www.maledatimes.com ኢህአዴግ አጣብቂኝ ውስጥ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢህአዴግ አጣብቂኝ ውስጥ

By   /   September 6, 2012  /   Comments Off on ኢህአዴግ አጣብቂኝ ውስጥ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 10 Second

 

የቅዳሜ ማስታወሻ

         የኢህአዴግ ስራአስፈፃሚ ማክሰኞ፣ መሰከረም 4፣ 2012 ተሰብስቦ ውሎአል። ስብሰባውን ባለማጠናቀቁም ዛሬ መስከረም 5 ቀጥሎ እንደሚውል መረጃዎች ይጠቁማሉ። የስራአስፈፃሚው አባላት በጥቅሉ 36 ሲሆኑ፣ በመለስ መሞት ምክንያት ተሰብሳቢዎቹ 35 ናቸው።
ህወሃትን ወክለው በስብሰባው ላይ የተገኙት 8 ሰዎች፣ ፀጋይ በርሄ፣ አባይ ወልዱ፣ አባዲ ዘሙ፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ደብረፅዮን፣ በየነ እና (አዜብ መስፍን?) ሲሆኑ፣ ነባሮቹ እና አንጋፋዎቹ የህወሃት አመራር አባላት ከስብሰባው ውጭ በመሆናቸው ኢህአዴግ በብአዴን እጅ ላይ መውደቁ ይነገራል። ከብአዴን በረከት ስምኦን እና አዲሱ ሲገኙ ከኦሮሚያና ከደቡብ አስቴር ማሞ (ግርማ ብሩ?) እና ሬድዋን ሁሴን ተገኝተዋል። 8ቱ የህወሃት አባላት መለስን የሚተካ አንድ ሰው ወደ ስብሰባው ለመጨመር ጠይቀው የአመራሩ አባላት አሰራሩን በመጥቀስ ሳይፈቅዱላቸው ቀርተዋል።
ትናንት በዋለው ስብሰባ ላይ ሙሉ መግባባት ላይ ሊደርሱ ባለመቻላቸው፣ አጀንዳቸውን ለማሳደር ተገደዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የስራአስፈፃሚው ስብሰባ ላይ መሳተፍ ያልቻሉት አንጋፋዎቹ የህወሃት አመራር አባላት ድርድር ጠይቀዋል። እነዚህም፣ ስዩም መስፍን፣ አርከበ ኡቅባይ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ፣ ስብሃት ነጋ እና ሳሞራ የኑስ ናቸው።
አከራካሪው አጀንዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የምክትሉ ሹመት ጉዳይ ሲሆኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታም እንዲሁ እያወዛገበ ይገኛል።

(ኢህአዴግ ድረገፅ ግን እውነታውን በመሸፋፈን የሚከተለውን ዘግቦአል)
“….የባለ ራዕዩና ታላቁ መሪ የጓድ መለስ ዜናዊን ድንገተኛ ህልፈት ተከትሎየተጓደለው አመራር በሚሰየምበት አቅጣጫ ዙሪያ የመከረ ሲሆን የአመራር ምደባ ጉዳይለጋራ ዓላማ በሚደረግ ትግል ውስጥ አንድን ጓድ ይበልጥ መስዋዕት ይከፍል ዘንድከመመደብ ያለፈ ትርጉም የሌለው ቀላል ጉዳይ መሆኑንና ዋናው ስራም ሁሉምበየተሰማራበት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት መሆኑን አውስቷል፡፡ በመሆኑም ዋናውጉዳይ የሆነው ለህዝቡ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት በቂ ምላሽ መስጠት በሚቻልበት አቅጣጫዝግጅት እየተደረገ የግንባሩን ሊቀመንበርና ም/ሊቀ መንበር የመሰየም ጉዳይ የግንባሩ ምክርቤት ስልጣን በመሆኑ በመጪው መስከረም የመጀመሪያ ሳምንት በሚካሄደው የምክር ቤቱስብሰባ እንዲፈፀም ወስኗል፡፡)
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 6, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 6, 2012 @ 12:23 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar