www.maledatimes.com የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ በሌለበት ጄነራሎች ተሾሙ ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ በሌለበት ጄነራሎች ተሾሙ !

By   /   September 12, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 30 Second

በህገ መንግስቱ  ረቂቅ አዋጅ መሰረት የጄነራሎችን በእጩነት ማቅረብ የሚቻለው ከመከላከያ ሚንስትር ውስጥ ከተቋቋመው ኮሚቴ ለጠቅላይ ሚንስትሩ በማቅረብ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትሩ ደግሞ አስፈላጊውን ጥናታዊ ከተመለከቱ በኋላ ለሃገሪቱ አስተዳደራዊ መንግስት ወይንም ፕረዚዳንት እጩዎቻቸውን በማቅረብ የሹም ሽር የሚከናወነው  በሃገሪቱ ርእሰ ብሄር ከሆኑት ፕረዚዳንት  የሚደረግ ህግ የነበራት ሃገር  የነበረችው ኢትዮጵያ እስከ 1993 አም. በዚህ አስተዳደራዊ ስርአት ትተዳደር ነበር ።በ1993 አ.ም በተፈጠረው የህወሃት ክፍፍል ጠ/ሚንስትሩ በፓርቲው መሃከል ጣልቃ በመግባት ለራሳቸው በሚመቻቸው መልኩ አገሪቱን ለማሽከርከር እና የሚፈልጉትን ሰው በሚፈልጉት ቦታ ለማስቀመጥ  2 ጄነራሎችን አባረሩ እነዚህም  ሜ/ጀነራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ እና አበበ ተ/ክለሃይማኖት (ጆቤ) ሲሆኑ ፣እነዚህን ጀነራሎች ካባረሩ በኋላም  ከሃገሪቱ ርእሰ ብሄር  ከነበሩት ፕረዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር በተደረገው ውይይት እና በተፈጠረው አለመግባባት ጠ/ሚንስትሩ ስህተታቸውን  ከማረም  ይልቅ የሃገሪቱን ህገ መንግስት እንደ ገና የጠቅላይ እዙ እና ሹም ሽር በእሳቸው (በጠ/ሚንስትሩ )እጅ እንዲዞር አደረጉ ።

ያገሪቱ ፕረዚደንት ማባረር እና ስልጣን ሰጥቶ መሾም ሲገባው  የቀድሞውን ፕረዚዳንት ዶ/ነጋሶ ጊዳዳ ይህንን ባለማድረጋቸው  ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር በመነጋገርጠቅላይ ሚንስትሩ ህግ በመጣሳቸው እስከ መጋጨት ደርሰው  እስከ ስልጣን መልቀቂያ ድረስ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው ። ሆኖም ዛሬም ጠ/ሚንስትሩ በህይወት በሌሉበት እና እንደገና የቀድሞው ጠ/ሚንስትር ሽረውት በእጃቸው እንዲሆን ያደርጉት የሹም ሽር ሂደት ዛሬ ደግሞ በሃገሪቱ ፕረዚደንት ሊከናወን ችሏል ።ተጠሪነቱም በጠቅላይ ሚንስትሩ በኩል የነበረው የመከላከያ ሚንስትር ኮሚቴ አባላትም ተግባራቸው ምን ደረጃ እንደድረሰ ሳይታወቅ የህገመንግስቱ መሻር እና የስልጣን መበራከት ጀምሯል:: የሃገሪቱ ህገ መንግስት የተቀመጠው ለይስሙላ ይሆን እንዴ?ለምንስ እንደገና የሃገሪቱን ህገ መንግስት በመጣስ ጀነራሎችን የማእረግ ሽልማት ሊሰጣቸው ቻለ ?በአገሪቱ ህገመንግስት መሰረት 34 ኮሎኔሎች በብራጋዴር ጄነራል ማዕረግ ፣ ሶስት ብራጋዴር ጄነራሎች ደግሞ በሜጀር ጄነራል ማዕረግ ተሹመዋል፡፡ አብዛኞቹም የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ከሁለት ወገን የዘር ሃረግ ያላቸው ናቸው ፣ከእነዚያም ውስጥ የትግራይ ተወላጆች እንደሚበዙ ከሪፖርቱ ተገልጿል

በተሰጠው ከፍተኛ ወታደራዊ ሹመት መሰረት ብራጋዴር ጄነራል ሆነው የተሾሙት ብራጋዴር ጄነራል ያይኔ ስዩም፣ብራጋዴር ጄነራል አታክልቲ በርሄ ፣ብራጋዴር ጄነራል ፍስሃ በየነ፣ ብራጋዴር ጄነራል ጉዕሽ ፅጌ ፣ ብራጋዴር ጄነራል ገብረኪዳን ገብረማሪያም፣ብራጋዴር ጄነራል ማዕሾ ሃጎስ፣ብራጋዴር ጄነራል ገብሩ ገብረሚካኤል፣ብራጋዴር ጄነራል ማሸሻ ገብረሚካኤል፣ ብራጋዴር ጄነራል አብረሃ አረጋይ፣ ብራጋዴር ጄነራል ደግፊ ቢዲ ናቸው፡፡

እንዲሁም ብራጋዴር ጄነራል አስካለ ብርሃነ፣ ብራጋዴር ጄነራል ሀለፎም እጅጉ፣ ብራጋዴር ጄነራል አብርሃ ተስፋዪ፣ ብራጋዴር ጄነራል ሙሉ ግርማይ፣ብራጋዴር ጄነራል ወልደ ገብርኤል ባቢ፣ብራጋዴር ጄነራል ፍሰሃ ኪዳነ ማሪያም፣ብራጋዴር ጄነራል አሰፋ ገብሩ፣ብራጋዴር ጄነራል የማነ ሙሉ፣ብራጋዴር ጄነራል ገብረመድህን ፍቃዱ፣ብራጋዴር ጄነራል ታረቀኝ ካሳሁን፣ብራጋዴር ጄነራል አስራት ዶኖይሮ፣ብራጋዴር ጄነራል ጥጋቡ ይልማ የማዕረግ ዕድገቱ ከተሰጣቸው መካከል ናቸው፡፡

በተመሳሳይ እንዲሁ ብራጋዴር ጄነራል ዘውዱ በላይ፣ብራጋዴር ጄነራል ኩምሳ ሻንቆ፣ብራጋዴር ጄነራል አጫሉ ሸለመ፣ ብራጋዴር ጄነራል ሹማ አብደታ፣ብራጋዴር ጄነራል ድሪባ መኮንን፣ብራጋዴር ጄነራል ደስታ አብቺ፣ብራጋዴር ጄነራል አቤል አየለ፣ብራጋዴር ጄነራል ይመር መኮንን፣ብራጋዴር ጄነራል ከድር አራርሳ፣ብራጋዴር ጄነራል ይብራህ ዘሪሁን፣ ብራጋዴር ጄነራል ኩመራ ነጋሪ፣ብራጋዴር ጄነራል ዱባለ አብዲ ናቸው፡፡

ሜጀር ጄነራል ሆነው የተሾሙት ደግሞ ሜጀር ጄነራል መሐሪ ዘውዴ፣ ሜጀር ጄነራል ሐሰን ኢብራሂምና ሜጀር ጄነራል መሰለ በለጠ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 12, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 12, 2012 @ 3:12 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ በሌለበት ጄነራሎች ተሾሙ !

  1. hagerachehun bekinenet ena betamagnet eski ageligelu lenanite hiwo sayihon lemitemerut serawit ena hizb hiwot kidemia setu yane hulum neger yetekana yihonal achenafim tehonalachehu jemirut metifowu yiwegedal mengedum kena yihonal semachehum kemekabir belay kef yilal bergit kelal demo aydelem gin zare nege satelu jemirut ena milionochin aselefu selam.

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar