www.maledatimes.com አንቀጽ 19 በተግባር ተጥሷል – ሕገ መንግስቱን ሳያከብሩ ማስከበር አይቻልም የታሳሪዎች የምርመራ ሂደትን አስመልክቶ ከዞን 9 የተሰጠመግለጫ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አንቀጽ 19 በተግባር ተጥሷል – ሕገ መንግስቱን ሳያከብሩ ማስከበር አይቻልም የታሳሪዎች የምርመራ ሂደትን አስመልክቶ ከዞን 9 የተሰጠ መግለጫ

By   /   May 16, 2014  /   Comments Off on አንቀጽ 19 በተግባር ተጥሷል – ሕገ መንግስቱን ሳያከብሩ ማስከበር አይቻልም የታሳሪዎች የምርመራ ሂደትን አስመልክቶ ከዞን 9 የተሰጠ መግለጫ

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 23 Second

አዘጋጅ 

ከታሰሩ 22 ቀናትን ያስቆጠሩት የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች በቤተሰብም ሆነ በሕግ ባለሞያ የመገናኘት መብታቸውን
 ለማግኘት 19 ቀናትፈጅቶባቸዋል፡፡ ከታሰሩ እስከ 17 ቀን ድረስ ማንም የቤተሰብ አባል ሳይጎበኛቸውና በወዳጅ ዘመዶች
 ሳይጠየቁ የከረሙ ሲሆን ከጠበቆች
 ጋርለመገናኘት ደግሞ 19 ቀናት ፈጅቷል፡፡ አሁንም ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት ያልቻሉ ቀሪ እስረኞች አሉ፡።
በተለምዶው እነደሚደረገው የፓሊስ ማእከላዊ ምርመራ የቤተሰብ ጉብኝትን አይቻልም በሚል ቀላል ቃል የከለከለ ሲሆን
ለጠበቆች ስብሰባ ላይነን የሚል ምክንያት ሲሰጥ ከርሟል፡፡ ይህ በመሆኑም የተነሳ የተያዙ ሰዎች መብት የሆነው የህገ መንግስቱ
አንቀጽ 19 ሁለት ላይ ያለው የተያዙሰዎች ያለመናገር
 መብት ( the right to remain silent) በይፋ ተጥሶ ያለማንም የህግ ባለሞያ ምክር ለብዙ ቀናት ምርመራ ሲደረግባቸውቆይቷል፡፡
ምርመራቸውን ጨርሰዋል ተብለው የታሰቡ ታሳሪዎቸን ካልሆነም በስተቀር በምርመራ ወቅት የህግ ባለሞያ ለማግኘት አልተፈቀደላቸውም፡፡
መሰረቱ መሰረታዊ የሆነው ያለመናገር መብትና የሕግ ባለሞያ የማግኘት መብት መከልከሉ የተለመደውን ማእከላዊ ምርመራ የሚታማበትን
የማስገደድ ምርመራ እውነተኛነት የሚያጋልጥ ነው፡፡ በተጨማሪም የአካልና የስነልቦና ጉዳት የማድረስ ምርመራ ሲፈጸምባቸው እነደነበረ የተያዙየዞን ዘጠኝ አባላት በተናገሩበት ወቅት ፍርድ
ቤቱ የነዚህን ጉዳቶች መከልከል ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጪ ይሄ ነው የሚባል እርምጃ እናማጣራት ለመውሰድ አልሞከረም፡፡
ማዕከላዊ ምርመራ ከዚህ በፊት የሚታወቅበት ድብደባ፣ ምግብና እንቅልፍ መከልከል፣ የስነልቦና ጫና እና ማስፈራሪያ የተለያዩ ዛቻዎች
ሁሉም በተያዙ የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ በተለያየ መልኩ እነደደረሰ ተረድተናል፡፡ ይህም ምርመራውን ተከትሎ የሚመጣውንማንኛውንም ማስረጃ በሕግም በሞራልም ተቀባይነት እነዳይኖረው እነደሚያደርግ እናውቃለን፡፡
ከታሳሪዎች የሚገኙ ማንኛውም መረጃዎች በከፍተኛ ተጽእኖ ስር እንደተሰጡ አንዲሁም ዝም የማለትና የሕግ ባለሞያ ምክር የማግኘት ሕገ-መንግስታዊ መብቶቻቸው ተጥሰው የተገኙ እንደሆኑ ዞን ዘጠኝ ያምናል፡፡ በወንጀል ህግ ስነስርአት መሰረት እነዚህ ያለህግ ባለሞያ ጉብኝትያለመናገር መብታቸው (የህገ መንግስቱ አንቀጽ 19) ተጥሶ የተገኙ መረጃዎች
በዚህ ምክንያት ብቻ ተቀባይነት እነደማይኖራቸውም የአገሪትዋሕግ ይደነግጋል፡፡
በመሆኑም መንግስት ታሳሪዎቹን አንደፈታ እና ጉዳያቸው ሕገ መንግሰታዊ እና የወንጀል ህግ ሥነ-ስርአት ሕጉን ተከትሎ አንዲሆን እንዲያደርግና
ሌሎች እንዲያከብሩ የሚጠይቀውን ሕግ መንግስት ራሱን በማክበር አንዲጀምር አሁንም በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን ፡፡
ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ ማእከላዊ ምርመራ የሚገኙ የዞን ዘጠኝ አባላት እና ጋዜጠኛ ወዳጆቻችን ያለንን ክብር እና ፍቅር እየገለጽን ጽናታቸው
አስተማሪ ሲሆን በሚከተሉት ቀናት በሚኖሩት ማንኛውም የህግ ሂደቶች ውስጥ የሚኖሩትን አዳዲስ መረጃዎች ለዞን ዘጠኝ ነዋሪያንእንገልጻለን፡፡ነገ ቅዳሜ ግንቦት 9 እና እሁድ ግንቦት 10 የሚደረጉ የፍርድ ቤት ሄደቶችን አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ጠዋትበመገኘት መከታተልና
 አጋርነታችሁን ማሳየት ትችላላችሁ፡፡
የዞን ዘጠኝ ስብስብ አባላቶቹ ምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደማያውቁ በድጋሚ ለማረጋገጥ ይወዳል፡፡
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on May 16, 2014
  • By:
  • Last Modified: May 16, 2014 @ 6:52 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar