www.maledatimes.com የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ

By   /   April 16, 2014  /   Comments Off on የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 42 Second

ፍርድ ቤት ቀርበው ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል

የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ በሙስና  ተጠርጥረው ታሰሩ

የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡርን ላለፉት በርካታ ዓመታት በዋና ሥራ አስኪያጅነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ጥዑም ተኪዔ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከሚያዝያ 2 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታወቀ፡፡

በሥራ ምክንያት ወደ ድሬዳዋ መሄዳቸው የተገለጸው አቶ ጥዑም፣ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ሥር የዋሉት ባረፉበት ሆቴል መሆኑን የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ለአቶ ጥዑም በቁጥጥር ሥር መዋል ዋናው ምክንያት በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘው የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ስፖርተኞች (ሠራተኞች) ክበብ ጋር የተገናኘ ሳይሆን እንደማይቀር ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡ ላለፉት ዓመታት ክበቡን በኮንትራት ይዘውት የነበሩ ግለሰብ የኮንትራት ጊዜያቸው በሰኔ ወር 2006 ዓ.ም. የሚያበቃ ስለሆነ፣ ኮንትራት እንዲያራዝሙላቸው ዋና ሥራ አስኪያጁን ሲለማመጡ እንደነበር ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡

አቶ ጥዑም ያረፉበት ሆቴል እንዲፈተሽ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፀረ ሙስና መርማሪ ፖሊስ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ አውጥቶ ሲፈትሽ፣ ክበቡን በኮንትራት የያዙት ግለሰብ ለመርማሪ ፖሊሶች ያስመዘገቡት 2000 ብር በመገኘቱ፣ አቶ ጥዑም በቁጥጥር ሥር ሊውሉ መቻላቸውን አስረድተዋል፡፡

አቶ ጥዑም ሚያዝያ 5 ቀን 2,006 ዓ.ም. ድሬዳዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው  ፖሊስ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸው፣ በድጋሚ ሚያዝያ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. መቅረባቸው ታውቋል፡፡ ፖሊስ ምርምራ እንደሚቀረው ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት ተጨማሪ የ14 ቀናት ጊዜ ጠይቆ እንደተፈቀደለትና ለሚያዝያ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱም ታውቋል፡፡ አቶ ጥዑም የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና የሚከለክል በመሆኑ የዋስትና መብታቸው መታለፉም ተገልጿል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on April 16, 2014
  • By:
  • Last Modified: April 16, 2014 @ 2:44 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar