www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ 30ኛ አመት የልደት ክብረ በአል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ” ያለፈውን እያወደስን ለመጭው እንዘጋጅ “ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ 30ኛ አመት የልደት ክብረ በአል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ” ያለፈውን እያወደስን ለመጭው እንዘጋጅ “

By   /   May 4, 2014  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ 30ኛ አመት የልደት ክብረ በአል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ” ያለፈውን እያወደስን ለመጭው እንዘጋጅ “

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 32 Second

ያለፈውን እያወደስን ለመጭው መዘጋጀት በሚለው አስደሳች መርህ ለ30 አመታት ጉዞውን ያቀናው የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አሶሴሽን ኦፍ ችካጎ በዛሬው እለት የሰላሳ አመት ልደቱን በደማቅ ሁኔታ አከበረ ። ያሳለፋቸውን ውጣ ውረዶችን እያነሳ ፣ባሳለፉት ዘመናት ግልጋሎት ሲሰጡ የነበሩትን ሁሉ እያመሰገነ ዛሬ ላይ ደረሰ እና ይሄው የእናንተ ጥረት የሰማይ ያህል እንድርቅ አድርጎኛል ሲል ብስራቱን ለማህበረሰቡ አበለጸገ ።በዛሬው እለት የሰላሳኛ አመቱን ክብረ በአል በሚያወድስበት በዚህ ታሪካዊ  ወቅት ላይ በሌላም በኩል የሚኒያፖሊስ ኢትዮጵያን ኮሙኒቲ የህንጻ ማሰሪያ የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም እንደነበረ እና የችካጎን ኮሙኒቲ ጥንካሬ መሰረት በማድረግ የህልውናችን መሳሪያ ነው ሲሉ እንደ አብነት እንደገለጹት ከስፍራው የነበረው ሪፖርተራችን ገልጾልናል ። የኮሙኒቲው 30ኛ አመት አከባበር ከእንኳን ደስ ያላችሁ የጀመረው እና የተለያዩ እንግዶች ፣የመንግስት ባለስልጣኖች እና ታላላቅ ባላሃብቶች የተገኙበት እንደነበር የማለዳ ታይምስ ሪፖርተር ገልጾአል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከተለያዩ የአሜሪካ ሴክተር መስሪያቤቶች እና የመንግስት ተቋማት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ለኮሙኒቲው ደብዳቤዎች ደርሶታል ከዕነዚህም መካከል ከችካጎ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ከንቲባ  ራሃም ኢማኑኤል የጻፉት ደብዳቤ በዋነኝነት ሲጠቀስ ሴናተር ሪቻርድ ደርቢን ፣ከኮንግረንስ ማህበር አባላት ጃን ሽኮዋስኪ፣ከሴናተር ሄዘር ኤ ስቴንስ ፣ከስቴት ሪፕረዘንታቲቭ ኬሊ ካሲድ ፣ከስቴት ኦፍ ኢልኖይ ኦፊስ ኦፍ ዘ ኮምፕትሮለር   ጁዲ ባር ቶፒንካ፣ከሲቲ ካውንስል አልደርማን ጆሴፍ ኤ ሞር ፣አልደርማን ሃሪ ኦስተማን ፣እና እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ዴቨሎፕመንት በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙት ጥቂቶቹ ናቸው ።በክብረ በአሉ ላይ የተለያዩ የኢትዮጵያ ባህላዊ እቃዎች በጨረታ ምዝገባ ተሸጠዋል ገቢው ለኮሙኒቲው ለሚያሰራው የወጣቶች መዝናኛ እና እንዲሁም ለሙዚየም ስራ የሚውል እንደሆነ ተጠቁሞአል ።2014-05-03 22.15.15 2014-05-03 22.22.59 2014-05-03 22.23.01 2014-05-03 23.02.35 2014-05-03 23.02.55 2014-05-03 23.03.25 2014-05-03 23.03.39 2014-05-03 23.04.05 2014-05-03 23.04.13 2014-05-03 23.04.22 2014-05-03 23.04.41 2014-05-03 23.04.50 2014-05-03 23.05.07 የዘሃበሻ እና የማለዳ ታይምስ አዘጋጆች እንኳን ለ30ኛ አመት ክብረ በአላችሁ በሰላም አደረሳችሁ እኛም በእናንተ ስራ ኮርተናል ሲሉ ደስታቸውን ገልጸዋል ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on May 4, 2014
  • By:
  • Last Modified: May 4, 2014 @ 12:21 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar