www.maledatimes.com ከጉርድ ሾላ ሰአሊተ ምህረተ ቅድስት ማሪያም አራት ሚልዮን ብር እንደተዘረፈ ተገለጸ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከጉርድ ሾላ ሰአሊተ ምህረተ ቅድስት ማሪያም አራት ሚልዮን ብር እንደተዘረፈ ተገለጸ

By   /   September 10, 2012  /   Comments Off on ከጉርድ ሾላ ሰአሊተ ምህረተ ቅድስት ማሪያም አራት ሚልዮን ብር እንደተዘረፈ ተገለጸ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 45 Second

በአዲስ አበባ ከተማ ጉርድ ሾላ ከምትገኘው ስአሊተ ምህረተ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ቤተክርሰቲያን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ከአራት ሚልዮን ብር በላይ እንደተዘረፈ የመረጃ ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡ የውስጥ አዋቂ ምንጮቻችችን እንደሚሉት ‹‹ህንጻ ቤተክርስቲያኑ የአካባቢው ምዕመናን ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን አስተባብረው ያቋቋሙት ነው፡፡ ሆኖም ግን በቅርብ ጊዜ ተመድበው የመጡት የደብሩ አሰተዳዳሪ አባ ወ/ማርያም አድማሱ፣ የደብሩ ፀሐፊ መጋቢ ጥበበ ሩፋኤልና ታምራት ውቤ የተባሉ ተቧድነው ዝርፊያው እንዲፈጸም አድርገዋል፡፡ የአጥቢያ ምዕመናንም ‹‹በገንበዛቸውና በንብረታቸው
አያገባችሁም ተብለን ተቀምጠናል››፡፡ሲሉ አማርረዋል፡፡
የደብሩ አጥቢያ መምዕናን በተደጋጋሚ ዝግጅት ክፍላችን ድረስ የተለያየ የሰነድ ማስረጃዎችን ይዘው በመቅረብ እንዳስረዱት ‹‹ቤተክርስቲያኑን ባቋቋሙት መዕምናን ላይ ተደጋጋሚ ግፍ ተፈጽሟል፡፡የሙታን አጽም ተለቅሞ ወንዝ ተጥሏል፡፡በየትኛውም የሐገሪቱ ክልል ባሉ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኝ ምዕመን በሞት ሲለይ መንፈሳዊ አገልግሎት በነጻ በማግኘት የመቀበር መብት አለው›› የሚለውን
የቤተክህነት ህግ በመሻር ለመቃብር ብር 1.300 እንዲከፍል አድርገዋል፤ በሰንበቴ ማህበር ተደራጅተው የቦታ ጥበትን ለማስወገድ የሰሩትን ፉካ ብር 25ሺ ካልከፈላችሁ እንነጥቃችኋለን
ተብለው ተገደው እንዲከፍሉ ተደርጓል፤ ለጉዳይ ማስፈጸሚያ ተብሎ 90 ሺ ብር ወጪ ተደርጎ ተዘርፏል፤ ደብሩ ደረጃውን በጠበቀ የብረት ሽቦ እንዲታጠር ከንቲባው አዘዋል ተብሎ 70 ሺህ
ብር ወጪ ተደርጓል፤ ለፓትሪያርኩ ግብዣ ሰንጋና ለውስኪ መግዣ 70ሺ ብር ተብሎ ሂሳብ ከጉርድ ሾላ ሰአሊተ ምህረተ ቅድስት ማሪያም አራት ሚልዮን ብር እንደተዘረፈ ተገለጸ ተወራርዷል፡፡ በካዝና የነበረ ብር 400 ሺህ ብር ባክኗል፤ለፓትሪያርኩ ስጦታ ተብሎ 25ሺ ብር ወጪ ተደርጓል፡፡ ለሚፈፀመው ሙስናና ህገ ወጥ አሰራር አንተባበርም ያሉ ካናትና የሰበካ ጉባኤ አባላት ከደብሩ እንዲባረሩ ተደርጓል፡፡
አሁንም አይተባበሩንም ተብሎ የሚገምቷቸውን ምክንያት እየፈለጉ ጥቃት ይፈፀሙምባቸዋል፡፡ መጋቢ ጥበበ ሩፋኤል ቀደም ሲል ጋብቻ ፈፅመው ልጅ መወለዳቸው እየታወቀ ህገ ቤተክርስቲያኗን
በመጣስ ከቤተክርስቲያን ብር 300 ሺ ወጪ አስደርገው ፓትሪያርኩ በተገኙበት በጋብቻ ላይ ጋብቻ በተክሊል ፈጽመዋል፡፡ይህ ወንጀል ይፈፀም የነበረው ፓትሪያርኩን ሽፋን አድርገው መሆኑ
አሳዝኖናል፡፡›› በማለት ቅሬታቸውን ካቀረቡ በኋላ ‹‹የሚመለከተው የቤተክህነት ኃላፊዎች፣ሲኖዶሱና የመንግስት አካላት እንዲያውቅልን ጩኸታችንን አሰሙልን፡፡››ብለዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 10, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 10, 2012 @ 8:29 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar