www.maledatimes.com የያራ ፋውንዴሽን እና የህወሃት ወያኔ ጥምረት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የያራ ፋውንዴሽን እና የህወሃት ወያኔ ጥምረት

By   /   September 9, 2012  /   Comments Off on የያራ ፋውንዴሽን እና የህወሃት ወያኔ ጥምረት

    Print       Email
0 0
Read Time:21 Minute, 1 Second

የያራ ፋውንዴሽን የተቋቋመው  በያራ ኢንተርናሽናል በኩል ሲሆን እ.ኤ.አ 2005  ዘመን ነበር ።የምስረታው ዋነኛ አላማ የአፍሪካን የአረንጓዴነት የመለወጥ ዘመቻ በሚል የተሰየመ ሲሆን ለዚህም ዋናው አንቀሳቃሽ በመሆን የተመዘገቡት የቀድሞው የዩኤን ሰክረተሪ ጀነራል ኮፊ አናን በዋናነት ይጠቀሳሉ ይህ የአፍሪካ አረንጓዴ የለውጥ ጉዞ የሚለውንም ስያሜ ያገኘው በኮፊ አናን በኩል እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ ።መቀመጫውን በኖርዌይ ያደረገው ይሄው የያራ ፋውንዴሽን በየአመቱ በግብርናው ዘርፍ ስኬት አመጡ የሚላቸውን የተለያዩ አገራትን በሽልማት ማንበሽበሹን ተያይዞታል ከእነዚህም ውስጥ አንዷ ኢትዮጵያ ለ2ኛ ጊዜ የሽልማቱ ተቋዳሽ ሆናለች በዘንድሮው አመት ደግሞ ሽልማቱን ያገኙት የኢትዮጵያ የምርት ገበያ መስራች እና ዋና ስራ አስፈሳሚ ዶ/ር ኢሌኒ ገብረ መድህን ናቸው ።

በተለያዩ ጊዜያት ውስጥ  የያራ ፋውንዴሽን ለህወሃት ወያኔ መንግስት የሚሰጠው የሽልማት ስነስርአት  በቅጡ ተመዝኖ እና ለአደረጉት የስራ ጥረት ታይቶ ነው ሽልማት የሚያበረክተው  ወይ የሚለው በየጊዜው አጠራጣሪ ከመሆኑም በላይ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የቅርብ ሽርክና ያለው አስመስሎታል ። ባለፉት አመታት ለሟቹ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የተሰጠው የዚህ ድርጅት ሽልማት በብዙዎች ዘንድ በሙስና የተሰጠ ነው ፣መመለስ ይገባዋል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተው እንደነበር እና የተለያዩ የመገናኛ  ብዙሃኖች  ትክክለኛ ሽልማት አይደለም ሲሉም መዘገባቸው ይታወሳል ።በተለይም በዌስተርን መንግስታቶች እና በአሜሪካኖች በኩል “አስገራሚው ሽልማት “ሲሉት በለበጣ አነጋገር የሽልማት ድርጅት ሰጭውን እና አቶ መለስ ዜናዊን ወርፈዋቸዋል።

መንግስት በግብርናው ልምአተ ግብአት ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረኩ ነው በሚለው በዚህን ሰአት የአርብቶ አደሩ እና የአርሶ አደሩ ቁጥር የኑሮ ደረጃም ሆነ የምርት ደረጃው እየተመናመነ ባለበት  ወቅት  አገሪቱን  በግብርናው ልማት እድገት አሳይታለች የሚለው ይህ ድርጅት ከምን አንጻር እንደሆነ ጎልቶ ለማሳየት የቻለ ድርጅት አይደለም ።እንደ ህወሃት ስልት ከሆነ በወረቀት ተቀነባብሮ የሚጻፍለትን አመታዊ ሪፖርት በማየት ብቻ የሚሰራቸው ፣የሽልማት ስነስርአት ሽርጉድ ፣በተጣራ መልኩ ቢሆን እና የሽልማት ስነ ስርአቱ አርብቶ አደሩን እና አርሶ አደሩን ብቻ ያማከለ ቢሆን እና ሽልማቱም ተገቢነቱ ለነርሱ ብቻ ቢሆን በተመረጠ ነበር ።

ነገር ግን ላለው ይጨመርለታል ነውና ነው ነገሩ ።ዛሬም በተመሳሳይ ሁኔታ የኢትዮጵያ የምርት ገበያ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እሌኒ ገብረ መድህን በግብርና ግብዓት አምራችነቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቀው ያራ ፋውንዴሽን የዘንድሮ ተሸላሚ በመሆን የተበረከተላቸውን 30 ሺሕ ዶላር ለበጐ አድራጐት ድርጅት ሊያውሉት እንደሚችሉ ተጠቅሶአል ።የኢትዮጵያ ህዝቦች በቁጥር በየአመቱ በአማካይ በ3% ያድጋል ።ይህ ማለት በ1-15 አመት እድሜ መካከል ባላቸው ሰዎች  በአማካይ 150 ሚሊዮን የሚሆኑ ትውልዶች ተፈጥረዋል የህዝቡ ቁጥር በዚህን ያህል በነዚህ ጥቂት አመታት ውስጥ ከጨመረ የኢሃዴግ የግብርናው ምርታማነት ያደገው ደግሞ 1.7% ብቻ ነው በዚህም ሳቢያ ኢሃዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ ለረሃብ የተጋለጠው ገበሬ ቁጥር እየጨመረ ይሄዳል ሄዷልም።

ከ1994/95 አ.ም 14 ሚልዮን ወርዶ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም በ2005 ደግሞ 7 ሚልዮን ነበር ፣ኢሃዴግ ስልጣን ሲይዝ ግን 6 ሚሊዮን ብቻ  ነበር የተራበው ህዝብ አሃዝ ቁጥር ።የኢህአዴግ አገዛዝ ከቀጠለበት እና በተለይም ከምርጫ 97 በኋላ ባለው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዝርገታ ዲስኩር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ማለትም ከዛሬ ሰባትእና  ስምንት አመታት ውስጥ ብቻ ፣ለረሃብ የተጋለጠው ገብሬ ከ20 እስከ 30 ሚሊዮን ደርሶአል ።ይህ ቁጥር ከአንድ የአፍሪካ አገር ጋር የሚነጻጸር የቁጥር አሃዝ ነው ።

በእንደዚህ አይነት የኢኮኖሚ እና የግብርና እድገት ባለባት አገር ውስጥ የያራ ፋውንዴሽን ለህወሃት አመራር አባላት እና ወዳጆች የሚያቀርበው የሽልማት ገንዘብ ፣ምንን ያመለከተ ነው እንዴትስ ሊሆን ቻለ ። ምን አይነት  የስራ ድርሻ ተወጥተው ነው ወ/ሮ እሌኒ ? ወይስ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር የቅርብ ረዳት ሆነው ስላገለገሉ የተበረከተላቸው የያራ ፋውንዴሽን ስጦታ ? በእንደነዚህ አይነቶች የስጦታ ዙሪያ ላይ ምንም አይነት የምርምራዊ ስራ ባይከናወንባቸውን መንግስት ከመቀበል ወደኋላ የማይል እንደሆነ ይታወቃል ።በተለይምእት  የወያኔ መንግስት ገንዘብ ልውውጥ እና መሬት ሽያጭ ወደ ተባለበት ቦታ አዝማሚያቸውን  በማዞር የሃገሪቱን አንጡራ ሃብቶች ሁሉ እስከመሸጥ መለወጥ ደርሰዋል። በግብርናው ልማት ያለው አሰራር እስካሁን ድረስ ካለው ችግር አንጻርና ከድህነቱም ባሻገር ሃገሪቱ በከፍተኛ የኑሮ እና የኢኮኖሚ አዘቅት ውስጥ ገብታለች ።በሃይለኛ ውጥረት ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያን የፖለቲካዊ ይዘት ለመለወጥ በተለያዩ መንገዶች የህብረተሰቡን አሉታዊ እና አወንታዊ ተጽእኖዎች ለመቀልበስ የሚያመች ዘዴ መፈጠሩ አነጋጋሪ ጉዳይ ነው ።

ለወ/ሮ ኢሌኒ የሽልማት ስነ ስራትን አስመልክቶ ያራ ፋውንዴሽን እንደሚለው ከሆነ $60.000 የሽልማት ስጦታ ከዋንቻ እና የዲፕሎማ ሰርተፊኬት ጋር ሲኖረው ስድሳ ሺህ ብሩን ለሁለት ከፍሎ ለሁለት የአፍሪካ ተሸላሚዎች እንደሚሸልም አረጋግጦአል አንደኛዋ ዶ/ር አግነስ አሊባታ የሚባሉ የግብርና እና እንሰሳት እርባታ ሚንስትር የሆኑ ሲሆን ዜግነታቸው ሩዋንዳዊት ናቸው ሁለተኛዋ ዶ/ር ኢሌኒ ናቸው የዶ/ር ኢሌኒን ስንመለከት ግን ሽልማቱን ሊያገኙበት የቻሉበት የቡና ምርትን በከፍተኛ ደረጃ ቀድሞ ከነበረበት በበለጠ ሁኔታ አሳድገውታል ሲል ያብራራል ይህም ሆኖም እኛም ሙሉ ቃሉን እንደዚህ በእንግሊዝኛው አስቀምጠነዋል ።Reasoning behind Dr. Eleni Gabre-Madhin’s award
Dr. Eleni Gabre-Madhin is the founder and outgoing CEO of the Ethiopia Commodity Exchange (ECX). She is being awarded the prize for showing visionary and remarkable leadership in managing the transformation process toward an efficiently functioning market, especially for smallholder coffee producers in Ethiopia.

The ECX has had a far-reaching impact in Ethiopia in several areas of agriculture and in the lives of small farmers since its inauguration in 2008. Under her leadership, ECX’s growth has seen a strong increase in volumes every year, from trading 138,000 tons in the starting year 2008/2009 to 601,000 tons in 2011/2012. The value of ECX trades reached USD 1.2 billion in 2011/2012, representing up to USD 20 million per day. With a transparent and efficient market, the share of the final export price for coffee has risen from 38 percent to 65 percent, having a positive impact for 15 million coffee farmers in Ethiopia. At present, 12 percent of ECX membership is made up of farmer cooperatives, representing 2.4 million smallholder farmers. Dr. Gabre-Madhin was among The Africa Report’s “50 Women Shaping Africa” 2011, was named Ethiopian Person of the Year 2010 and was nominated for Outstanding Businesswoman of the Year 2010 by African Business. She received the African Banker Icon Award for 2012 እንዲህ ከሆነ ነገሩ ታዲያ ለምን የኢትዮጵያ ቡና አምራች ገበሬዎች ማህበር እድገቱን አያሳየንም ?ለምን የራሱን የሆነ መፈልፈያ አቋቁሞ ፣የግብርናውን ልማት አያስፋፋም ፣የቡና ገበያው እንዲህ ሰፍቶ ሃገሪቱንም ለሽልማት የሚያበቃ ከሆነ ግንባር ቀደም ተጠቃሚው እና ተሸላሚው ገበሬው እንጂ ዶ/ር ኢሌኒ ሊሆኑ ባልተገባ ነበር ። አመት ለፍቶ ጥሮ ግሮ ላቡን አፍስሦ የምርቱን ውጤት በጥሩ ሁኔታ የማያገኘው ያገሬ ህዝብ መች ይሆን የዚህ እድል እጣ ፈንታ የሚወጣለት ? ወይስ ገንዘብ ካለህ በአምራች ገበሬው ስም ልትሰየም ግድ ይላል ?ለዚህ ሽልማት አሁንም ተጠያቂው የያራ ፋውንዴሽን ሲሆን ግብርና ልማት ፣ማምረት እና አምራች ልዩነቱን ማወቅ ተገቢ ሲሆን ወደ ውጭ የሚወጡት የቡና ምርት መጨመር እና መቀነስም የሚለካው ከገበሬው ወቅታዊ የኑሮ ሁኔታ እና የግብርና ዘርፍ የእድገት ወይም የስራ ጥረት ቅልጥፍና እንጂ የዶ/ር እሌኒ የወረቀት ማሸግ ስራ እንዳልሆነ ሊታወቅ የሚገባ ነው።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ቡና ገበያ ምርት ከገበሬው ከተወሰደ በኋላ በማከማቻዎቻቸው በማስመጥ ፣እንደ እሌኒ ላሉት የጊዜው ባለሃብቶች በማከፋፈል የስራ ድል ተቆናጠጡ ስኬትን አመጡ እያሉ ከማወደስ ይልቅ ፣የስራ ፈጠራን ለጀመሩት ታላላቅ የሃገራችን ገበሬዎች ክብሩን ባወረስናቸው ፣ለነገው የሚሆነውንም የምርት ስራ እና ትርፍ ግብርናንም ባሳየን መልካም ነበር ነገር ግን ዋነና ሰሪውን ከማወደስ ይልቅ ገንዘብ እና ስም ያለውን መገንባት የለመደው የዚህ አለም አሰራር መች ይለወጥ ይሆን ። አሁንም የወይዘሮ ኢሌኒ ሽልማት ተገቢ ሊሆን እንደማይችል ምንም ጥርጥር የለውም ።ሙሉውን የያራ ፋውንዴሽን ሪፖርት አስመልክቶ ከዚህ በታች አቅርበነዋል ያንብቡት እናመሰግናለን ማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል።

(2012-09-05 08:00)

Yara International ASA: African female leaders awarded the Yara Prize

 

Oslo (2012-09-05): The Yara Prize 2012 is being awarded to Dr. Agnes Kalibata, Minister of Agriculture and Animal Resources in Rwanda, and to Dr. Eleni Gabre-Madhin, outgoing CEO of the Ethiopian Commodity Exchange (ECX) in Ethiopia.

The Yara Prize Committee has selected two prominent African female leaders for their work on groundbreaking areas for the African Green Revolution: effective public policies in support of agricultural growth and profound innovation in agricultural markets.

Both leaders have demonstrated how transformative change can be achieved in a complex and challenging environment. They have applied innovative approaches, collaborating with partners in new ways. Their achievements are fit to inspire other countries to transform the productivity and sustainability of their agricultural sectors.

“Yara creates impact by addressing global challenges. By awarding the Yara Prize, we salute the champions of sustainable agricultural development. I wish to extend my personal congratulations to the laureates,” Jørgen Ole Haslestad, President and CEO of Yara and Chairman of the Yara Prize Committee, said.

“The impressive transformational work the laureates are doing provides great inspiration, and this is exactly the kind of development we want to promote in the Grow Africa Initiative, co-chaired by Yara alongside NEPAD and the African Union.”

The two laureates will be celebrated at the State Banquet/Gala night on September 27 during the African Green Revolution Forum (AGRF) 2012 in Arusha, Tanzania.

Reasoning behind Dr. Agnes Kalibata’s award
Dr. Agnes Kalibata is being awarded the prize for her great leadership in the transformation of food security and agricultural development in Rwanda in a relatively short period of time.

She currently serves as the Minister of Agriculture and Animal Resources for the Republic of Rwanda. For six years, Minister Kalibata has been the architect of the remarkable transformation of Rwandan agriculture. Rwanda has moved from having a food deficit to being a country that is largely food self-sufficient. Over 1 million Rwandans have moved out of poverty between 2005 and 2011. Dr. Kalibata has been able to align national agricultural policies with the NEPAD/CAADP frameworks, i.e. the commitment to increase government budget share for agriculture to 10 percent, and Rwanda was the first country to adopt a Comprehensive Africa Agriculture Development Programme (CAADP) compact. Internationally, the country has in many ways become a success story that has inspired other African countries. By sustaining the gains in food security and the future of agriculture in Rwanda, Dr. Kalibata has been a driving force behind the Grow Africa Initiative, a partnership platform to accelerate investments for sustainable and inclusive growth in African agriculture.

Reasoning behind Dr. Eleni Gabre-Madhin’s award
Dr. Eleni Gabre-Madhin is the founder and outgoing CEO of the Ethiopia Commodity Exchange (ECX). She is being awarded the prize for showing visionary and remarkable leadership in managing the transformation process toward an efficiently functioning market, especially for smallholder coffee producers in Ethiopia.

The ECX has had a far-reaching impact in Ethiopia in several areas of agriculture and in the lives of small farmers since its inauguration in 2008. Under her leadership, ECX’s growth has seen a strong increase in volumes every year, from trading 138,000 tons in the starting year 2008/2009 to 601,000 tons in 2011/2012. The value of ECX trades reached USD 1.2 billion in 2011/2012, representing up to USD 20 million per day. With a transparent and efficient market, the share of the final export price for coffee has risen from 38 percent to 65 percent, having a positive impact for 15 million coffee farmers in Ethiopia. At present, 12 percent of ECX membership is made up of farmer cooperatives, representing 2.4 million smallholder farmers. Dr. Gabre-Madhin was among The Africa Report’s “50 Women Shaping Africa” 2011, was named Ethiopian Person of the Year 2010 and was nominated for Outstanding Businesswoman of the Year 2010 by African Business. She received the African Banker Icon Award for 2012.

About the Yara Prize
The Yara Prize for an African Green Revolution seeks to contribute to the transformation of African agriculture and food availability, within a sustainable context, thereby helping to reduce hunger and poverty. The Yara Prize is based on nominations of candidates who are carefully evaluated by the Yara Prize Committee. The Yara Prize consists of USD 60,000, which will be split between the laureates, a crystal trophy and a diploma. The Yara Prize was handed out in Oslo from 2005 to 2009. In 2012, it moved to Africa and will be handed out on September 27 at the State Banquet/Gala night as part of AGRF 2012 in Arusha, Tanzania. The Yara Prize will be handed out annually in Africa. Read more at:www.yaraprize.com

To the editorial offices:
Link to pictures of the two laureates: 
http://yaraurl.com/irj7

For more information, please contact:
Bernhard Stormyr, Communication Manager, Yara International ASA
Telephone: +47 9010 7685
E-mail: bernhard.stormyr@yara.com

Yara delivers solutions for sustainable agriculture and the environment. Our fertilizers and crop nutrition programs help produce the food required for the growing world population. Our industrial products and solutions reduce emissions, improve air quality and support safe and efficient operations. Founded in Norway in 1905, Yara has a worldwide presence with sales to 150 countries. Safety is always our top priority.
www.yara.com

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 9, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 9, 2012 @ 9:45 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar