www.maledatimes.com በ250 ሚሊዮን ዶላር ለሚገነባው የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አምስት አማካሪ ኩባንያዎች ቀረቡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በ250 ሚሊዮን ዶላር ለሚገነባው የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አምስት አማካሪ ኩባንያዎች ቀረቡ

By   /   April 5, 2014  /   Comments Off on በ250 ሚሊዮን ዶላር ለሚገነባው የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አምስት አማካሪ ኩባንያዎች ቀረቡ

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 7 Second
በ250 ሚሊዮን ዶላር ለሚገነባው የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አምስት አማካሪ ኩባንያዎች ቀረቡዋና ዜና
 ተጻፈ በ  

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ተርሚናል ማስፋፊያ ግንባታ ሥራ የሚቆጣጠር፣ ከአዲስ አበባ ውጪ ለመገንባት ያሰበውን ግዙፍ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የሚያጠና አማካሪ ድርጅት ለመቅጠር የሚያስችለውን ዓለም አቀፍ ጨረታ በቅርቡ አውጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ ዳዊት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ 38 ኩባንያዎች የጨረታ ሰነዱን የገዙ ቢሆንም አምስት ኩባንያዎች ብቻ ፕሮፖዛላቸውን ለድርጅቱ አስገብተዋል፡፡ ኩባንያዎቹ ያቀረቡትን ፕሮፖዛል የድርጅቱ የጨረታ ኮሚቴ በመገምገም ላይ መሆኑን የገለጹት አቶ ዳዊት፣ በሦስት ሳምንት ውስጥ ግምገማው ተጠናቆ ውጤቱ እንደሚገለጽ አስረድተዋል፡፡

የማስፋፊያ ግንባታው ዲዛይን ‹‹ሲፒጂ›› በተሰኘ የሲንጋፖር ኩባንያ የተሠራ ሲሆን፣ የኤርፖርቶች ድርጅትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለሙያዎች በረቂቅ ዲዛይኑ ላይ አስተያየት እየሰጡ ናቸው፡፡ በዲዛይኑ ሥራ ላይ የመጨረሻ ማስተካከያ ሥራ ተደርጐ የመጨረሻው ዲዛይን ከሁለት ሳምንት በኋላ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ታውቋል፡፡

ኤርፖርቶች ድርጅት የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ተርሚናል በ250 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ለማስፋፋት በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡ ለፕሮጀክቱ ወጪ የሚውል ገንዘብ ከቻይና መንግሥት በብድር ተገኝቷል፡፡ የብድር ስምምነቱን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሐሙስ አፅድቆታል፡፡

የማስፋፊያ ፕሮጀክቱን የሚገነባው ‹‹ሲሲሲሲ›› የተሰኘው የቻይና ኩባንያ ነው፡፡ አዲሱ ተርሚናል የመንገደኞች መሳፈሪያ ቦታዎች፣ ምግብ ቤቶች፣ መዝናኛዎችና የመገበያያ ሥፍራዎች ይኖሩታል፡፡ የመንገደኞች መሳፈሪያ በሮች፣ ድልድዮችና ሰፊ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራ በማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ተካተዋል፡፡ ሌላው የፕሮጀክቱ ዋና አካል የቪአይፒ ተርሚናል ግንባታ ነው፡፡ የቪአይፒ ተርሚናሉ በዓይነቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲሆን የአገር መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ዲፕሎማቶች ይስተናገዱበታል፡፡

ተርሚናሉ የተለያዩ ሳሎኖች፣ የመሰብሰቢያ ክፍሎች፣ የመዝናኛ ሥፍራዎች፣ የቀረጥ ነፃ ሱቆች፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከልና የተለየ የመኪና ማቆሚያ ይኖረዋል፡፡

የግንባታ ሥራው በሦስት ዓመታት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡ ኮንትራክተሩ የግንባታ ሥራ ክፍያ መጠኑን ለኤርፖርቶች ድርጅት በቅርቡ እንደሚያቀርብ፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል በክፍያ ዙሪያ ድርድር እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሲሲሲሲ ለግንባታው የሚውል ገንዘብ በብድር ከቻይናው ኤግዚም ባንክ ያስገኘ በመሆኑ ፕሮጀክቱ ያለጨረታ ተሰጥቶታል፡፡

የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ተርሚናል ማስፋፊያ ሥራን የሚቆጣጠረው አማካሪ ድርጅት ኤርፖርቶች ድርጅት ከአዲስ አበባ ውጪ ለመገንባት ላሰበው ግዙፍ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ጥናት ያካሂዳል፡፡ ይህ ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ የሚችልባቸው ሦስት ቦታዎች በእጩነት የተመረጡ ሲሆን እነርሱም ሞጆ፣ ዱከምና ተጂ ናቸው፡፡ ኤርፖርቶች ድርጅት በቦታ መረጣ ላይ ጥናት በማካሄድ ላይ ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያደርግለትም ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ጨረታውን የሚያሸንፈው አማካሪ ድርጅት የአዋጪነት፣ የቴክኒክና የፋይናንስ ጥናቶች እንደሚያካሂድ እንዲሁም የኤርፖርት ማስተር ፕላን እንደሚያዘጋጅ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም አዲሱን አውሮፕላን ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጋር እንዴት ማስተሳሰር እንደሚቻል ጥናት ሠርቶ ያቀርባል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on April 5, 2014
  • By:
  • Last Modified: April 5, 2014 @ 5:10 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar