www.maledatimes.com አባይ ፀሃዬ የህወሃትን የሊቀመንበርነት ቦታ እንዲይዙ አሻጥር እየተሰራ ነው ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አባይ ፀሃዬ የህወሃትን የሊቀመንበርነት ቦታ እንዲይዙ አሻጥር እየተሰራ ነው ።

By   /   September 9, 2012  /   Comments Off on አባይ ፀሃዬ የህወሃትን የሊቀመንበርነት ቦታ እንዲይዙ አሻጥር እየተሰራ ነው ።

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 10 Second

የህወሃት ክፍፍል እየተጠናከረ በመጣበት በአሁኑ ሰአት የቀድሞውን ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከፍተኛውን  ቦታ ለመቆናጠጥ የሚያስችላቸውን  የእዝ ቦታዎች ለመያዝ የህወሃት የበላይ አካሎች አሁንም በከፍተኛ ትግል ላይ ሲሆኑ ፣የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በጠ/ይ ሚንስትርነታቸው የመቀመጥ ጉዳይ በሰፊው አስጊ ነው ።በአሁን ሰአት ከፍተኛ አሻጥር እየተሰራ ያለው አቶ አባይ ጸሃዬን በማምጣት የህወሃት ሊቀመንበር ለማድረግ ዝግጅታቸውን እያጠናቀቁ ሲሆን ፣ከፊሎች ደግሞ ይህ እንዳይሆን ትግላቸውን አጠናክረዋል።

በተለይም በአሁን ሰአት የሹም ሽር እየተደረገ ያለው በትግራይ ተወላጆች እና በኤርትራ ተወላጆች ላይ የበላይ ተቆጣጣሪነት ሲሆን ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ስጋት ላይ እንወድቃለን ብሎ ለእራሱ ሲያለቅስ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ሳይደርቅ የሚፈጸም ይመስላል ፣ይህንንም ስንል እርስ በራሳቸው ግጭታቸውን አባብሰውት ወደ ግድያ ያመራሉ ተብሎ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ሲሆኑ አራት የህወሃት አባሎች ከሌሎች አምስት  የጦር አዛዦች ጋር ለሚቀጥለው መስከረም አምስት በዚህ ጉዳይ ላይ ለመወያየት ሚስጥራዊ ስብሰባ ለማካሄድ  ዝግጅታቸውን ማጠናከራቸውን ከውስጣዊ ምንጮች ያገኘነው ዘገባ ሲያመለክት አምስቱም የጦር አዛዦች በተለያዩ የሜካናይዝድ ክፍለጦር በአዛዥነት የሚያገለግሉ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ በተጠንቀቅ ትእዛዛቸውን ለመፈጸም ያመቻቸው ዘንድ የሚረዳ ስልት የህወሃት አባሎች ሰራዊቱን ከአጠገባቸው ለማቆም ትግል ላይ ናቸው።

በተለይም ከእነአቦይ ሰብሃት በኩል ለመጣው ውጥረት እና እንዲሁም በእነ ጀነራል ሳሞራ በኩል ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የስልጣን ክፍፍል ከእነ አቶ በረከት እና አዜብ መስፍን በኩል ላለው ልዩ ፍራቻ የሃገሪቱን ውጥረት አሁንም ይበልጥ ያባብሰዋል።በተለይም ከህወሃት አባላት ውጭ ሌላ ሰው ቁንጮ ሆኖ መቀመጥ የለበትም የሚሉት የእነ አዜብ መስፍን እና የአክራሪው ስብሃት ነጋ ቡድን ሁለቱም ፍጥጫቸው በተለያየ መልኩ ሊሄድ ይችላል ነገር ግን ግጭቱ ወደ አንድ አቅጣጫ ያመራቸዋል ሲሉ ፤የግጭቱ መንስዔ ግን የቦታ ይገባኛል እና የሚፈልጉትን ሰው በሚፈልጉት ቦታ የማስቀመጥ ጉዳይ መሆኑ ፣ይበልጥ አሳሳቢ እና ግራ የሚያጋባቸው ሆኖአል ።

በሌላ በኩል ደግሞ የአቶ በረከት የኤርትራ ተወላጆችን ወደ ስልጣን ማምጣት እና እሳቸው በሚያሽከረክሩት አዙሪት ውስጥ ለመጣድ የሚያደርጉት ጥረት ስኬቱ ጎልቶ የሚታይ ባለመሆኑ በኦህዴድ እና ብአዴን ውስጥ ላሉት አመራሮች ፍራቻን ቢጭርባቸውም እስካሁን ድጋፋቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል ፣ሆኖም ግን የኤርትራ ተወላጆች የከበቧት የስልጣን ቦታ ለኤርትርያን ተወላጆች እና እንዲሁም አቶኦ በረከት የበላይ ሆኖ እንዲመራ የሚፈልጉ እንደሌሉ በሁሉም ክልል መንግስታቶች ፍላጎት እንደሌለ እያሳዩ ይገኛሉ ፣ሆኖም ግን ውስጣዊ ፍራቻቸው አይሎ ከወጣ ግጭቱን ሊያሰፋው ይችላል ፣ለዚያም ይመስላል አቶ በረከት ስምኦን  በቀድሞው ጠ/ሚንስትር የተተኩትን ጠ/ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ቃለ መሃላቸውን ፈጽመው ስራቸውን እንዳይጀምሩ አድርገው ያቆዩአቸው ፡ይርፍላጎታቸው ስኬት ካልተሟላ እንቅልፍ አይተኙም የሚለው የማለዳ ታይምስ ሚስጥራዊ መረጃ ምንጭ ።  የጤና ሚንስትር የሆኑትን ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በጠቅላይ ሚንስትርነት ተሾመዋል  የሚለው ጭምጭምታ የውሸት ሲሆን በአሁን ሰአት ግን ግብግቡን እሳቸውም የቦታው ሽሚያ ላይ ተያይዘውታል ሲል ዘግቦአል። for maledatimes report wondwosen from addis ababa

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 9, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 9, 2012 @ 6:44 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar