www.maledatimes.com ዘላለም እሼቴና አለምነው መኮንን ምንና ምን ናቸው? ታረቀኝ ሙጬ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዘላለም እሼቴና አለምነው መኮንን ምንና ምን ናቸው? ታረቀኝ ሙጬ

By   /   March 19, 2014  /   Comments Off on ዘላለም እሼቴና አለምነው መኮንን ምንና ምን ናቸው? ታረቀኝ ሙጬ

    Print       Email
0 0
Read Time:35 Minute, 16 Second

“ከሰደበኝ ስድቤን አምጥቶ የነገረኝ” ይባላል፡፡ ዶክተር ዘላለም እሼቴ በተባለ ሰውዬ  በአማሮች ላይ ተጻፈ በተባለ አንድ አጭር ደብዳቤ ላይ ተመሥርቶ አድማሱ በላይ የሚባል ሌላ አቃቂረኛ የሰጠውን ተገቢና ወቅታዊ ግብረ-መልስ በአቡጊዳ ድረ ገፅ ላይ አነበብኩና እኔም በማውቀው ቋንቋ በአማርኛ ትንሽ መናገር አሰኘኝ፡፡ የዶክተሩን ጽሑፍ ያነበብኩት የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት አጠገቤ አስቀምጬ ከአንዴም ሁለቴና ሦስቴ ደጋግሜ ነው፤ አጭር በመሆኑም ጊዜ የሚወስድ አልነበረም፡፡ መዝገበ ቃላት ያላገኘሁለት ነገር የዶክተሩን ማንነት ለማወቅ የነበረኝን ጉጉት አዘል ጥያቄ የሚመልስልኝ ነው፤ ሰውዬው የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ የማያውቅ ምናልባትም ጨረቃ ላይ የሚኖር ዓለመኛ ዜጋ መስሎኛለ፡፡ እነሱ የተወራከቡት በፈረንጅ አፍ ነው፡፡ የዶክተር ተብዬውን ጽሑፍ ከአድማሱ ጽሑፍ ውስጥ በተወነጨፈ ማያያዣ አማካይነት በኢትዮሚዲያ ድረገፅ ላይ ነው ያነበብኩት – በከፍተኛ እልህ፡፡ የለም፣ ግዴላችሁም ይሄን አማራ የሚባል መከረኛ ሕዝብ ለማጥቃት ያሰፈሰፈው በዝቶኣለ፡፡ ከድረ ገፅ አንስቶ እስከቴሌቪዥኑ እየተረባረቡበት ናቸው፡፡ ምን አር’ጓቸው ይሆን ከ23 ዓመታትም በኋላ ሊበርድላቸው ያልቻለው? ለመሆኑ የአማራ ኮከብ ምን ሆኖ ይሆን እንዲህ ጠላት የበዛበት? በእውኑ በጣም ይገርመኛል፡፡ ተኝቶም የማያርፉለት የሲዖል ትሎች ተላኩበት፡፡

ዘላለም ባለው ነገር ላይ ባልስማማም ያለውን ነገር ለማለት መብቱ እንደሆነ አምናለሁ፤ አማራ ስሙ ሲነሳ ራሱ የሚቀፋቸው የሚመስሉኝ የሚዲያ አካላትም በዚህ ዘውግ ላይ የሚሰነዘርን ዝባዝንኬ ሁሉ እውነትነቱን አንዳችም ለማጣራት ሳይሞክሩ እንዳለ ማስተናገዳቸው የነሱን ማንነት ከመግለጡ ውጪ ሌላ ጉዳት የለውምና ብዙም ቅር አይለኝም – በዚያ ላይ የርሱን የመናገር መብት እንደጠበቁ የኔንም ቢጠብቁ ጥሩ ዳኞች ባሰኛቸው ነበር፤ ግን ይሞቷታል እንጂ ይህን አያደርጉም፡፡ ምክንያቱም ከአቋማቸው ውልፊት የሚልን ነገር ማስተናገድ ይቅርና ማየትም አይፈልጉምና – ተበላልተን ጨርሰናል፤ አራዶች “ተነቃቅተናል!” ይሏታል ይቺን አካሄድ – እንአካሄድ፡፡ አለበለዚያ ፊታውራሪ አደፍርስ ደቻሳ ሻሌሞ ወይም ደጃች አስደግድግ ግደይ ቢራቱ ወይም ባላምባራስ ውቤ ጉልማ ሙክታርና ራስ ገመቹ ሐጎስ ደስታ በተናጠልም ሆነ በቡድን አማርኛን እየተናገሩ የዛሬ ስንት አሠርትና ምዕተ ዓመታት በፊት ባጠፉት ጥፋት ዛሬ ላይ ሆኖ አማራነቱን እንኳን በቅጡ የማያውቅ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋና የጎንደር ምሥኪን ገበሬ በወያኔ የቻምበር ጋዝ የዕልቂት ወረፋ እየተጠባበቀ ባለበት ወቅት ንስሃ እንዲገባና በጸጸት ዕንባ እየታጠበ አድራሻቸውና ማንነታቸው በውል ያልተገለጸ ሌሎች ወገኖችን ይቅርታ እንዲጠይቅ የሚጋብዝን የወያኔን ተልእኮ ያነገበ መርዘኛ  “ምሁራዊ ጥናት” ለማስተናገድ ድፍረት የሚያገኝ አንድም ሚዲያ ባልተገኘ ነበር፡፡ ይህ ዐረፍተ ነገር ቢረዝምም ደግማችሁ እንድታነቡልኝ በትህትና ብጋብዛችሁ ደስ ይለኛል፡፡ በእውነቱ አለመታደል ነው፡፡ በርግጥም ባቢሎን ሆነናል፡፡ ይህ ግብዣ እውነት የሚሆነው መላዋን ኢትዮጵያ እንደ አንበጣ ወርረው ሀገሪቷንና ሕዝቡን እንደመዥገር እየቦጠቦጡ ለሚገኙት ከትግሬው አብራክ ለተገኙ  የገዢ መደብ አባላት ቢሆን ነበር – ነገሩ “ዐይጥ በበላ ዳዋ ተመታ” ዓይነት ነው፡፡ ለወያኔ ወረራ የሽፋን ተኩስ የሚሰጠው አካል መብዛቱን ስመለከት “ወርቅ የጫነች አህያ የማትደረምሰው ምሽግ የለም” የሚለው የፈረንጆች ብሂል ፊቴ ላይ ድቅን ይልብኛል፡፡ በመሠረቱ ይህ ዘላለም የተባለ  ሰው አማራ ነኝ ማለቱን በጭራሽ አልቀበለውም፡፡ ለምን ቢባል አማራን አያውቀውምና፡፡ እንደእውነቱ አማራነትን ማንም ለማንም የሚሰጠው የችሮታ ጉዳይ አይደለም – ሰውዬው አማራ ቢሆንም ግድ የለኝም ለማለት ነው፡፡ በትንሹ አማርኛን መናገር ወያኔው በልካችን ሰፍቶ የሰጠንን የአማራነት ማንነት ለማግኘት በቂ ነው፡፡ ስለሆነም እንኳንስ አማርኛን ለመናገር የሚጸየፉ አንዳንድ ደናቁርት የኢትዮጵያ ምድር ሰዎች ይቅርና ስንትና ስንት ፈረንጅና ጥቁር አፍሪካዊያን አማርኛን ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ባልተናነሰ ወግ ሲጠርቁበትና በሀበሻነት የድራቦሽ ማንነትም ሲኮሩበት እያስተዋልን የኖርንበት ሁኔታ ሞልቷል፡፡ እናም እንኳንስ አማርኛን የሚናገረው የአማራው ንስሃ አባት ዶክተር ዘላለም ሲልቪያ ፓንክረስትም አማራ ነኝ ብትል ይቻላት ነበር – አማራነት ከኢትዮጵያዊነት ጋር መጣበቅ ካለበትም ነበረች ማለትም እንችላለን፡፡

በነገራችን ላይ አማራን የሚጠሉ ወገኖች አንዱና ትልቁ ችግራቸው አማራ በጎጥና በቋንቋ እየተኮማተረና እየጠበበ ወርዶ እንደነሱ ሸጥ ውስጥ ለመወተፍ የሚያበቃው ግለሰባዊና ማኅበረሰባዊ የሥነ ልቦና ልክፍት የሌለው መሆኑ ነው፤ ይህ የአማራ ኮስሞፖሊታዊ ባሕርይ የሚያበሳጫቸው ይመስለኛል፡፡ ፀረ-ኢትዮጵያውያን – የውስጦቹም የውጪዎቹም – በጣም የሚቋምጡለት ነገር ቢኖር አማራን ቢችሉ ማጥፋት ባይችሉ አስተሳሰቡን ማክሰም ነው – የሚፈሩት አማራዊ አስተሳሰብም “እኔ ሰው እንጂ፣ እኔ ኢትዮጵያዊ እንጂ፣ እኔ አፍሪካዊ እንጂ እኔ የዚህች ዓለም አንድ አካል እንጂ በዘርና በጎጥ መከፋፈል የማምን፣ እንደውሻ አጥንትና ደም የማነፈንፍ ጎሰኛና ዘረኛ ልሆን የማልፈልግና የማልችልም ንጹሕ ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሚል ነው – በዚህ ምክንያት ነው የዕልቂት ዐዋጅ የታወጀበት፤ ሌላ ይቅርታ የሚያስጠይቅና ጸጸትና ንስሃ ውስጥ የሚያስገባ ወንጀልም ሆነ ኃጢኣት የለበትም፤ ይህንንም ስል እንደማንኛውም ሕዝብ አንዳንድ አባላቱ በራሱም ሆነ በሌሎች ላይ ጥፋት የማይፈጽሙ ቅዱሣንና ብፁዓን ናቸው የማለት ወያኔያዊ ድፍረት የሌለኝ መሆኔን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ጥፋትና ልማት ሰብኣዊ እንዲ ብሔረሰባዊ አይደለም – አማራን በአጥፊነት ሌላን በአልሚነት የመመደብ አዝማሚያ ካለ ዕብደት ነው፡፡ ቀፎው ዘላለም ይህን ይረዳልኝ፡፡ አማራ ቢወቅጡት ቢፈጩት ከእንግዲህ ወደሸጥና ፈፋ ወርዶ የሚወተፍላቸው አይደለምና ጠላቶቹ ቁርጣቸውን ቢያውቁ ደስ ይለኛል – እንደግል አመለካከቴና እንደአካሄድም፡፡ በመሠረቱ ዘላለም አማራ ነኝ ማለቱ እውነትም ሀሰትም ሊሆን ይችላል፤ በረከት ስምዖን፣ አዲሱ ለገሠ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ታምራት ላይኔና ሌሎችም አማራ ነን ብለው ድርቅ ካሉ ደግሞ ማንም መሆን የማይችልበት ምክንያትም የለም፡፡ አሜሪካዊው ጆን ኬሪስ አማራ ነኝ ቢል መቀበል እንጂ ምን ምርጫ ይኖረናል? ሆ!  አማራ አናት ላይ ፊጥ ያላችሁ ኧረ እባካችሁን ውረዱለትና ይረፍበት!

የአስተሳሰብ ጓደኛው አለምነው መኮንንም አማራ ነኝ ብሎ ሲያበቃ በስድብ አጥረግርጎን የለም በዚያን ሰሞን? አማራ እንኳንስ ለስድብ አንገቱን ለካራ አመቻችቶ ከሰጠ ሩብ ምዕተ ዓመት ሊሆነው ነው – ዕድሜ በስሙ ሀገር እየገዙ ለዚህ ሰቆቃ ለዳረጉት ኢትዮጵያውያን መኳንንትና መሣፍንት፡፡ ራሱ ልጋጉን ሳይጠርግ ልጋጋም የሚል አማራ ነኝ ባይ የወያኔ አፋዳሽና ሆዳም ባንዳ አማራን በተሳደበ ማግሥት ይሄ ዘላለም እሚሉት ሰው በለሰለሰ አንደበትና በጨዋ ቋንቋ ከአለምነው ያልተለዬ መልእክት በኢትዮሚዲያ ማስተላለፉን ስረዳ በርግጥም በዚህ የተገፋ ሕዝብ ላይ የተቀነባበረ ዘመቻ ከውስጥም ከውጪም እንደተከፈተበት መገንዘብ አላቃተኝም፡፡ ግን ለምን? ግፍ ሲበዛ ወደራስስ ይዞር የለምን? ለምን እየተስተዋለ አይሆንም?

የዘላለም ጽሑፍ ዋነኛ መልእክት አማራው ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ስላሰቃዬና ስለበደለ አሁን ያሉት አማሮች በነቂስ ወጥተው የበደሉትን ይቅርታ ይጠይቁ ነው፡፡ የኛ ማንዴላና የኛ ማዘር ተሬዛ ዶፍተር ዘላለም በዘወርዋራ መንገድ የሚለን ያለ አማሮች እግዚኦ በሉና ከኦሮሞና ከጉራጌ፣ ከሲዳማና ከዳዋሮ፣ ከጀምጀምና ከኮንሶ፣ ከወላይታና ከሃዲያ፣ ከጠምባሮና ከከምባታ፣ … ታረቁ አለበለዚያ የአባቶቻችሁና የአያት ቅድመ አያቶቻችሁ ኃጢኣት በእናንተ ላይ መፍረዱን እንደቀጠለ ይቀራል በማለት እያስፈራራን ነው፡፡ የሰውዬው አባባል እውነትነት ቢኖረው ኖሮ አነሳሱ የሚጠላ አይደለም፤ እንደዚህ ዓይነት ክስተቶች በአርመኖችና በቱርኮች እንዲሁም በሌሎች የቅኝ ገዢና ተገዢ ሀገሮች መካከል ታይተዋል፡፡ ይሁንና ይህ ሰው አንድም ሞኝ ነው(foolish or naïve at best)፤ አንድም የኢትዮጵያን ታሪክ ፈጽሞውን አያውቅም፤ አንድም አእምሮው ያልበሰለ ጮርቃ ነው፤ አንድም በአማራው ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይና መከራ አናፍሎት የሚሠራውን ስላሳጣው ሳይታወቀው የወያኔን ወንጀል በተበዳዩ በአማራው ላይ ደፍድፎታል፤ አንድም እንደነአለምነውና እንደሙሉጌታ አሥራት፣ እንደነገነት ግርማና ክፍሌ ወዳጆ፣ እንደነ አሰፋ ብሩና እንደተቀዳ ዓለሙ፣ … ሰውነቱን ለወያኔ ያከራዬ አጋሰስና ገልቱ ዜጋ ነው (ሰለጠነ በሚባለው ዓለም ችግረኛ ሴቶች ማኅፀናቸውን ለሀብታሞች እያከራዩ ገንዘብ ያገኛሉ ይባላል፤ የነዘላለምም የነአለምነውም የነብርሃኑ ዳምጤም እንደዚያው ነው – ሰውነትን፣ አንደበትን፣ ምንን ምናምንን – የሚነገርንም የማይነገርንም የሰውነት አካል ባወጣ ማከራየትና ጃዝ ሲባሉ እንደውሻ መጮኽና እንደአህያ ማናፋት፤ ተናገሩ ወይ ጻፉ ሲባሉ ሼክስፒርን በሚያስንቅ የቋንቋ ምጥቀት የጅሎችን ጭንቅላት በአሰስ ገሰስ ቱሪናፋ ማሾር – ከዚያም ወያኔን በዕድሜ ማራዘሚያነት ማገልገል(ARV – antiretroviral)፤ ከዚያም ሆድን በቆሻሻ መኖና በቆሻሻ አልኮል መቆዘር፤ ከዚያም በሥነ ልቦና ቀውስ መቆዘምና መዋተት፣ ከዚያም ጥቁር ታሪክ ጥሎ ዘር ማንዘርን ማዋረድ – ከዚያም … ከዚህ በላይ ምን ከዚያም አለና ዳሩ)፡፡ አዬ መማር! ትምህርት እንዲህ እንደዋዛ ገደል ይግባ?

እንዲያ ባይሆን ኖሮ አማራው ባለፈ ታሪኩ ጥፋት እንኳን ቢኖበት በአሁኑ ወቅት እንደዐይጥ በተገኘበት እየተጨፈጨፈ በሚገኝበት ሁኔታ፣ መንግሥታዊ ጄኖሳይድ ታውጆበት ከዐርባጉጉና በደኖ ጀምሮ ያለዕረፍት በጥይትና በርሀብ፣ በመፈናቀልና ሆን ተብሎ በሚሰራጭ በሽታና የኤድስ ቫይረስ፣ ሆን ተብሎ በመርፌ በሚሰጥ ዘር አምካኝ መርዝ ትውልድ እንዲከስምና አማራ እሚባል ከናካቴው እንዲጠፋ እየተደገረበት ባለበት ሁኔታ እንዲህ ያለ የግፍ ግፍ ሊጻፍ ባልተሞከረ ነበር፡፡ ስለዚህ እላለሁ – ስለዚህ ዘላለም የሚባለው ደደብ ሰውዬ የሸንጎ ፍርድ የሚገባው የመጨረሻ ገልቱና የአማራ ጠላቶች ተላላኪ ነው – እዚህች ላይ የኢትዮጵያዊነት ጨዋነት ባህል ባይገድበኝ ኖሮ “የውሻ ልጅ!” ብዬ ብሰድበው ምንኛ እልኼን በተወጣሁ ነበር፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው – ባህላችንም መጽሐፉም አትሰዳደቡ አትነቃቀፉም ይላላ! ጅል ሰው አያጋጥማችሁ ወንድሞቼ፡፡ ደደብነቱ አስገድዶኝ እንዲህ ስናገረው ስለርሱ ሞኝነትም ስለኔ የመረረ ስሜትም በደምሳሳው ስለሁለታችንም በጣም አዝናለሁ [ይቅርታና ‹ደደብ› ስል ሌላ ቃል ከማጣት አንጻር ቀለል ባለ የፈረንጅኛው አገላለጽ idiot ወይም moron ለማለት እንጂ stupid ለማለት ፈልጌ እንዳልሆነ በትህትና ልግለጥ]፡፡ ይህ ሰው የይቅርታን ቃል ምንነት በፍጹም አያውቀውም የሚል ግምት አለኝ፡፡ ኢትዮሚዲያም የይቅርታን ምንነት ሊያስረዳው አልቻለም ወይም አልፈለገም፡፡ የወደቀ ግንድ ምሣር ይበዛበታልና ግዴለም ሁሉም በዚህ ምሥኪን ሕዝብ ላይ ያለውን ሽብልቅ ሁሉ እያነሳ ይቀርቅብ – “እከክ የሰጠ ጥፍር አይነሳም” ይላሉ አሉ ወዳጆቻችን ዐረቦች፡፡ ዋናው ጉዳይ ግን ለሁሉም ጊዜ ያለው በመሆኑ እንዲህ በግልጽና በአደባባይ በአማራው ላይ ያላገጡና ያሾፉ ሁሉ የውሻን ደም በከንቱ የማያስቀረው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሥራቸውን እንደሚሰጣቸው መረዳት የሚገባን መሆኑን አለመዘንጋት ነው፡ አሁን ዘመኑ የነሱ ነው፤ ዘመነ ዕቡያን ወዕኩያን፡፡ እነአያ ምንተስኗቸው አሁን ቢፈልጉና ሲፈልጉ ሟችን ለገዳይ ይቅርታ እንዲጠይቅ ሊያደርጉት ይችላሉ – ዘላለምም ሆነ ወንድሙ አለምነው እያደረጉ ያሉትም ይህንኑ ነው – በጌቶቻቸው ወያኔዎች ጃዝ ባይነትና ድርጎ ከፋይነት፤ የሆድ ነገር አያድርስ፡፡ ማን ነበር “ሆድ እንኳንስ ከኋላችን አልሆነ፤ ቢሆን ኖሮ ገፍትሮ ገደል ይከተን ነበር” ያለው? ጥሩ ብሏል፤ እንኳንስ ከፊት ለፊታችን ሆነ – ባይሆን ከፊታችን ተንጠልጥሎ ይጎትተን፡፡

በመሠረቱ የሞተ ሰው ማንንም ይቅርታ አይጠይቅም፤ እንዲጠይቅ መፈለግም ቂልነት ነው፡፡ ሣሞራ የኑስ “አማራን አርቀን ቀብረነዋል” ሲል፣ የእንጨት ሽበቱ አቦይ ስብሃት ነጋ “ኦርቶዶክስንና አማራን አርቀን ቀብረናል” ሲል፣ የፈራረሰው መለስ ዜናዊ “አማራን ገድለን ቀብረናል” ሲል፣ ድምፂ ወያኔ “አማራ አህያ ነው፤ ቦቅቧቃም ነው፤ እያሳደድክ ጀርባ ጀርባውን በለው” ሲል፣ አማራው በአርሲ፣ በማጀቴ፣ በጉራፈርዳ፣ በቤንሻንጉል፣ በሐረር፣ በሶማሌ፣ በጅማ፣ በአዲስ አበባ፣ በክልሉ፣ ወዘተ. ሕጻን ዐዋቂው አንገቱ በሠይፍ እየተቀላና ደረቱ በጥይት እየተቦተረፈ ሲረፈረፍና ከኖረበት ቀየ ባዶ እጁን ሲባረር … ይህንና መሰል ውርጅብኝ በአማራው ላይ በሥነ ልቦናም በአካልም ሲደርስበት በዳዮች ይቅርታ እንዲጠይቁት ሃሳብ ያቀረበ አንድ እንኳን ዘላለም እሼቴ ነበረ ወይ? ወይንስ አማራው ከውሻ ያነሰ ነፍስ ያለውና ግፍና በደሉ ሊታይለት የማይገባው እዚህ ግባ የማይባል ፍጡር ይሆን? ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተገኘና ነው ለዚያውም አማራ ነኝ በሚል – አማራ መሆኑ ግን በሚያጠራጥር ሰው አማራው ይቅርታ እንዲጠይቅ በተቅለሰለሰ በእግረ መንገድም ለሹመት ይሁን ለሽልማት የሚቅመደመድ በሚመስል አንደበት የሚጠየቀው? ምንድን ነው እየሰማን ያለነው? አእምሮ ወዴት ተሸሸገ? ማሰብን ምን በላው? ለመሆኑ ዘላለም ማነህ? ምንድንስ ነህ? በሕይወት ካለህ እስኪ አናግረኝ፡፡ ይህን ዕውቀት ከየት አባህ ማለቴ ከየት አገኘኸው? “ወይ መዓልቲ!” አለ ትግሬ – እንደኔ ቢጨንቀው፡፡ እኚህ ወያኔዎች በየወሩ አዳዲስ አወዛጋቢ አጀንዳዎችን እየቀረፁ ቅንጭላታችንን ሥራ ያስፈቱ á‹«á‹™ እኮ፡፡ እኒህ ሸረኞች፡፡ ደግሞም የተባባሪወቻቸው ኆልቁ መሣፍርት ማጣት፡፡

ጎበዝ፣ ባይቆጭ ያንገበግብ ይባላል፡፡ በጣም አዝናለሁ፡፡ ማጽናናት ሲገባ እንዲህ ያለ የበደል በደል፣ እንዲህ ያለ የግፍ ግፍ ከወያኔ መንደር ካልሆነ በስተቀር ከማንም ሊፈልቅ አይችልም፡፡ አድማሱ በላይ በጥሩ አነጋገር ጥሩ መልስ ሰጥተሃልና የአማራው ውቃቢ ይጠብቅህ ልጄ፡፡ ሌሎችም ባንተ መጣጥፍ ሥር እንደኔው የተናደደ መልስ ሰጥተዋልና የበለጥሻቸው አድባር በሄዱበት ትከተላቸው፡፡ ጥቂቶቹን ከዚሁ ከአቡጊዳ ድረገፅ ላይ ጨልፌ እንዳሉ ከዚህ በታች ላስቀምጥና የንዴትና ቁጭት ብዕሬን ለአሁኑ ልስቀል፡፡ ከተናግሮ አናጋሪ ግን ይሠውራችሁ ወገኖቼ – ቀንድ ነው ጭራ እምትሉትን አስበቀለኝ እኮ፡፡ ደግሞ ምንም ኤዲት ሳላደርግ እንዲሁ እንዳለች ነው እምልካት፡፡ ሰውን ግን ምንድን ነው እንዲህ እያጀዘበው ያለው? የአብዬን ወደ እምዬ አሉ? ማንም የሁሉም ዘር ጥጋበኛ በአማራ ስም እየተነሣ አዳሜን እየቀጠቀጠ ገዛና ሁሉም ያለፈ የታሪክ ሰምበርና ጠባሳ በዚህ ምሥኪን ሕዝብ መሳበብ አለበት? ግን ግን ዶፍተሩ እንደተባለው የአለምነው መኮንን ወንድም ይሆን? ጠርጥር ገንፎም አለው ስንጥር፡፡

  1. Ethioman –   Well said mr Admasu! The politics of anger and hate should end
    We are one people against a system of division and dictatorship
  2. ጊታው   -    ምን አልባት ዶ/ር ዘልአለም የአለምነው ዘመድ ይሆን? ጎበዝ! የዚህ ሁሉ ችግር ምንች ወያኒ ብቻ የሚነግረንን ታሪክ መስማታችን ነው;; ጆሮአችንን ለታሪክ ሰዎች ቅድሚያ እንስት;; ፖለቲከኖችን በተለይ ጎሳን መሰረት ያደረጉትን አንከተል;;የህዝብ ልጅ መሆን ይሻላል;;
  3. Anonymous  –  One of our serious handcap of present day Ethiopians is our blind affinity to worship those who have/or say they have a PhD. It is not surprizing because education is highly valued in Ethiopia. Zelalem Eshete is a remarkably foolhardy idiot no matter what his cousin says about his narrow and artificial ‘scholastic apptitude’ Anyone with an elementary common sense would recoil with the idea or a suggestion of an Amhara collective guilt let alone offer apologies. We know that the extremly naive and foolhardy Welloye, Wallelign Mekonen, was manipulated by his Tigrean and Eritrean handlers and was idiot enough to publish what they wrote for him in his name. Once their purpose was achieved they informed about his hijacking of a plane to the Ethiopian authorities and his group was killed just after they left Bole airport.Better to get rid of the fool FAST. That is the Wallelign of the Tigreans and their “hero” Maybe his follower Zelalem may not even be aware of this and is expecting some reward from TPLF. But they know a fool inside out and know how to deal with his type. They will make him roll in their mud for some time first. We will soon see.
  4. Saaby – This guy called zelalem is not even using his real name. The guy is a Tplf cadre pretending to be amhara and doing the job which Tplf started in Dedebit 40 years ago to annihilate the amhara population. It is a campaign of genocide and persecution on the amhara population which is an openly known agenda of TpLF.

The dead psychopath and fascist meles zenawi let the cat out of the bag when he said in 2005 that interahawme is coming to Ethiopia. He was reiterating his agenda of evicting, dispossessing, massacring, and persecuting the amhara.

Make no doubt about it the fascist woyane are preparing the ground for more genocide and [ersection of amharas and we should not sit and watch from the side lines. Any one who has seen what the fascist Tplf can do and has done has to take heed.

  1. Derba Gochu –

“No, Revolutionaries” must repent In truth, it is the so called “revolutionaries” who should repent. They have grossly misrepresented the politics and aspirations of Ethiopian people for the last fourty to fifty odd years. Their analyses have largely been wrong. Their conclusions were as bad or even worse. They picked up a complex ethnic issue took it through a complicated thought process, when they hit the walls they come up with a very simplistic solution in the form of secession. To justify this fix they cut and paste f’..up Stalin’s gibberish or references from the man from the far corner of the world (Mao). You don’t need to have a PhD to work out that Ethiopia has very little resemblance to those countries conditions. Poor Ethiopia somehow was put on a par with the industrialized nations of Europe as a colonizing power who came in search of Labor and raw materials for their industries. How sillier and ridiculous could it get? No one ethnic group is immuned from dominating act and ill doing to other ethnic groups, in the past and even today. To paint a bad and good guy scenario was wrong and as we all know that only happens in Hollywood. The honest thing to do is to acknowledge our problems and formulate solutions to solve them with honesty and in fairness in a collaborative manner and move forward. No point exaggerating the problems beyond what they already are and run for cover in the form of simplistic cope out exercise (secession). Simply, the analysis we have been fed for so long lacked originality massively and totally ignored the aspirations of the Ethiopian people. It reads like this. “I have read it and it worked elsewhere. Accept it.” One should not dictate while championing Democracy. Because of this Ethiopia endured incalculable Human and economic cost. Thanks for the resilience of the Ethiopian people. In the face of all the hate propaganda, a call to rise up to send them at one another’s throat and divisions thrown at them they managed to stick together and have been riding the storm as best as they could. What one should do is help them to stick together and face the challenges in life as one and not disharmonize them.
In the past year, a couple of prominent contributors, have put up separate apologies and thought that was a good beginning and hoped the different organizations will do the same but it is disappointing to see none following suit. The quest for repentance should be taken up by the “Revolutionaries” and not by any Ethiopian ethnic group. The writer should be commended for highlighting this fallacy.(ሠረዝ የተጨመረ)

(tmuchie95@gmail.com)

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 19, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 19, 2014 @ 9:33 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar