www.maledatimes.com የመለስን ነፍሰ አይማር አልልም (ኪዳኔ ገ/እግዚአብሄር ለማ ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የመለስን ነፍሰ አይማር አልልም (ኪዳኔ ገ/እግዚአብሄር ለማ )

By   /   September 12, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:13 Minute, 24 Second

የአቶ መለስ ስርአተ ቀብር ሲከናወን ፎቶ ማለዳታይምስ

እንዳው የምሰማወና  የማዬው ነገር ያሳዝነኛል ያሰገርመኛል  .. ይህንንም ያልኩበት ምክናያት ያአቶመለስ የስልጣን ዘመን በቀብር ስነስረአታቸው ላይ ሆነ በአንዳንድ የሚድያ አውታሮቸ ስለመለስ  የነገሩን ገድሎቸ  ሰውየው እነኘህ ኢትዮጽያኖች ሳንሆን መስካሪዋቻቸው የውጭዎቹ አሳምረው ሲናገሩላቸው ጉድ ነው ያልኩት   የኛው መለስ መሆናቸውን ተጠራጠርኩ

ጎበዝ እኔ እደሰማሁትና እንደገባኘ አቶ መለስ በኢትዮጵያ የዘረጉት ዲሞክራሲያዊ ስረአት እና የኢኮኖሚ እድገት በተለይ የሱዛን ራይዝ አገላለጽ  ራሳቸውም አገር የታየ አይመስልም  ታዲያ ይህ ብቻ መቿ የወያኔ ጉችሎችና ያአቶ መለስ ባለቤት ምስክሩ ህዝብ ነው የመለስ ራእይና ፖሊሲ እስካልተበረዘ በቀጣይ አለንላቸሁ  እያሉን ነው ፤ እኔም ይህንን ስሰማ አንድ ነገር ልል ፈለግሁ፤

እኔ የምጀምረው ወያኔን \የመለስን\መንግስት በደንብ ካወቅሁበት ና በግልጽ  ስራቸውን ካየሁበት ጊዚ ይሆናል በምርጨ 97 ፤ ከዚያ በፊት አለማወቄ አይፈረድብኘም እኔም እደሌላው ህዝብ መረጃ ስለሌለኝ ፤ ራሴን ያወኩት ያኔ ነበር ።ምን ያህል በወያኔ ስርአት አገራችንና በባዶ ና በዘፈቀደ የምትመራ ሀገር መሆኗን ያየሁበትና ህዝቡም ምን ያህል ለዲሞክሪሲያዊ ስርአት  መምጣት ፍላጎቱ የተነሳሳበት ጊዚ  እንደነበር ሳስታውስ መለስ ማነው­፤ ለሚለው ትንሽ የበኩሌን ልል ወደድኩ።

አቶ መለስ በምርጫ   97 በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት ወይም ለማቆም ፍጹም እንከን የሌለው ምርጫ በሃገሪቱ ለማካሄድ ኢህአድግ በቆራጥነት መነሳቱን አወጀ።ለውጪ መንግስትም ለፈፉ። የሚድያ አውታሮችም  ነፃ ጋዜጦችም በነጻነት እንዲጽፉ  እንዲያወያዩ በነጻነት እንዲሰሩ አበሰሩ።“ብራቮ ብራቮ መለስ“ ተባለለት።ድራማው ተጀመረ ።ሕዝቡም ድራማውን በቴሌቭዥን መስኮት ይከታተለው ጀመር ።ውሸትና እውነት ተፋጠጡ።ክርክሩም ጦፎ ቀጠለ። በውሸቱ ድራማ እውነት ተገለጠ። እያንዳንዱ የወያኔ ባለስልጣንን የፈተነ የክርክር ድራማ “አይነጋ መስለሏት ምን…….“ እንደሚባለው ተረት የወያኔ መንደር ሲተራመስ ያኔነው እራሴን ያወኩት ….የወያኔን ባዶነትና ሙስና የሃገሪቱን መፈራረስ እንዲሁም ሕዝብና ሃገር ወደ መከ-ራ እየተጓዙ እንደሆነ የገባኝ።በስተመጨረሻም ስልጣን ለማስተላላፍ ማሰባቸዉ ለነሱም ለሃገርም ይበጃል ሕዝብ ደመደመ የወያኔም ድንጋጤ በረታ አካኪ ዘራፍም አልፎ አልፎ ተጀመረ።“አንቺው ታመጪዉ አንቺው ታሮጪው“እንዲሉ የቴሌቭዥን መስኮት ተዘጋ የምረጡኝ ዘመቻ ተጀመረ የድጋፍ ሰልፍ ተወጣ የወያኔ የድጋፍ ሰልፍ ቀደመ መለስ ከሚናገሩበት መድረክ ወርደው ሕዝቡም መካከል ገብተው ለመተቃቀፍ ከጀላቸው“ይህንን ሕዝብ ይዘን“ብለው ሲቃ ተናነቃቸው እናም ሲደንሱ አደሩ።

ከዚያው ማግስት የቅንጅት አመራሮች የድጋፍ ሰልፍ ጠሩ መላው የ አዲስ አበባ ሕዝብ እሳቻው ደገፉኝ ያሏቸው ሳይቀሩ ተ አምር አሳዩ ሳይውል ሳያድር የሆነውንና የተደረገውን አይተው መለስና መሰሎቻቸው ተመልሰው ተሸበሩ ግራ ቢጋቡም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው በመለስ የበላይነት የሚመራ የወያኔ አመራሮች የሕዝቡን ድምጽ ለመቀማት እስትራቴጂ ቀየሱ ምርጫው ተጀመረ መላው የ ኢትዮጰያ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ድምጽን ሰጠ በ አዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ተሸነፋ ወከባውም ተጀመረ ከክልል ጣቢያወች የምርጫ ውጤት አብዛኛው ተሰማ ቅንጅት በሰፊ ልዩነት ማሻነፉ እየተነገረ አቶመለስ ስልጣን የሰጡትን የምርጫ ቦርድ መብት ጥሰው  በክርክሩ በተዋረዱበት ቴሌቪዠን ብቅ ብለው አሸንፈናል  እንግዲህ ጣት ብታወጡ ጣት ይቆረጣል ብለው አረዱን አንድ በሉ  ፤ በዚህም አልበቃ ድምፃን ተቀማሁ ብሎ ተቃውሞ የወጣውን ህዝብ በጥይት በመምታት ከሁለት መቶ ሰዎች በላይ አቶ መለስ አስጨፈጨፉ እንከንየለሽ  ሁለት አትሉም ፤ በዚህም አልቆመም  የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዋችና አባላቶች እያደኑ ማሰር ጀመሩ እንከን የለሽ ምርጫ ሰዎስት አትሉም ፤የመለስን ነፍስ አይማር አልልም፤ ይህም ሲደረግ አሁን የሚመሰክሩላቸው ሰዎች አልሰሙም አላዩም ማልት ነዉ፤አቶ መለስ ታዲያ ተሳክቶላቸው ከትልልቅ ጉድፎቻቸው ትንንሹን አወጡና ትልልቁን ኩል እያኸኸሉ  እያሳመሩ ቀጠሉ 2002 አስቂጘ  በሆነ ድምጽ 99.9% አሸንፈናል ሲሉ ኢትዮጽያኖች ብቻ ሳንሆን አለም የሳቀበት  ነበር

ታዲያ መለስ በሙስና እና በቅጥፈት ከበሮ እያስደለቁ አፋኝ  ፖሊሲአቸውን ለመተግበር ያቋቋማቸውን የኢኮኖሚ ተቋማት ፤ ከህዝብ  የዘረፉአቸውን  ሀብቶች  የኑሮ ውድነት ካቅሙ በላይ ሆኖበት መኖር ያቃተውን የህብረተሰብ ክፍል በገንዘብ እርጥባንና  ድጎማዎች በማታለል ሲጠሩት አቢት ሲልኩት ወዲት እዲል ያደረጉት ወጣትና ሊላም የህብረተሰብ ክፍል ከጘናቸው ያሰለፉ መስላቸው ቀጠሉ፤በሀገሪቱ የዘር ልዩነትን በመፍጠር በጋቢላ፤ባኦሮሚያ፤ባፋር በሊሎችም ቦታዎች የተገደሉት ከቀያቸው የተፈናቀሉት

የፍትህ ስርአቱ  በሳችው የሪሞት ኮንትሮል  እደተፈለገ የሚታዘዝ በመሆኑ ማሰር ያስፈለጋቸውን ያስራሉ ምህረት የሚያረጉለት ያረጉለታል፤  ነፃ-ጋዚጠኞች፤ ተቀዋሚ ፣ አመራሮችና አባሎች ሲታሰሩ ከሀገር ሲሰደዱ ኢትዮጵያኖች  አናውቅም ያለም ህብረተሰብ አያውቅም ታዲያ መለስ የትኛው ናቸው እንደዚያ ገድል የሚተረክላቸው? ፤ ህዝቡን ነጻነት እጦትና የኑሮ ውድነት አንድቀን እንደ ቅንጂቱ አመጽ ይፈነዳል ብለው ያሰቡት መለስ በተለይ አዲስ አበባ ላይ ያፈና መረባቸውን በመዘርጋት ካድሪዎቹን/ፎረሞቺን/ እንደ ፋብሪካ በማምረት  ከምርጫ 97 በመላው ከክፍለሀገር 125.000 ወጣቶቺንና  ሲቶች መልምለው በማስገባት አዲስ አበባ ውስጥ ደግሞ 250.000 በድምሩ ከዋናዎቹ/ከቀደሙት/ በተጨማሪ 400.000 የሚጠጋ ደጋፊ/አባል ሲያደርጉ ይህ በኑሮ ውድነት ምንም አማራጪ ያጣ  የህብረተሰብ ክፍል ውሎ አድሮ ሲሞቱ አዛኘና አልቃሽ መሆኑ አልቀረም፤

ታዲያ መለስን  ከእኛ ከባለቤቶቹ በላይ አዋቂወቸ ሆነው ስለ መለስ በጎ ምግባር የሚደሰኩሩልን ፡ስለ እኛ አገሩመለስ ነው ወይስ እኛ ማንነታቸውን ሳናውቃቸው እነርሱ በመለስ የማንበርከርኪያ ምላስ እንደታለሉና እንደደነቆሩ ቀሩ  !

ወገኔ እኔ“ የመለስን ነፍስ ይማር በሃሰት የሚመሰክሩላቸውን ግን አይማር እላለሁ“

ከዚህ በሗላ ወያኔን በቃ ! ልንለው ይገባለል „“ ሞኝ ሰው በ እባብ ሁለቴ ይነደፋል አሉ አንድ ጊዜሳያይ እንደገና ሰወችን ሰብስቦ

እዚህ ጋር ነው የነደፈኝ ብሎ ቦታ ሲያሳይ“ ስለዚህ ሁላችን የወያኔን ፖሊሲና ራእይ ይቅር አይቀጥልም ማለት መቻል አለብን።

 

Kidane  Gebregziabher  Lema

German  Kitzingen

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 12, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 12, 2012 @ 4:21 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With: ,

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “የመለስን ነፍሰ አይማር አልልም (ኪዳኔ ገ/እግዚአብሄር ለማ )

  1. It’s new year, our strategy has to be enforced with a new device.

    We have to wake in this coming month the ocnscioiusness of the farmers and general public. To refuse pecefuly from being an instrument to woyane and to protest the selling of our land, the killing of Afar people, Gambela, Sidama the dislocation of Amhara, the killing og Oromia.

    If the general population refuse to collaborate and protest the woyanes has no choice and international corporation will not get involved in anstable country and pour their money. The diaspora can play a big role in stoping the foreign aid by exposing the regime on press freedom and being a totalitarian regime.

    We have to follow the money that’s flowing outside the country and block and expose those woyane member buying businesses in illegal money in both europe and america and the killers has to be exposed for the American government. Before they know it they have no other way but fall when they can not finance their military they have to run and we’ll never give up to hunt them down and expose them through International tribunal court. If meles died his wife and the rest of the regime is still responsible for all absolut inhumane treatment of Ethiopian people torture and comitting genocide.

    We should not rest before they all are set to be an example of African dictators….this has to be our new year resolution. We can until the day I die I’ll not give up this I can promise each and every brutal woyanes for killing innocent Ethiopian in your dungeon

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar