www.maledatimes.com ኢሕአዴግ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሕወሓት ተወካይ ጋር አብረው ሃገር እንዲመሩ ሕግ ሊያጸድቅ ነው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢሕአዴግ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሕወሓት ተወካይ ጋር አብረው ሃገር እንዲመሩ ሕግ ሊያጸድቅ ነው

By   /   September 11, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 35 Second

zehabesha የአዘጋጁ ትዝብት፡ – ኢሕአዴግ አቶ መለስ ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ሙሉ ስልጣኑ በእጃቸው ባለበት ወቅት ለምክትል ጠ/ሚ/ሩ ምንም ዓይነት ስልጣን አልሰጠም ነበር። የወላይታው ተወላጅ አቶ
ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠ/ሚ/ርነቱን በሚይዙበት ወቅት ግን ምክትላቸው ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁትና አሁንም እንደምክትል ጠ/ሚ/ርነት እየሰሩ ያሉት ብርሃኔ ገብረክርስቶስን የስልጣኑ ተጋሪ
እንዲሆኑ በማሰብ አዲስ ሕግ ያወጣል።
አዲስ የሚወጣው ሕግ ሕወሓት ስልጣን እንዳያጣ፤ ሃይለማርያም ደሳለኝንም ነጻ ሆነው እንዳይሰሩ የሚያደርግ ነው። በዚህ ሰሞን የሚደረገው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ኃይለማርያም ደሳለኝን እና ብርሃኔ ገ/
ክርስቶስን ዋና እና ምክትል አድርጎ ይመርጣል። ኃይለማርያምም በአቶ ብርሃኔ ሕወሓት ስር ወድቀው ይሰራሉ። የኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ
የሰጡትን ቃለ ምልልስ እንደወረደ ያንብቡት።
አዲስ አበባ፡- «በጠቅላይ ሚኒ ስትር መለስ ዜናዊ ግንባር ቀደም መሪነትና ቀያሽነት የኢትዮጵያ ህዝቦች የጀመሩትን የህዳሴ ጉዞ ለማሳካት ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በላቀ ፍጥነት ከህዝብ ጋር ይሰራል» በማለት የግንባሩ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አስታወቁ። የኢህአዴግ ሊቀመንበርንና ምክትል ሊቀመንበርን የመምረጥ ጉዳይ ማን የበለጠ መስዋዕትነት ይክፈል የሚለውን የሚያመላክት ብቻ መሆኑን ገለጹ።
የግንባሩ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳለመከቱት፤ ግንባሩና የግንባሩ ሥራ አስፈፃሚ አካላት የአቶ መለስን አደራ ስንቅ በማድረግ የሀገሪቱን ህዳሴ ለማሳካት ቁርጠኛ ሆነዋል፤ ህዝቡ አቶ መለስ የተዋደቁለትን ዓላማ ለማስቀጠል ያለው መነሳሳትና ቁጭት ከፍተኛ መሆኑንም ሥራ አስፈፃሚው ተገንዝቧል። በዚህም ምክንያት «የግንባሩ ሥራ አስፈፃሚና መላው የኢህአዴግ አባላት የኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ በስኬትና በስፋት እንዲቀጥል ከፍተኛ ርብርብ ያደርጋሉ» ብለዋል።
ህዝቡ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስና የድርጅታቸውን ዓላማዎች ተገንዝቦ በቁጭት ትግላቸውን ለማሳካት ዝግጁነቱን ሲያረጋግጥ ምንም ጉድለት የለባችሁም ከሚል ስሜት ፀድቶ አለመሆኑን ኢህአዴግ እንደሚገነዘብ ጠቁመው፤ በተለይ ከመልካም አስተዳደር፥ ከአፈፃፀም ቅልጥፍናና ጥራት ጋር የተያያዙ ችግሮችን እንዲሁም የተጀመሩ የፍትህ ሥርዓት ማሻሻያና ሲቪል ሰርቪስ ማሻሻል ተግባሮችን ከተጀመረው ፍጥነት በላይ ለመፍታት ግንባሩ እንደሚረባረብ አስረድተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩንና የሀገሪቱን ራዕይ ለማሳካት ግንባሩ ሙሉ ዝግጅት፥ አቅምና ቁርጠኝነት እንዳለውም ገልጸዋል።

«ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህይወት ዘመናቸው ያለ መታከት ብዙ በመስራት በርካታ ተተኪዎችን አፍርተዋል» ያሉት አቶ ሬድዋን «በኢህአዴግ መበላላት፥ መጎሻሸም፥ መገፋፋት የለም፤ ተተኪን የመምረጡ ጉዳይ ማን ይበልጥ ያስተባብር በሚለው ላይ ያነጣጠረ ነው» ብለዋል። ግንባሩ በስልጠናና ተግባር ልምምድ በታገዙ የእውቀት ሽግግሮች የተገነቡ መሰረታዊ የድርጅቱን እሴቶች የማስቀጠል አቅም እንዳለው ተናግረዋል።ለግንባሩ የመተካካት ጉዳይ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነትን የመጫንና ማን አስተባብሮ ይሂድ የሚለውን ከመግለፅ ውጪ በድርጅቱ ባህል ስልጣን ምቾትና ድሎት አይደለም » በማለት በአፅንኦት ገልጸዋል።የድርጅቱንና የኢትዮጵያ ህዝቦችን ጥቅም ከማስጠበቅ አኳያ ግንባሩ የሚጠመዘዝ እጅ እንደሌለው ጠቁመው፤ በማንም ኃይል የማደናቀፍ ተግባር የህዝቡን ፍላጎትና ዓላማ ከማሳካት ወደ ኋላ እንደማይል አስረድተዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 11, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 11, 2012 @ 5:17 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “ኢሕአዴግ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሕወሓት ተወካይ ጋር አብረው ሃገር እንዲመሩ ሕግ ሊያጸድቅ ነው

  1. How can two people be a leader at the same time. This is in contradiction to leadership principles. According to leadership principles their shoud be Unity of Command. Subordinates can not be responsible for two people at the same time.There should alawys be one leader to be responsible for anything.I guess this will crate a leadership crises soon. If one person receive conflicting order from his/her boss which boss s(he) has to obey?

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar