www.maledatimes.com [የሳዑዲ ጉዳይ] ዲፕሎማቱ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤትን ተቆጣጠሩ፤ ለተመዘበረው 1.7 ሚሊዮን ሪያል «ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ» ወላጆችን ባለዕዳ አደረጉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

[የሳዑዲ ጉዳይ] ዲፕሎማቱ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤትን ተቆጣጠሩ፤ ለተመዘበረው 1.7 ሚሊዮን ሪያል «ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ» ወላጆችን ባለዕዳ አደረጉ

By   /   March 28, 2014  /   Comments Off on [የሳዑዲ ጉዳይ] ዲፕሎማቱ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤትን ተቆጣጠሩ፤ ለተመዘበረው 1.7 ሚሊዮን ሪያል «ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ» ወላጆችን ባለዕዳ አደረጉ

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 1 Second

ከኢትዮጵያ ሃገሬ ከሳዑዲ አረቢያ ጂዳ

ከ1500 በላይ በሆኑ ወላጆች በባለቤትነት እንደሚተዳደር የሚታወቀው በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት በዲፕሎማቱ ቁጥጠር ስር መዋሉን የሚገልጹ ምንጮች ለዛሬ ማርች 28 2014 በኤምባሲው ደብዳቤ የስብሰባ ጥሪ ተላልፎላቸው የነበሩ ወላጆች ባለመገኝታቸው የስብሰባው አዳራሽ ባዶ ሁኖ መዋሉን አክለው ገልጸዋል፡:

ንበረትነቱ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እንደነበር የሚነገርለትን ት/ቤት ኤምባሲው ለመቆጣጠር እያደረገ ያለው ጥረት ከግልጥቀም የመነጨ መሆኑንን የሚናገሩ ውስጥ አውቂ ምንጮች ት/ቤቱን ከኮሚኒቲው በመነጠል ከወላጆች በሚመረጥ የቦርድ አስተዳደር ይመራል በሚል ሽፋን ላለፉት 5 አመታት በት/ቤቱ ጥሬ ገዝንዘብ ላይ ግልጽ የሆነ ምዝበራ መፈጸሙን ይናገራሉ። ይህን አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ዲፕሎማቱ ልግል ጥቅማቸው ለማዋል ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልበጠሱት ቀጠል እንደሌለ የሚናገሩ ወገኖች ከዛሬ 7 ወር በፊት ለይስሙላ ህብረተሰቡ በቦርድ አባልነት ለመሳተፍ የሚያስችለውን ማስታወቂያ አውጥተን የሚቀርብ ሰው አጣን ለማለት የመወዳደሪያውን ማመዘኛ ዲግሪ እና ከዛ በላይ ከፍ በማድረግ ማንኛውም ወላጅ በቀላሉ ማቀረብ የማይችላችውን ተጨማሪ ድብዳቤዎች እንዲያቀርብ የሚጠይቅ መስፈርቶችን በማስቀመጥ ወላጆች ት/ቤታቸውን ለማስተዳደር እንዳይችሉ መደረጋቸውን ይገልጻሉ።

ይህ በዚህ እንዳለ ወላጆች ባላቸው አቀም እና የትምህርት ደረጃ አቋቁመው ለዘመናት ያለማንም ድጋፍ እና ረዳት በማስተዳደር ለዚህ ያበቁትን የልጆቻቸውን ዕውቀት መገብያ ማዕከል ኤምባሲው ለመንጠቅ በሪያድ የዲያስፖራው ሃላፊ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ተመስገን ኡመርን በጓሮ በር አሾልኮ በመስገባት ቀደም ብለው ያዘጋጇቸውን ታማኝ አገልጋይ የቦርድ አባላት ስልጣን ካፀደቁ በሃላ ዛሬ ወላጆችን ለማደናገር በኤምባሲው ማህተም በተደገፈ ደብዳቤ ስብሰባ መጥራታቸው የዲፕሎማቱን አላውቂ ሳሚነት በግልጽ ያሳይል ተብሏል።

ዲፕሎማቱ በኤንባሲ ሽፋን ህገወጥ ተግባር በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ የሚናገሩ ወገኖች 1500 በላይ የሆኑ ወላጆች በባለቤትነት እንደሚቆረቆሩለት የሚነገርለትን ት/ቤት ቁጥራቸው ከ 50 የማይበልጥ የት/ቤቱ ጉዳይ የማይመለክታቸውን ደጋፊዎቻቸውን ሰብስበው አዳራሽ በማስገባት «አይጥ በበላው ዳዎ እንዲሉ » ምንም የማያውቁትን ወላጆች የ 1.7 ሚሊዮን ሪያል ባለእዳ የሚያደርግ ሪፖርት በዲይስፖራው ሃላፊ አማካኝነት በማቅረብ ዲፕሎማቱ የመረጣቸውን ህገ ወጥ የቦርድ አማራር አባላት ህጋዊ ለማድረግ ከወላጆች ጀርባ ዛሬ የፈጸሙት ደባ በህግ ሊያስጠይቃቸው የሚገባ ብሄራዊ ወንጀል መሆኑን ገልጸዋል። ስብሰባው ላይ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ህሰን መገኘታቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል። በዚህ ዙሪያ የዲያስፖራውን ሃላፊ አቶ ተመስገን ዑመርን ለማነጋገር ያደርኩት ሙከራ አልተሳካም::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on March 28, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 28, 2014 @ 8:30 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar