www.maledatimes.com በጎንደር ከተማና እና አካባቢዋ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የሰው ህይወት አለፈ፡፡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጎንደር ከተማና እና አካባቢዋ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የሰው ህይወት አለፈ፡፡

By   /   May 4, 2014  /   Comments Off on በጎንደር ከተማና እና አካባቢዋ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የሰው ህይወት አለፈ፡፡

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 33 Second

በአማራ ክልል ጎንድር ከተማ ውስጥ እና በመተማ እና የሱዳኗ ገላባት አካባቢዎች ላይ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የሰው ህይወት ማለፉን በአካባቢው የሚገኙ የወሬ ምንጮች ለድሬቲዩብ ገልጸዋል፡፡

የመጀመሪያው ግጭት የተነሳው መተማ አካባቢ መሆኑን የገለጹልን ምንጮቹ ‹‹ አንድ የባጃጅ ሹፌር ከሱዳኗ የገለባት ከተማ ኮንትሮባንድ እቃዎችን ጭኖ ለመግባት በሚሞክርበት ወቅት ከፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲቆም ጥያቄ ቢቀርብለትም ረግጦ ለማለፍ በሚያደርገው ጥረት በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት መሞቱን ተከትሎ የአካባቢው ማህበረሰብ ከፖሊስ ጋር ግጭት ፈጥሮ ከፖሊስ እና ከአካባቢው ነዋሪዎች የሰው ህይወት አልፏል፡፡››

ከኢትዮጵያ ድንበር ከተማ መተማ ወደ ሱዳኗ ገለባት ከተማ ማንኛውም ሱዳናዊ ሆነ ኢትዮጵያዊ ለገበያም ይሁን ለሌሎች ነገሮች መግባት እና መውጣት የሚፈቀድለት መሆኑን ያስረዱት ምንጮቹ አካባባው የኮንትሮባንድ ተግባርን እንደመተዳደሪያ የሚጠቀሙበት ሰዎች ያሉበት እና የጦር ማሳሪያ የታጠቁ ግለሰቦች የሚበዙበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ሚያዝያ 23 ቀን 2006 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ልዩ ቦታው ‹‹ገንፎ ቁጭ›› በሚባለው አካባቢ በተነሳ ያለመግባባት ቢያንስ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉንም ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡ የወሬ ምንጮቹ ከዓመታት በፊት የክልሉ መንግስት አካባቢውን ለልማት በመፈለጉ እና የአካባቢውን ገበሬዎች ካሳ ከፍሎ እንዲለቁ ስምምነት ከተደረሰ በኋላ ልማቱ እስኪጀመር በእርሻ ስራቸው እንዲቀጥሉ መደገሩን የሚያስታውሱ ሲሆን ገበሬዎች ግን ቦታውን በመሸንሸን ለቤት ሰሪዎች በርካሽ ዋጋ በመሸጥ ገዢዎቹ ቦታው ይጸድቅልናል በሚል ተስፋ መኖሪያ ቤት እንደሰሩበት አብራርተዋል፡፡

ባለፈው ሃሙስ ሚያዝያ 23 ቀን 2006 ዓ.ም የመንግስት አካላት አካባቢውን ለማፍረስ የሚፈርሱትን አካባቢዎች በቀለም ምልክት እያደረጉበት ባለበት ሰዓት ነው ከነዋሪዎቹ ጋር ግጭት የፈጠሩት፡፡

ግጭቱ የተጀመረው ረፋድ አካባቢ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ከምሽ 12 ሰዓት ላይ በክልሉ ልዩ ሃይል እና በፌደራል ፖሊስ አባላት ርብርብ ግጭቱ ቢቆምም ምንጮቻችን እንዳሉት ከሆነ የ9 ህጻትን እና የፖሊስ አባላትን ጨምሮ የ9 ሰዎች ህይወት አልፏ፡፡

በጎንደር ከተማ በተመሳሳይ ህግን ሳይከተሉ የተገነቡ ቤቶች 7 ሺህ እንደሚደርስ የተነገረ ሲሆን ‹‹አይራ›› አካባቢ እና ‹‹ህዳር 11 ትምህርት ቤት›› አካባቢዎች ላይ በርካታ ተመሳሳይ መኖሪያ ቤቶች መገንባታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

በአካባቢው በነፍስ ወከፍ ደረጃ የጦር መሳሪያዎች የሚይዙ ግለሰቦች በርካታ መሆናቸውም ተጠቁሟል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on May 4, 2014
  • By:
  • Last Modified: May 4, 2014 @ 12:12 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar