www.maledatimes.com ስደት መረረን Gedion from Norway - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ስደት መረረን Gedion from Norway

By   /   September 1, 2012  /   Comments Off on ስደት መረረን Gedion from Norway

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 22 Second

 

ተሰደን ተሰደን አላልቅ ስላልን እንጂ በጣም ተሰደናል እኮ፥ አገራችንን ለቀን እየወጣን ለባዳ ሳናቀው እያስረከብን እኮ ነው፥፥

የድሮው የማናቀው የቅኝ ግዛት ታሪክ ተከረባብቶ ወደ ወደተስፋይቱ ምድር ወደ አገሬ ኢትዮጵያ ከች እያለ ነው፥፥ እርግጥ ነው አንዳንዴም የመለስ ስርአት ሲመረን አንዳንዴም የነጮቹ ኑሮ ሲያስቀናን መጀመርያ ትዝ የሚለን ስደት ነው፥፥

አሁን አሁን ግን የምንሰደደው የሆነ ከአቅም በላይ ፍለፊታችን ግትር ያለ የሰይጣን ተራራ የሚሉት አይነት ባላንጣ የቆመ መሰለኝ፥፥ እኛም ደሞ ተልፈስፍሰናል፥ ምን እንደምንፈልግ እንኩአን ያወቅነው አልመሰለኝም፥፥ ሰይጣኑን በማስወጣት ፈንታ ለሰይጣኑ መገበር ጀምረናል፥፥

ሁሉም ተቃዋሚ ነኝ ይላል ፥ ሁሉም መለስን ለማውረድ እሰራለው ይላል፣ ሁሉም ስለአንድነት ያወራል,፣፥ ግን ደሞ አብሮ ለመስራት የራሱ ፕሮግራምን ብቻ የኢትዮጵያ ህዝብ ፕሮግራም አርጎ ያያል፥፥ ይሄን ያህል አመታቶች በነጮቹ አገር እየኖርን እንኩአን ከነሱ ለመማር አልቻልንም,፣ ነው ወይስ እኛ ልንከተል የምንፈልገው የፖለቲካ አይነት ገና አልተፈተረም፥ ነው ወይስ አስማት ነው የምንፈልገው፥፥

እኔ በበኩሌ ስለወያኔ መስማት ሰለቸኝ እንዴ አስቡት እስኪ እኔ በአንድ የኖርዎይ  ጋዜጣ ላይ እንዳነበብኩት እንግዲህ ወያኔ ወይም ወይ ያኔ በ1997 ምርጫ ላይ የነበረው የደጋፊ ብዛት 800000 ነበር አሁን ኦፊሻሊ የሚታወቀው ወደ 3 000 000 ደጋፊ እንዳላቸው ነው፣ እሱም በተለያያ መንገድ በነጋዴው ላይ በተማሪው ላይ በሰራተኛው ላይ በሚደርሱ የተለያዩ ጫናዎች ምክንያት ነው የሚል የራሴ ከፍተኛ እምነት አለኝ፥፥ ከነዚህም ውስጥ ደሞ ሆዳም ለሆዱ አዳሪ የሆነው ይበዛል ባይ ነኝ፣፥ እንኩአን መለስ ሃሳብ ሰቶ አደለም ሃሳብ ለመስጠት ሲያስብ ሆዳሞቹ ሁለት እጃቸውን ሊያወጡ ይችላሉ ድሮ ልጅ እያለን በቀደመ በቀደመ እያልን እንደተጫወትነው ማለት ነው፥፥ በቻ ባጭሩ ቁጭ ብሎ መደናነቅ ነው፥

 

 

ያም ሆነ ይህ ግን አስቡት ይሄ ማለት ግን ወያኔ በውነት ሃይል ስላለው አደለም እየገዛን ያለው እኛ አሜን ብለን ስለተገዛንላቸው ነው እንጂ፥ ወያኔ እንዲወርድ ብንፈልግም  ዳሩ ግን ታግለን ሳይሆን ተአምር ወይም አስማት እንጠብቃለን፥፥

አንዳንዱ ወያኔን በጣም ይጠላል ግን ደሞ መቃወም ያስብና አገር ቤት መስራት የጀመርኩት ቤት ጭቃው ተለጥፎ ሳያልቅ ፣ ለክረምት ሂጄ ቤተሰቤን ሳላይ፥ አዲስ  አበባ ናፍቃኛለች ምናምን ወይም ደሞ ወገቤን መቀነት ሳልታጠቅ ቀርቼ ነው ሃተታ ያበዛል፥ ሌላው ደሞ ጠንካራ የተቃዋሚ መሪ የለም ይላል፥፥

እና ምን ይሻላል፥ በቃ አገራችንን እየለቀቅን ለወያኔና ለቻይና እናስረክብ ? እኔ በበኩሌ ስደት መሮኛል፥

አሁን መለስ ሞቷል፥ ሃይለማርያም ነው የሚቀጥለው ሹፌር፥፥

ግን አይገርምም አቶ በረከት መለስን ምን ያህል ቢወደው ነው 2 ወር ሙሉ አልሞተም እያለ በአለም ህዝብ ፊት ሲያወራ የነበረው፥ እንግዲህ መለስ እኔ አልሞትም ብሎ አሳምኖት ይሆን፥፥

በሉ እዚጋር ወራጅ አለ፥ ሰላም ሁኑ

የዋልድባ መነኮሳት እምባ ስራውን እየሰራ ነው፥፥

እኛ ብንፈዝም ኢትዮጵያን ግን ሁሌም እግዚአብሄር ያያታል፥

አሜን

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 1, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 1, 2012 @ 6:07 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar