www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)

By   /   May 2, 2014  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 45 Second

Ethiopian People’s Congress for United Struggle (Shengo)
www.ethioshengo.org shengo.derbiaber@gmail.com

ግፈኛው ስርዓት እንዲያከትም፣ የጋራ ትግሉን አጠንክረን እንቀጥል
ሚያዝያ 23፣ 2006

May 01, 2014

ባለፉት ጥቂት ቀናት እንዳየነው፣ ገዢው ህወሓት/ኢህአዴግ የመብት ረገጣውንና ሌሎችም አስቃቂ ተግባሩን በከፍተኛ
ደረጃ በተለያዩ የሀገሪቱ ዜጎችና ተቋማት ላይ እየሰነዘረ ነው። ባለፉት ሁለት ሳምንታት የደረሰውን ብቻ እንኳ ብናይ ፦

• ትላንት ሚያዝያ 22 በአምቦ ከተማ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የህወሓት/ኢህአዴግ የጸጥታ ሀይሎች በከፈቱት ተኩስ
ቢያንስ ስድስት ተማሪዎች በግፍ እንደተገደሉ ተዘግቧል።
• ዞን ዘጠኝ በመባል የሚታወቀው ስብስብ አባላት የሆኑ ስድስት ወጣት ጋዜጠኞችና ጦማሪዎች ፤ መሰረታዊ
ሃሳብን የመግለጥ መብታቸውን በመጠቀማቸው ብቻ፣ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም አመጽ ሊያሰነሱ ሞክረዋል
በሚል የተለመደ አስልች ሰበብ ለእስራት ተዳርገዋል፤
• ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማደናቀፍ፣ የፓርቲውን አመርር አባላትና ደጋፊዎች በማሰር ከፍተኛ
መንገላታት ደርሶባቸዋል፤
ይህ ሁሉ ገዢው ህወሓት/ኢህአዴግ ምን ያህል ህዝብን እንደሚፈራና ባንጻሩ ደግሞ የህዝብ ቆራጥነትና ለመብቱ መከበር
የሚያደርገው ትግሉ እየጎለበተ መምጣቱን ነው የሚያሳየው።
የኢትዮጵያያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ (ሽንጎ)፣ አገዛዙ በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፋዊ እርምጃ በጥብቅ እያወገዘ፣
በእስር ላይ ያሉ የዞን ዘጠኝ አባላት እና ሌሎች ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ሰዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ በንጹሃን ዜጎች ላይ
ግድያ የፈጽሙ ባስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ይጠይቃል። ከአንድነት ፓርቲና ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ያለውን የትግል
አጋርነትም ይገልጻል።
ትግሉ ተጠናክሮ አስፈልጊውን ህዝባዊ ድል እንዲቀዳጅም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለነዚህና ሌሎች ታጋዮች በሁሉም መልክ
ድግፉን እንዲሰጥ ሸንጎ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል።
ልዩነቶችን አጥብበና በሀገር ጉዳይ ላይ አተኩረን ስንነቃነቅ እንኳንስ የህዝብ ድጋፍ የሌለው አምባገነን ይቅርና ማንም ሌላ
ሀይል ሊገታን እንደማይችል የማይታበል ነው። ይህ እንዲሆንም በእያንዳንዳችን በኩል በተግባር መንቀሳቀስን የግድ ይላል።

በተባበረ ህዝባዊ ትግል ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንመሰርታለን
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ

Tel: 44 7937600756 , +1 9168486790 E-mail : shengo.derbiaber@gmail.com

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on May 2, 2014
  • By:
  • Last Modified: May 2, 2014 @ 6:17 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar