www.maledatimes.com የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ

By   /   May 4, 2014  /   Comments Off on የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 33 Second
ዘረኛው እና አምባገነኑ የትግራይ ነጻ አውጪ ስርኣት በአገራችን ኢትዮጵያ እያደረሰ ያለዉን በደል ለመቃዎም የተጠራ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግቶን ዲሲ

ያላግባብ የመሬት መነጠቅን በመቃዎም ሰላማዊ ሰልፍ ለማረግ የወጡ ንጹሃን የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያንን በጭካኔ በጥይት የተጨፈጨፉትን ፣ መጠለያቸው
ያላግባብ ፈርሶ ልጆቻቸዉን የሚያሳድሩበት ጎጆ በማጣታቸው አቤት ለማለት የወጡ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የግፍ ግድያ እርምጃን ፣ ሃሳባቸዉን በነጻ ለመግለጽ
በሞከሩ ጋዜጠኞች እና የየዞን ፱ ድረ ገጽ ጦማሪዎች ለእስር መዳረግ ፣ ህገመንግስቱ የሚፈቅደውን መብታቸው ተጠቅመው ህግና ደንብን ተከትለው ፍጹም ሰላማዊ የሆነ
የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ በተንቀሳቀሱ የሰማያዉ እና የአንድነት ፓርቲ አባላት ላይ የደረሰዉን የእስር እና የድብደባ ወንጀል ለመቃዎም የተጠራ ሰልፍ ነዉ። 

ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ ስርአት በንጹህ ዜጎቻችን ላይ እያደረሰ ያለዉን ግድያ ፣ እስርራትና ያገራችን ኢትዮጵያን ህልዉና አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶች 
ለመቃዎም እንዲሁም ለአገር አንድነት ፣ ለዲሞክራሲ ፣ ለዜጎች መሰረታዊ መብት እና ለመልካም አስተዳደር ሲሉ አምባ ገነኑን ስርእት በቆራጥነት ተጋፍጠው ዋጋ እየከፈሉ
ያሉና ደብዛቸው ጠፍቶ ለቀሩት ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችንን እና ፓርቲዎች ለሚያረጉት ጥረት ከጎናቸው መቆማችንን ለመግለጽ የተዘጋጀ ሰላማዊ ሰልፍ ነዉ።

በተጨማሪም ይህ የምንኖርበት የአሜሪካ መንግስት ለዚህ ሰላማዊ ዘጎችን ለሚጨፈጭፍ አምባገነን ስርኣት የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያቆም እና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ
ለነጻነትና ዲሞክራሲ የሚያደርገዉን ትገል አጋር አንዲሆን እንደ ግብር ከፋይ ነዋሪነታችን እንደዘወትሩ ሳንታክት የምናሳስብበት ነው። 

ሰሞኑን ኢትዮጵያን ጎብኝተው ያላግባብ የታሰሩ ጋዜጠኞች ጉዳይ እና የፖለቲካ ስርእቱ መጥበብ ያሳሰባቸው መሆኑን በይፋ የገለጹት የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ባለስልጣን
አክብሮታችንን አሳይተን ባንጻሩ ቃላቸውን በተግባር እንዲተረጉሙ ጉብኝታቸዉን አጠናቀው ሲመለሱ በጽህፈት ቤታቸ ፊት ለፊት ተገኝተን የምንጠይቅበት ጭምር ነው።

እነዚህ እና ሌሎችም አንገብጋቢ ያገራችን ጉዳዮች ያገባናል ወይም ይመለከተናል የምንል በሙሉ ዘር እና ሃይማኖት ሳንቆጥር በዚህ ሰልፍ ላይ ተገኝተን የዜግነት እና
የሰብአዊ ህሊና ግደታችንን እንድንዎጣ የሰልፉ አዘጋጆች በትህትና ጥሪ እናቀርባለን።

ቀን፥ እረቡ ሚያዚያ ፪፱ (Wed May 7, 2014)

ሰአት፥ ከጠሗቱ ፱ ኤ. ኤም (9:00AM)

ቦታ፥ ከአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ጽ/ቤት ፊት
ለፊት ዋሺንግቶን ዲሲ 

(US State Department, 22nd & C st, NW, Washington DC

አዘጋጅ፥ በዋሺንግቶን ዲሲ የጋራ ግብረ
ሃይል (Washington DC Joint Task Force)

ለተጨማሪ መረጃ፥ dcjointtaskforce@gmail.com
<mailto:dcjointtaskforce@gmail.com>
or (202) 556-3078

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on May 4, 2014
  • By:
  • Last Modified: May 4, 2014 @ 1:31 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar