www.maledatimes.com ሰሚ ያጣ ጩክት ከሱዳን /ካርቱም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሰሚ ያጣ ጩክት ከሱዳን /ካርቱም

By   /   May 15, 2014  /   Comments Off on ሰሚ ያጣ ጩክት ከሱዳን /ካርቱም

    Print       Email
0 0
Read Time:15 Minute, 20 Second

በ አባት አያቶቻችን ክቡር ደም ተከብራ የኖረችው ኢትዩጽያ አሁን በኛ ዘመን ልጆቾ  ለደረሰባት ውርደት ዝቅጠት ሰደትን እንደመፍትሄ አድርገን መውሰድ ከመጀመራችን በፊት በአለም አቀፍ ደረጃ ስደተኛን በማስተናግድ ቀዳመዊ ነበረች ለዚህም እስራኤሎቾን፤ አረቦችን፤ አርመኖችና ግሪኮች ምስክር ቢሆኑንም በዋናነት ጝን የታሪኮ ቁንጮ ሆኖ የተመዘገበው ነብዩ መሀመድ እምነታቸውን ለማስፋፋት ችግር በገጠማቸው ግዜ ተከታዮቻቸውንና ቤተሰባቸውን ወደ ሀበሻ የሰላም ምድር፤ እምነቶች በ እኩልነት የሚስተዳደሩባት  ፍርዱ ትክክል የሆነ መሪ ያለባት ሀገር እንዲሄዱ ቤተሰቦቻቸውን  ሸንተው ተከታዮቻቸውን በክብር ተቀብላ ጥላ ከላላ፤ የመከራ ግዜ መጠጊያ ሆና የኖረች በገናና ታሪኮ እንደ ሰለሞን ጌጥ ጥበብ አለም  ያደነቃት ያካበራት የምንኮራባት ሀገራችን  ኢትዩጽያ  ናት;; እነሆ የነዚያ ደጋግና ቆራጥ ልጅ  ልጆቾ እስልምና  እምነት ተከታይ በሆነቸው ጎረቤተ ሀገር ሱዳን በስደት ተጠለልን በምንኖርበት ምድር ግፍ  እየተፈፀምብን ይገኛል ;;  

በ እርግጥ ሱዳኖች ለወያኔ ታላቅ ባለውለታ እንደመሆናቸው መጠን አይናችን እያየ የዮሀንስ ከተማ መታማ ና በበርካታ በክርሰ ምድሮ  የደለበ  ማእድናት ና ድንግል መሬት  ባላቤት ሆነዋል በዚህም አላበቃም ዛሬ ሀገራችን በ እንቨስትመንት ስም  ከቻይና ቀጥሎ በሁለተኛነት ኢትዮጽያን የተቀራመቶት ከቅጥረኛው ወያኔ ባለስጣናት ጋር  በ መሰሪ ተግባራቸው በመመሳጠር በሱዳን ከበርቴዋች ስም  በርካታ እንቨስትመንት ባለቤት ሆነዋል በዚህ ተግባር አዜብ ከሱዳኖች ከበርቴ ጋር በስውር ሸርክና እንዳላት ለዚህ አንዱ ማሳያ ሆነ እንጅ ሁሉም ቅጥረኛው ዘራፊ የወያኔ ባለስልጣናት እንዳሉበት አሳምረን  አናውቃለን ፤ ዛሬ ከ ከሁለት መቶ ሀምሳ በላይ ሱዳናዊያን ከበርቴዎች በግብርና፤ በከፍተኛ የመንገድስራ ኮንስትራክሸን ባለቤት ና ወደ አርብ ሀገራት በቀን አስከ አምስ ሸህ የበግና የፍየል ስጋ በመላክ የተሰማሩ  የናጠጡ ከበርቴዎች ሆነዋል እኛ ግን እዚህ ሰርተን ጥረን ግረን በምንኖር ስደተኞች ከሌሎች ዜጎች በተለየ በወያኔ አቀነባባሪነት ቁም ስቅላችን እናያለን;;

ሱዳን ሀገር ውስጥ ለበርካታ አመታት በስደተኝነት የተሻለ ቀን እስኪመጣ ድረሰ ትክክለኛ አሀዙ የማይታወቅ ኢትዩጽያዊ የጉልበት ስራ እየሰራ ቤተሰቡን እያስተዳደረ የሀገሪቱን ሕግ አክብሮ ይኖራል ካለፈው ወር ጀምሮ ወያኔና የሱዳን መንግስት ይፋዊ ባልሆነ መልኩ ያደረጉት ድብቅ ስምምነት መሰረት በተቀናጀ መልኩ የሱዳን ደህንነት፤ የልዩ የፖሊስ፤ እንዲሁም ከወታደሩ ክፍል የተወጣጣ  ሰራዊት ዩኒ ፎርም የለበሱና ያለበሱ  የስደታኛውን ማህበረሰብ  ቤት ለቤት በመግባት ፤ በየ አውራ መንገድ ሀበሻው በሚኖርበት አካባቢ እየተዘዋወሩ የስደተኛ  መታወቂያ የያዘውንና እንዲሁም ወያኔና የሱዳን መንግስት ያዘጋጁት ለስድስት ወር የሚቆይ ጊዜያዊ ማታወቂያ ያለውንና ያልያዘውን  መታወቂያ በመጠየቅ በመንጠቅ አስገድደው መኪና ላይ በመጫን  ካርቱም ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ  እስርቤቶች በስሀፋ ዘለጥ፤ በሰሀፋ ሸሪ ፤ በዴም ፤በጅሬፍ፤ ባርኬዌት፤ በሶባ፤ ባህሪ፤ በ እንዱሩማን በከደሮ  በሀጅ የሱፍ ግፍ እየተፋፀመባቸው  ይገኛል ;;

እንደሚታወቀው ወያኔ በትግል ዘመኑ ይሁን ስልጣን ከጨበጠ አንስቶ በ በጎንደር ክ/ሀገር ለምና ወርቅ ምድር ከሆነው የፀለምትንና ሁመራ ወልቃይት ጠጌዴን ገበሬዎችን  በሽህዎች  የሚቆጠሩ ቅድመ አያቶቻቸው ተወልደው ድረው የኮሉበትን ባድማ፤ ለዘመናት ማእረግና ክብር ባዩበት ምድር በግፍ እንዲሰደዱ አድርጎ  የዘር ማፅዳት ወንጅል ካከናወኑ በሓላ በምትኩ  የወያኔን የትግል ዘመኑን ሰራዊትና የራሱን ሰዎች አስፍሮበት ፤ ለህሊና ማመን የሚከብደው ግፍ ከተፈፀመባቸው በሓላ አሁን በስደት የሚገኘው ማህበረሰብን በሚሰራበት የስራ ቦታ ፤ በመንገድ ልጆቹ እዚህ ካርቱም ተወልደው ለመታወቂያ ያልደረሱ ተማሪዎች በግፍ ከነ ቤተሰባቸው ታስረዋል ፤ከሁሉም በላይ ልጆቻቸውን ክርስትና አስነስተው  አስጠምቀው ከቤተክርስትያን በሕዝብ ትራንስፖርት ወደ ቤተቻው በመመለስ ላይ የነበሩትን አውርደው አስረዋቸዋል ፤ ከወለደች አንድ ወር የሆነች አራስ  እህት ከቤቶ አውጥተው በመታወቂያ ስም ከነ እርጥብ ጨቅላ ልጆዋ የሙቀት ደረጃው 50℅በሚደርስበት ሰአት  ታስራለች ፤ ሌላው በወያኔ ደላላ በቀን አንድ ሸህ ዶላር ይከፈላችሁል እየተባሉ ከሞቀ ቤታቸው ሴት ህፃናትን ከት/ቤት እያታለሉ ከሀድያ አካባቢ ከወላይታ፤ ከጅማና ከ አሩሲ ገጠራማው ለም ምድር  ሆን ተብሎ እያሰፈለሱ  በሸህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ካርቱም በሚገኙ የተላያዩ   እስር ቤቶች ውስጥ ኢትዮጽያዊያን  ግፍ እየተፈፀመባቸው ይገኛል; ባሳለፍነው እሁድ ከደሮ በሚገኘው እስር ቤት ኦሮምኛ የሚናገሩ ወንድሞቻችን ተመርጠው  ተነጥለው ወደ አልታወቀ ቦታም ተወስደዋል;;

ከሁሉም በላይ ይህ ሁል በደል በ ኢትዩጽያዊያን ስደተኞች ላየ ሲፈፀም ዩ ኔ ኤች ሲ አር UNHCR / ከ አቅማችን በላይ ነው የሚል መልስ መስጠቱ ያሳፍራል ባሳለፍነው ሳምንት  አቶ ኢሳያስ ወደ ሱዳን ሲመጡ እጅ መንሻ ዳረንጎት ይሆን ዘንድ 30 ኤርትራዊያን ስደተኛ ወገኖቻችን  ለኤርትራ ተላለፈው ሲሰጡ አለም አቀፍ የሰባአዊ መብት ተቆርቐሪ ጮኸት ማሰማታቸው ቢያስደስተንም ይህ ሁሉ በደል በኛ ላይ እየተፈፀመ በየ ቀኑ  እንደወንጀለኛ አንድ መቶ ሀምሳ የሚገመትና አራት መቶ ሸህ የሱዳን ፓውንድ እየተቀጡ  ንብረታቸውን ሳይዙ  ኢትዮጽያዊያን ሲባረሩ አንዳንችም አለምማቀፍ የሰባአዊ መብት ተሞጎች ካው ቦይስ ትንፍሸ አለማለታቸው  ከልብ ያሳዝናል;; ትናትና 13/5/2014 ሁዳ  እየተባለ ከሚጠራው ከ እንዱርማን ውጭ  በርሀ ውስጥ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ ከ አቶ ኢሳያስ ጉብኝት መመለሰ ጋር በተያያዘ ይሁን አይሁን ባይታወቅም 300 ኤርትራዊያን   እስረኞች በነፃ ሲለቀቁ ከ300 በላይ ኢትዮጽያዊያን ሲኖሩ እነዚህም ለበርካታ አመታት ጠያቂ የለላቸው እስረኞችም የመከራን ሕይወት እየገፉ ይገኙበታል;; ሌላው አስገራሚው ድራማ ግን 150 ኢትዮጽያዊያን በዛሬው እለት 14/5/2014 ወደ መተማ ይባረራሉ ከነዚህ እስረኞች መሀል በትናትናው እለት የመሸኛ ወረቀት ሊሴ ፓሴ ሲያዘጋጁ አንዱ እስራኛ  ወያኔ ኢንባሲ ውስጥ  አምልጦቸው ለሊቱን ሙሉ የቀሩትን ሲደበድቦቸው እንዳደደሩ አይን እማኞች ተናግረዋል;;

ለወገን ደራሸ ምንግዜም ኢትዮጽያዊው ወገን ነውና ሰውዲ አረቢያ በነበሩ ወገኖቻችን ሰብአዊነት የጎደለው ግፍ ሲፈጸም ፈጥኖ በመደረስ ይደረስ የነበረውን ውርደት ግፍ  አለምአቀፋዊ ጩኸት በማሰማታችሁ ሊቆም ችሎል አሁንም እኛ ይህንን ሁሉ ሰቆቃ እንደ ራሄል እንባ በማንባት በመንበረ ፅብዐቱ እሰኪ ዘልቅ የግፍአን እንባና ጮኸታቸን በየቤቱ ሁሉም እያሰማን   ብንገኝም ከ እለት እለት ተዘርዝሮ የማያልቅ በደል ሰሚ የለለው በኛ ምንዱባን ላይ በወያኔ ልዩ ቅንብር ስለሚፈፀምብን በመላው አለም የምትገኙ ወገኖቻችን ከምንግዜው በበለጠ ትደርሱልን ዘንድ እንማፀናለን;; ይህንን የግፍአን ድምፅ ልሳን ትሆን ዘንድ እያቃተትን እንማፀናለን ;; አዎ ! ይህንን ሁሉ በደል ከደንበሩ ጋር  ስለምናያይዘው የሱዳን መንግስት አለም አቀፍ ስምምነቶችን አክብሮ ሰብአዊነታችንን እንዲያከብር እንዲሁም ዩ ኔ ኤች ሲ አር UNHCR ጉዳያችን ቅድምያ ሰጥቶ ዝምታውን ሰብሮ  ይህንን ሁሉ ግፍ በ አስቸኾይ እንዲያስቆም በ አንድ ድምፅ ታሰሙለን ዘንድ እንማፀናለን;;

አጥናፉ መሸሻ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on May 15, 2014
  • By:
  • Last Modified: May 15, 2014 @ 9:50 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar