www.maledatimes.com ፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ተከሰሱ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ተከሰሱ

By   /   April 16, 2014  /   Comments Off on ፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ተከሰሱ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 9 Second

 

በየካቲት ወር 2005 ዓ.ም. ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሸ ዞን ያሶ ወረዳ በተፈናቀሉ የአማራ ብሔር ተወላጆች ምክንያት የክልሉ መንግሥት፣ የፌደራል ሚኒስቴርና በድርጊቱ ተሳትፈዋል በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመሥረቱ ታወቀ፡፡

ለበርካታ ዓመታት ከኖሩበት አካባቢ ያለምንም ማስጠንቀቂያ 1,346 የሚሆኑ አባዎራዎችን ጨምሮ 3,240 ቤተሰቦቻቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡

በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ በወቅቱ ለምን እንዲፈናቀሉ እንደተደረገ፣ የተፈናቀሉትም ወደነበሩበት ቀዬ እንዲመለሱና ለደረሰባቸው ጉዳት ካሳ እንዲከፈላቸው፣ አፈናቃዮቹም ለሕግ እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ መጠየቁ አይዘነጋም፡፡ የአማራ ተወላጆችም የተፈናቀሉት ኪራይ ሰብሳቢዎች በሠሩት ስህተት መሆኑን በመጠቆም በሕግ እንደሚጠየቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በግልጽ መናገራቸውም እንዲሁ፡፡

ነገር ግን የክልሉ መንሥትም ሆነ ፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ለተፈናቃዮቹ ካሳ መስጠትም ሆነ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ባለማድረጋቸውና በተጠርጣሪዎቹ ላይ ዕርምጃ ባለመውሰዳቸው፣ ሰማያዊ ፓርቲ በታዋቂው የሕግ ምሁር ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም አማካይነት ያቀረበው ክስ ተቀባይነት በማግኘቱ፣ በክሱ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ የክልሉ መንግሥትና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ሚያዝያ 9 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስምንተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ቀርበው የተጠረጠሩበት ክስ እንደሚነበብላቸው መታወቁን ሪፖርተር ጠቅሷል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on April 16, 2014
  • By:
  • Last Modified: April 16, 2014 @ 2:41 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar