www.maledatimes.com አስገራሚው የመለስ ዘመዶች (ኤርትራውያን) መልእክት (ትርጉም ኢየሩሳሌም አርአያ ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አስገራሚው የመለስ ዘመዶች (ኤርትራውያን) መልእክት (ትርጉም ኢየሩሳሌም አርአያ )

By   /   September 7, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 30 Second

              condolence-from-family-of-alemash-gebreluel-eritrea የትግሪኛውን ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል                                     

     

የትግሪኛውን ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል

የሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ ስጋ ዘመድ የሆኑ ኤርትራውያን የጋራ “ሃዘን መግለጫ “በአይጋ ፎረም በኩል አስተላልፈዋል።

“የምናፈቅረው ወንድማችን እና ልጃችን “ሲሉ የገለጿቸውን መለስ ዜናዊ “ቅዱስ” በማለትም  እነዚሁ ኤርትራውያን አሞኳሽተዋቸዋል ።እነዚህ ወገኖች መለስ ከኢትዮጵያ አልፈው ለአፍሪካ “ሰሩ” ያሉትን አሳፋሪ ትንተና ለመስጠት ከመከጀላቸው ባሻገር ኢትዮጵያውያን የመለስን መንገድ መከተል አለባችሁ ሲሉ ሊያሳስቡ ሞክረዋል። ይህንን መግለጫ ያወጡት የመለስ   ወላጅ እናት የሟቿ ወይዘሮ አለማሽ ገብረልኡል ቤተሰቦች ናቸው ።የሚገርመው የመለስ አያቶች በእናቱም በአባቱም ደጃዝማቾች ሲሆኑ የባለቤቱ አዜብ መስፍን አያት እንዲሁ ደጃዝማች ናቸው ።መለስ ብዙ ጊዜ ፊውዳሊዝምን ሲቃወሙ ይደመጡ እንጂ በእርግጥም የተጠናወታቸው እና እስከ ህልፈተ ሞታቸው ያራምዱት የነበረው መስመር የፊውዳል ስርአት ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው ።

አስገራሚውን “መግለጫ “እንደሚከተለው ተተርጉሞአል።

                                                            “የሃዘን ማፅናኛ መግለጫ “

“ በኤርትራ ምድር እና በመላው አለም የምንገኝ የደጃዝማች ገብረልኡል ተስፋማርያም  እና የአቶ ካህሱ መላ ቤተሰቦች የሆንን፤

በሞት በተለየን በምናፈቅረው፣ልጃችን እና ወንድማችን፣የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ የተሰማን መሪር ሃዘን እየገለጽን ፤ለዘመዶቹ ለቤተሰቡ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጽናቱን ይስጠን እንላለን።

አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ እና አፍሪካ ታሪክ ርሃብን ከሰፊው ህዝብ ለመንቀል ፣የታመመው እንዲፈወስ ፣መሃይሙ እንዲማር፣መብቱ የተገሰሰው ፍትህ እና ነጻነት እንዲከበርለት እና እንዲረጋገጥለት ፣ለአንድ ቀን እና ሰአት ሳያርፍ እና እፎይ ሳይል ፣ተወዳዳሪ የሌለው ዘላለማዊ የታሪክ ሃውልት ማኖሩ ፣ለህዝቡ እና ለቤተሰቡ የማይረሳ የድል ችቦ ፣የማይናድ ቅርስ ፣የማይጠፋ መብራት ፣ተጠብቆ የሚኖር ዘላለማዊ ክብር ፣. . . . ወዘተ ትቶ በማለፉ ፣የተሰማንን ትልቅ ኩራት እየገለጽን ፤በተለይ ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ ህዝብ በተለይም ደግሞ ለመላው ቤተሰቡ የጀመረውን ስራ ሳይጨርስ ፣ገና በ57 አመት እድሜው ማለፉ ሃዘናችንን ጥልቅ መሪር እና በጣም ከባድ ሸክም አድርጎታል።

አቶ መለስ ዜናዊ እድሜውን ሙሉ ሲያከናውነው የቆየው ፣መልካም እና የተቀደሰ ተግባራት ባይኖር ያለምንም ማጋነን እና አድሎ የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት አሁን ላለበት ደረጃ ሊበቃ እንደማይችል በማመን ፣እርሱ የጀመረው ወደር የሌለው የአገር እና ህዝብ ግንባታ አጠናክረው እንደሚገፉበት እና እንደሚያጎለብቱት ያለንን እምነት እና ተስፋ በዚህ አጋጣሚ እንገልጻለን ።ለአቶ መለስ ደግሞ ያንን ሁሉ የህዝብ እና ቤተሰቡ ጸሎት እና መሪር ሃዘን ፈጣሪ አምላክ ሰምቶለት በመንግስተ ሰማያት ያኑረው ።

             ከወይዘሮ አለማሽ ገብረሉልኡል ቤተሰቦች

            

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 7, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 7, 2012 @ 12:33 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With: ,

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “አስገራሚው የመለስ ዘመዶች (ኤርትራውያን) መልእክት (ትርጉም ኢየሩሳሌም አርአያ )

  1. Thank you God he’s gone for his stupid eritrean relatives just to let you know we most of are happy is gone. I wish he was never been a part of Ethiopia, we are actually embarased our country name is associated with him. We never as him to stay why didn’t he move to eritrea. Of course he has to make sure his mosquito family has something to eat.

    Don’t you ever mention our country we don’t want to have anything to do with you.
    Go to hell with the butcher, murderer of yours that’s all you people know. Worry about your own physco guy don’t speak about our country it’s none of your business.

    we are not pretenders like you we tell the truth.
    you’re arab when you meet arabs, you’re muslim when you meet muslims, you’re christians …what’re you?

    God bless Ethiopia and it’s people

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar