋ መናገር የማይችሉ ዜጎች ማየት ጀምረናል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጰያ አንድነቷ ተከብሮ የኖረው በልጆቸዋ ውድ መስዋትነተ እንደሆነ ማወቅ ማንነትን ማወቅ እንጂ የብሄር ጭቆና ማስታወስ አይደለም በነገራችን ላይ ኢትዮጵየዊነትን ከአማራ ብሄርተኝነት ጋር ማገናኘት አንዱ የህወሃት አስገራሚ የውሸት ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ ሁሉም ማወቅ ያለበት ግን ህወሃትም ሆነ እርሱ የሚመራው ኢህአዴግ ከምስረታው ጀምሮ ኢትዮጰያዊያንን በዘር ከመከፋፈል ውጭ ሰለሀራችን ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ሁለንተናዊ አድገት የማይጨነቅ መሆኑን ነው፡፡ስለዚህ እኛ ኢትዮጰያዊያን ፀረ ኢትዮጰያ አቋም ያለውን አስከፊ ስርዐት ማስወገድና ልጆቻችንን ታላቅ ሀገር እንዳላቸው ማስተማር  ለነገ ብለን የማናሳድረው ሀላፊነት ይመስለኛል፡፡

ኢትዮጲዊነት ያሸንፋል!! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

natnaelkab@gmail.com

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 17, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 17, 2014 @ 8:02 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar