www.maledatimes.com በኢቢኤስ ስለቀረቡ የኦሮምኛ ድምፃውያን ገረመው ሁንዴ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በኢቢኤስ ስለቀረቡ የኦሮምኛ ድምፃውያን ገረመው ሁንዴ

By   /   May 7, 2014  /   Comments Off on በኢቢኤስ ስለቀረቡ የኦሮምኛ ድምፃውያን ገረመው ሁንዴ

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 15 Second

 

በአንድ አስገዳጅ ሁኔታ ውጪ ከሰዎች ጋር አምሽቼ አሁን ቤት ስገባ ቤተሰብ ኢቢኤስ የሚባለውን ቲቪ ሲመለከቱ ደረስኩ፡፡ እኔም አየሁ፡፤ ትግስት የምትባል ጋዜጠኛ አራት የኦሮሞ ዘፋኞችን ታወያይ ነበር፡፡ አንዱ የምወደው ጃምቦ ጆቴ ነው፡፡ ሌሎቹንም በጣም እወዳቸዋለሁ፡፡ ጎነዝ ድምፃውያን ናቸው፡፡ ውይይቱ ሊያልቅ ሲል ነው የደረስኩት፡፡ ደስ የሚል ውይይት እንደነበር ከአጨራረሱ ያስታውቃል – የመጨረሻው መጨረሻ አላምር ብሎ ብዕሬን አስነሳኝ እንጂ፡፡ የኛ ሀገር ነገር አንዳንድ ጅምሮች ያምሩና ጥቂትም ፎቀቅ ሳይሉ አስጠሊነታቸው ይለጥቃል፤ እንዲህ እያልን አለን፡፡ የወደፊቱን አንድዬ ካላበጀልን እንደእስካሁኑስ ከሆነ መዳረሻችንን ለመተንበይ አስቸጋሪ ነው፡፡ ጠላት በተለመው ቦይ እየገባን የምንተላለቅና በጥላቻ ወጥመድ የምንጠላለፍ፣ በዘር የችግኝ መደብ እየተቧደንን የጋራ ጠላት በየተራ ሲመትረን እያየን “ይሄ የኔ ጉዳይ አይደለም!” በሚል የምንፈራረጅ አስቂኝ ፍጡራን ሆነናል፡፡ “የኦሮሞ ጉዳይ፣ የአማራ ጉዳይ፣ የትግሬ ጉዳይ፣…” እየተባለ ሁሉም ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ መሆን ሲገባው እንደውጭ ጉዳይ እየተቆጠረ መጥቶ እኛን ሽማግሎቹን በሣቅ እያፈነዳን ነው፡፡ የገመቹ አብርሃም ጉዳይ ሐጎስ ስንሻውን ወይም አብዲሣ በለጠን አያገባውም ሲባል በሣቅ ያልሞትን መቼ ልንሞት ነው አይ ኢትዮጵያ! ብለሽ ብለሽ እንደዚህ ያሉ ማፈሪያዎች ይፈጠሩብሽ? ኧረ መቼ ነው ነፍስ የምታውቂ? መቼስ ይሆን ሁለመናሽ ላይ ተገጥግጦብሽ ያለ ዕድፍ የሚጠራ?

ውይይቲ ሲጠናቀቅ ጋዜጠኛዋ “በኅብረት የምትዘፍኑት ነገር አለ ይሆን” ብላ ስትጠይቅ ወዲያዉኑ ቀድመው የተማከሩ ይመስል – መማከራቸውም በደንብ ያስታውቃል – አንድ ዘፈን ዘፈኑ፡፡ እዚህ ላይ እነዚህ ዘፋኞች አማርኛን ሙልጭ አድርገው ነው የሚናገሩት፡፡ እንዲያውም አማሮችም ይመስላሉ፡፡ አማርኛን የት እንደለመዱት ገረመኝ፡፡ ኦሮሞ ሆነው አማርኛን እንደዚህ መናገራቸው እኔን ብቻ ሳይሆን ኦባማን ሳይገርመው የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ለኔ እነዚህ አራት ሰዎች የተበለሻሹብኝ በቀጣዩ ምክንያት ነው፡፡

ሲዘፍኑ ኦሮምኛን የማይሰማ አማራ ወይም “ኢትዮጵያዊ” ያለ መስሎኣቸው ይመስለኛል – ቃለ መጠይቃቸውን ‹እንደዋዛ› ቁልጭ ባለ ማለትም በጠራ አማርኛ ከሰጡ በኋላ የመጨረሻ መልእክታቸውን በዜማ የሰጡት ግን ይቅርታችሁንና ቅርን ቅርን አለኝ – ይቅርታ ባማርኛየ፡፡ ወያኔ ወያኔ ይላል – ነገ ያፍሩበታል፡፡ ወይም አሁን እኔ በምለው ነገ ራሴ አፍርበታለሁ፡፡ …

በኅብረት የዘፈኑት ዘፈን መልእክት – “ኦሮሞ አንድ ነህ፡፡ ክርስቲያን እስላም ሳይባል ኦሮሞ አንድ ነህ – አንድም ሁን፡፡ ኦሮሞ በሃይማኖትና በጎሣ ሳትከፋፈል (ከሀበሻ ቅኝ ግዛት ነፃ ለመውጣት) በርትተህ ታገል…” በጣም ያሳዝናል፡፡

እነዚህ ድምጻዊያን ኢትዮጵያ አሳድጋ ለቁም ነገር አድርሳቸዋለች፡፡ አሁን ግን የእናታቸው ጠላቶች ፈጥረው በሰጧቸው ‹ኦሮምያ› የሚባል/የምትባል አዲስ ሀገር ፍቅር ተነድፈው ኢትዮጵያንም ሌሎች ጭቁን ኢትዮጵያንም ለወረት ፍቅር ለውጠው የበሉበትን ወጪት ሰበሩ – ሰብረው ላይሰብሩ፡፡ አርስት እንደዚህ አይወርደም፡፡ አርቲስትና ካህን ሀገርና ቋንቋ የላቸውም፡፡ ሁሉም ሀገር ሀገራቸው፣ ሁሉም ሕዝብ ሕዝባቸው፣ ሁሉም ቋንቋ ቋንቋቸው ሊሆን ይገባል፡፡

አንዲት ቃል እስከዚች አናገረችኝ፡፡ “አማራ አንድ ሁን፤ እስላምም ክርስቲያንም የሆንክ አማራ አንድ ሁን” የሚል የአማራ ዘፋኝ ቢገጥመኝ ምን እንደምል አውቃለሁ ወይም – እኔ እንጃ – እንዲህ ያለ ቅሌት ይኖራል ብዬ ስለማልገምት የምለውን ከአሁኑ አላውቅም ይሆናል፡፡ ብቻ እያዘንኩ መጣጥፌን ዘጋሁ፡፡ ግን ጅላጅሎችን በተቻለን መጠን እንምከር – ሁሉም ነገር ከልኩ ባይዘልም አጥብቀን እንምከራቸው፤ በዘርና በሃይማኖት፣ በጎሣና በነገድ የሥነ ልቦና á‹°á‹Œ የበከለው ጠባብ ኩሬ ውስጥ ገብቶ መንደባለል ከአንድ ዘመናዊ የኪነ ጥበብ ሰው አይጠበቅም – የኢትዮጵያን ሕዝብ ባህርይ ካለማወቅ የሚመነጭ ድንቁርና ይመስለኛል፡፡ በነዚህ ቂሎች አዝኛለሁ፡፡ አለማወቅ መጥፎ ነው፡፡ ለነገሩ ማወቅም መጥፎ ነው፡፡ ያላወቁትን እንዳወቁት ቆጥሮ መጃጃል ደግሞ ከመጥፎዎች ሁሉ የበለጠ መጥፎ ነው፡፡ በሸረኞች ወሬና ከንቱ ስብከት በመነዳት አቅልን ማጣት ስህተት ነው፡፡ በተለይ በተለይ ጨለማን እንደማይነጋ በመቁጠር ለከርስ ብቻ ማደር ከሁሉ የከፋ መጥፎ ነው፡፤ ሲነጋ ለማፈር አሁን በወጀብ ንፋስ ከነፈሰው ሁሉ ጋር አብሮ መንገላወድ በነገው ዕለት የራስን ብቻ ሳይሆን የትውልድን አንገትያስደፋል፡፡ ምን አለፋችሁ አንዳንድ ወገኖች በአሁኑ ወቅት ሲያደርጉት የምናስተውለው ነገር በእጅጉ አሣፋሪ ነው፤ ሌላው ሁሉ ይቅርና ወያዎች ራሳቸው አምቦ ውስጥ ሰሞኑን የገደሉትን ወይ ያስገደሉትን ሕጻን ልጅ ሬሣውን ፈልጋ ባገኘችው እህቱ ሲያሳብቡና እርሷን ሲያስሯት ምን ሊባል ይችላል? አያድርስ ነው፡፡ እስኪ የልጆቻችንንም ነፍስ ይማር፡፡ ሊነጋ ሲል ጨለማው በረታ እኮ! ወይ ጊዜ! ጊዜ ለካንስ እንደዚህ ወጭማዳ ኖሯላና!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on May 7, 2014
  • By:
  • Last Modified: May 7, 2014 @ 12:59 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar