www.maledatimes.com መዝናኛ ቤቶች ዘፈን በማሰማታቸው ታሸጉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መዝናኛ ቤቶች ዘፈን በማሰማታቸው ታሸጉ

By   /   September 10, 2012  /   Comments Off on መዝናኛ ቤቶች ዘፈን በማሰማታቸው ታሸጉ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 31 Second

ከኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሞት ጋር በተያያዘ በርካታ የምሽት ቤቶች እየታሸጉ መሆናቸው ተጠቆመ፡፡ በከተማው ውስጥ በመዘዋወር ዜናውን ያጠናቀሩት ዘጋቢዎቻችን ካቀረቡት ሪፖርት
መረዳት እንደተቻለው በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ቦታው ሰሜን ሆቴል አካባቢ በተለምዶ ‹‹ዳትሰን ሠፈር›› የሚገኙ ስድስት ባህላዊ የምሽት ቤቶች ታሽገዋል፡፡ አዋሳ ከተማ ውስጥም በተመሳሳይ
ምክንያት አምስት የምሽት ቤቶች መዘጋታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውም ምንጮቻችን ይሄንኑ አረጋግጠዋል፡፡
ምንጮቻችን እንደሚሉት “የምሽት ቤቶቹ የታሸጉት በአቶ መለስ ሞት ሐዘን ላይ እያለን ሙዚቃ ከፍታችኋል፤ ዘፈን አዳምጣችኋል” በሚል ሰበብ ነው ፡፡ በሌላ በኩል አምባሳደር ሲኒማ ቤት አካባቢ የሚገኝ አንድ ሬስቶራንት ሙዚቃ በመክፈቱ በአካባቢው የነበሩ ፀጥታ አስከባሪዎች ቤቱ ውስጥ ሆነው ሲዝናኑ የነበሩትን ከመደብደባቸውም በላይ ባለቤቱን በመደብደብ ይዘውት ሄደዋል፡፡” ሲሉ ምንጮቹ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡
መዝናኛ ቤቶች ዘፈን በማሰማታቸው ታሸጉ ከ11 ቀን በላይ ያስቆጠረው የአቶ መለስ ሞት ሀዘን ዜጎች ምንም ዓይነት ሙዚቃና የመዝናናት መንፈስ እንዳያሳዩ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጽእኖ ሲፈጠርባቸው የሰነበተ ከመሆኑም በላይ የወጣትና የሴቶች ፎረም፣ የየአካባቢው ጥበቃ ካድሬዎችና ደህንነቶች በየመኖሪያ ቤቱና በየንግድ ተቋማቱ እየዞሩ የንግድ ፍቃድን እየመዘገቡ “የሐዘን ልብስና ኮፍያ ግዙ፣ አደባባይ ወጥታችሁ አልቅሱ”  እያሉ ማስገደዳቸውም እንደቀጠሉ ይታወቃል፡፡ 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 10, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 10, 2012 @ 8:18 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar