www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት Ethiopian National Transitional Council ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት የአዲስ ዓመት መልዕክት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት Ethiopian National Transitional Council ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት የአዲስ ዓመት መልዕክት

By   /   September 9, 2012  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት Ethiopian National Transitional Council ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት የአዲስ ዓመት መልዕክት

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 15 Second

85 S. Bragg Street, Suite 504
Alexandria, VA 22312, USA
Tel: 1-202-735-4262
www.etntc.org
contact@etntc.org2.
አዲስ ዓመት ሲመጣ አዲስ ተስፋ፥ አዲስ ራዕይ፥ ሰንቆ መነሳት፥ በጎ መመኘት፥ ያለፈውን በመዝጋት ለወደፊቱ የተሻለ መመኘት፥ በአጠቃላይ መልካም ነገሮችን ሁሉ መሻት ባህላችን ነው። ካለፈው በመማር ለወደፊቱ የተሻለ ስራ ለመስራት መሰናዳት ደግሞ የበሳልነት ምልክት ነው። አልበርት አነስታይን እንዳለው ‘አንድን ነገር በተመሳሳይ መንገድ እየሰሩ የተለየ ውጤት መጠበቅ ሞኝነት ነው’ እና ባለፈው ዓመት የተከተልናቸውን ያልሰሩ አካሄዶች ገምግመን የተለየና የተሻለ አሰራር በመምረጥ ለተሻለ ውጤት መስራት ከሁሉም የሚጠበቅ ነው።
የሀገራችንን ያለፈውን አንድ አመት ተጨባጭ ሁኔታ ስንገመግመው እጅግ በርካታ አሳዛኝ ሁኔታዎችን የታዘብንበት ዓመት ሆኖ አልፏል። ህዝባችን በዋጋ ግሽበትና በገንዘብ የመግዛት አቅም ማነስ በመኖርና
በሞት መካከል የሆነ ኑሮ ላይ እንዲሆን የተገደደበት ሁኔታ ውስጥ ይገኛል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ዘንድሮም ለረሃብ በመዳረጋቸው ለምግብ እርዳታና ምጽእዋት ተዳርገዋል። አፈናው፥
ጭቆናው፥ ዘረኝነቱና ከፋፋይነቱም ብሶበት ቀጥሏል። ለነጻነታቸው የቆሙ በርካታ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ  መብት ታጋዮች ወህኒ ቤቶች ተወርውረው እየማቀቁ ይገኛሉ። የሃይማኖት ተቋማት ነጻነት ተረግጦ ይህንኑ የተቃወሙ አማኞች ተደብድበዋል፥ ታስርዋል፥ ተገደልዋል። የሀገሪቱ አንጡራ ሀብት እየተመዘበረ ይገኛል። ባጠቃላይ የህወሃት/ኢህአዴግ ስርአት አካሄድ ሀገሪቱንና ህዝቧን በከፍተኛ ሁኔታ ጎድቷል።
ይህ ሁሉ በእንዲህ እንዳለ፥ የወያኔ/ኢህአዴግ አምባገነን አገዛዝ መሪ የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ በዓመቱ የመጨረሻው ወራት አካባቢ ላይ ላይ በሞት በመለየታቸው የተቀሩት የስርዓቱ አራማጆችና የኢትዮጵያ ህዝብ ያልታሰበ አማራጭ ተቀምጦላቸዋል። አንደኛው እስካሁን በነበረው የጥፋት ጎዳና ላይ መጓዝ ሲሆን፥ ሌላው ደግሞ የፍትህ፥ የሰላምና የእድገት ጎዳናን መምረጥ ነው። ህዝባችን ባሁኑ ወቅት የሚሻዉ ቆራጥ፤ ደፋር፤ አቅጣጫ የሚያሲዘዉ አመራር ነዉ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤትም ሀገራችንና ህዝባችን አዲስ መንገድ፤ አዲስ አካሄድ፤ አዲስ ራእይና፤ አዲስ አመራር እንደሚያስፈልገዉ በአጽንኦት ያምናል። ይህም መሆን እንዳለበት ባለፉት
ተከታታይ ወራት ሲያስረዳ ቆይቷል። ለሕዝባችንም በድጋሚ ጥርት ያለውን አቋማችንና መደረግ ስለሚገባው የትግልና የለውጥ ሂደት ከዚህ በታች በዝርዝር እናስቀምጣለን።
1. ሀገራችንን ከህወሀት/ኢህአዴግ የጥፋትና የውድቀት ጎዳና ለመመለስና አዲስ አቅጣጫ ለማስያዝ አዲስ ሁሉን ያካተተ የሽግግር መንግስት በአስቸኳይ መቋቋም አለበት ብለን እናምናለን።
ስለዚህም ከእንግዲህ የምናደርጋቸው የትግል እንቅስቃሴዎች በዚህ ጥርት ባለው አቋማችን ዙርያ ይሆናል።
የሽግግር መንግስት ለማቋቋም ሁሉን አቀፍ የሆነ በሽግግር ሂደቱ ላይ የሚመክር ጉባኤ ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንዲካሄድ ጥሪ እያስተላለፍን ይህም እንዲሳካ የበኩላችንን
አስተዋጽኦ ሁሉ እናደርጋለን።
3. በሁሉም በጋራ በምንቀሳቀስባቸው መድረኮች ላይም የሽግግር መንግስቱን ምስረታ ሀሳብና የሂደቱን ራእይ ለማቅረብና ተቀባይነትም አግኝቶ ተግባራዊ እንዲሆን እንጥራለን።
4. ሀገር ቤትና በዉጭ የሚገኙ ይህንን የሽግግር መንግስት ምስረታ የሚደግፉ የፖለቲካና ሲቪክ ማህበራት እንዲሁም ግለሰቦች በሀሳቡ ዙርያ የሚሰባሰቡበትን ሁኔታዎች እናመቻቻለን።
5. የሽግግር መንግስት ምስረታውን ሃሳብ እውን ለማድረግ መላው ህብረተሰብ በዓላማው ዙርያ በመሰባሰብ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርግልን ጥሪ እናቀርባለን።
የሽግግር መንግስት ምስረታውን ሂደት በተመለከተ ህብረተሰባችን ግልጽ የሆነ የትግል አቅጣጫና አመራር የእንደሚሻ እናውቃለን። በሽግግር መንግስት ሀሳብ ዙሪያ ለዓመታት ስንሽከረከር ከርመናል። አሁን ግን ሁላችንም ደፋርና ቆራጥ በመሆን እየወደቀ ያለውን የህወሀት/ኢህአዴግ አገዛዝ የሚተካ ሁሉ-አቀፍ የሽግግር መንግስት በአቸስኳይ በማቋቋምና ያለንን ሀይል በማሰባሰብ ሀገራችንን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከግፈኛውና ጸረ-ኢትዮጵያ የወያኔ ስርዓት ነጻ ለማውጣት እንነሳ።
በአዲሱም ዓመት የእኛ ቁጥር አንድ ተግባር ይህንን የሽግግር መንግስት ምስረታ አላማ መላውን ህብረተሰብ በማሳተፍ ማሳካት ይሆናል። በኛ በኩል ያለንን ግልፅና የማያወላውል አቋም ለህዝባችን
አሳውቀናል። ወገናችንም በዚህ መሰረታዊና ግልፅ የትግል አማራጭ ዙርያ እንዲሰባሰብ የአዲስ አመት ጥሪ እናስተላልፋለን።
በአዲሱ ዓመት ግፍ፤ ዘረኝነት፤ ዝርፍያ፤ ስደት፤ ረሃብ፤ የኑሮ ውድነት፤ እስርና እንግልትን የምናስወግድበት የለውጥ ውጥናችን ተሳክቶ በምትኩ ነጻነት፤ ፍትህ፤ እኩልነት፤ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር
በሀገራችን እንዲሰፍን ያለንን ምኞት ለመላው ህዝባችን እንገልፃለን።
መልካም አዲስ አመት
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 9, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 9, 2012 @ 11:32 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar