www.maledatimes.com አቤ ቶክቻው በረረ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አቤ ቶክቻው በረረ

By   /   September 10, 2012  /   Comments Off on አቤ ቶክቻው በረረ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 12 Second

abe tokichaw 3rd book

የአቤቶክቻው ሽሙጦች በተሰኘው መጽሃፉ ፣ እንዲሁም አቤ ቶክቻው በሚለው ብሎግ እና ድህረ ገጽ የሚታወቀው አበበ ቶላ በዛሬው እለት ከኬንያ የስደት ህይወት  ወደ እንግሊዝ ማምራቱን ምንጮጫቸን ገልጸዋል ።ባሳለፍነው አመት መጀመሪያ ላይ በመንግስት የሚዲያን  አፈና  ምክንያት ከአገር እንዲወጣ የተፈረደበት አበበ ቶላ በከፍተኛ  የስቃይ እና መከራ ቆይታበስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን በታየለት ሁኔታ ወደ እንግሊዝ ኑሮውን እንዲያደርግ ተደርጓል ። ከዚያም በደህንነት አባላቱ አማካኝነት መንግስት አቋም እንደወሰደና ከዚህ በኋላ ቀጣቱ እርምጃ እስር እንደሚሆን ተነገረው። ወቅቱ የፍትህ ጋዜጣ ምክትል አዘጋጅ ውብሸት ታዬ እና የፍትህ አምደኛ ርዕዮት አለሙ የታሰሩበት፤ የአውራምባው ዳዊት ከበደ አገር ጥሎ የወጣበት፤ አቤ ቶኪቻውም በፍትህ ጋዜጣ ላይ በሚያወጣቸው ስራዎቹ በመንግስት የክትትል ስር የወደቀበት ወቅት ነበር።በስደቱ ዘመን አቤ ቶክቻው የት ገባ የሚል ፍለጋ ተብሎ  ፍለጋው ሲከናውን ነው ፍለጋ በአንድ ወንድሙ ሞት ሊፈጸም በቅቷል ።የወያኔ መንግስት የሚፈልገውን ሰው ሲያጣ በቤተሰቦቹ ላይ የመዞሩ ጉዳይ የተካኑት ትልቁ ስልታቸው ሲሆን በአቤ ቶክቻው (አበበ ቶላ) ቤተሰብ ላይ የተፈጸመው ፍርድ አንዱ እና በገሃድ የተደረግ ወንጀል መሆኑ ሁሉም የሚያስታውሰው ነው ። አበበ ቶክቻው በስደት ውስጥ እያለ አዲስ መጸሃፍ አሳትሞ ለገበያ ያቀረበ ሲሆን በመጸሃፉ ፊት ለፊት ገጽ ላይ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚንስትር ፎቶ በሶስት ደረጃ አስቀምጦት ይታያል ይሀውም የማርክሲዝም ሌኒንዝምን አላማ የሚያራምዱበት ስርአታቸውን የሚያሳይ ሲሆን በሌላም በኩል መለስ ከትግል ጀምሮ ስልጣን እስከተቆናጠጡበት እና እንዲሁም እስከ እለተ ሞታቸው ጊዜ የሚያሳየውን ልዩነት እና የፖለቲካዊ ፋይዳ የሚዳስሥ ገጽታ እንያለን ።አቤ ቶክቻው በቀልድ መልክ እያዋዛ የሚያጫውተን ቁምነገሮች የወቅቱን የፖለቲካ ሂደት እና አስተዳደራዊ ብቃት ጠንቅቆ የሚያሳይ ጽሁፍ ነው።በዛሬው እለት ጉዞውን ያደረገው አበበ ቶላ ባሳለፍነው ሳምንት በህመም ላይ ቆይቶ ስለነበር የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ለጠየቅነው ቃለመጠይቅ ጊዜ ባይሰጠንም ፣በኬንያ ሳለ ፣አብረውት ለነበሩ ፣በህይወቱ ሙሉ መልካምን ላደረጉለት እና በተለያዩ አጋጣሚዎች ጽሁፎቹን በመከታተል ጥንካሬውን ላደረሱት ወገኖች ምስጋናውን ያደረሰ ሲሆን እንግሊዝ ላላችሁት ወዳጆቹ እና የጽሁፉ አፍቃሪያን እዚያው ማንቸስተር ሲቲ እንገናኝ ብሏችኋል ።ማለዳ ታይምስ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 10, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 10, 2012 @ 7:54 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar