www.maledatimes.com ዶ/ር ያዕቆብ በኢትዮጵያ የ‘አሰብ ወደብ ቀን’ ለመሰየም አስበዋል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዶ/ር ያዕቆብ በኢትዮጵያ የ‘አሰብ ወደብ ቀን’ ለመሰየም አስበዋል

By   /   September 12, 2012  /   Comments Off on ዶ/ር ያዕቆብ በኢትዮጵያ የ‘አሰብ ወደብ ቀን’ ለመሰየም አስበዋል

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 18 Second

በዘሪሁን ሙሉጌታ (ሰንደቅ ጋዜጣ)

በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት የሕግ ባለሙያ የነበሩትና የቀድሞው ቅንጅት አመራር አባላት አንዱ የነበሩት ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም በኢትዮጵያ የ“አሰብ ወደብ ቀንን” ለመሰየም ማቀዳቸውን አስታወቁ። ምሁሩ “አሰብ የማን ናት” ከሚለው መፅሐፋቸው ያገኙትን ገቢ ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው ወገኖች ለሁለተኛ ጊዜ አበርክተዋል።
ዶ/ር ያዕቆብ ከመፅሐፉ ሽያጭ ያገኙት ገንዘብ ለሁለተኛ ጊዜ ያበረከቱት ባለፈው እሁድ ጳጉሜ 4 ቀን 2004 ዓ.ም ፒያሳ በሚገኘው ሚትማ ሬስቶራንት ውስጥ በተዘጋጀ የምሳ ግብዣ ላይ ነው። በዕለቱ ወላጅ አልባ ለሆኑ ሕፃናት፤ ጧሪ ለሌላቸው አረጋውያን፣ ጠያቂ ለሌላቸው የሕግ ታራሚዎች እና ለሌሎች ወገኖች ለእያንዳንዳቸው 500 ብር ለግሰዋል። የዛሬ ዓመት በተመሳሳይ ሀምሳ ለሚሆኑ ተረጂዎች ምሣ ግብዣና ለእያንዳንዳቸው 1 ሺህ ብር አበርክተዋል።
ዶ/ር ያዕቆብ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ እስካሁን ከመፅሐፉ ሽያጭ የተገኘው ብር 200 ሺህ ለበጎ አድራጎት ተግባር መዋሉን ገልፀዋል።
“እኔ እራሴ ጡረተኛ ነኝ። ነገር ግን የመፅሐፉ ሽያጨ ወደኪሴ እንዳይገባ የፈለኩበት ዋና ምክንያት በታሪክም ሆነ ባለንበት ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ ወደብ ከማጣት በላይ በደል ተፈፅሟል ብዬ ስለማላስብ በኢትዮጵያ ችግር ላይ እኔ መጠቀም ስላልፈለኩ ነው” ብለዋል።
ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ሀገር እንድትሆን በመዳረጓ በየቀኑ 6 ሚሊዮን ዶላር ለጅቡቲ ትከፍላለች ያሉት ዶ/ር ያዕቆብ፤ሀገሪቱ በገንዘብ በኩል እያጣችው ካለው ሀብት በተጨማሪ በፀጥታ፣ ደህንነትና ሉአላዊነቷ ላይ አደጋ መጋረጡ እንደሚያሳስባቸው ገልፀው የአሰብ ጉዳይ ከኢትዮጵያውያን አዕምሮ እንዲወጣ አልፈልግም ብለዋል።
“አሰብ የማን ናት” የሚለው መፅሐፍ በሀገር ውስጥ 15 ሺህ ቅጂ መታተሙን በውጪ ሀገር ደግሞ ሁለት ሺህ ቅጂ መታተሙን የገለፁት ዶ/ር ያዕቆብ ለወደፊቱም መፅሐፉ በተሸጠ ቁጥር ተረጂዎችን ምሳ መጋበዝና የኪስ ገንዘብ የመለገሱ ሂደት እንደሚቀጥልም ዶ/ር ያዕቆብ አያይዘው ገልፀዋል።
በኖርዌይና በስዊዲን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዓመት አንድ ቀን “የአሰብ ወደብ ቀን” በሚል ቀኑን ታስቦ እንዲውል ማድረግ መጀመራቸውን ያስታወሱት ዶ/ር ያዕቆብ በኢትዮጵያም በተመሳሳይ ዕለቱን ለማሰብ እቅድ እንዳላቸው ገልፀዋል። የአሰብ ቀን ታስቦ በሚውልበት ዕለት ምሁራን ስለ አሰብ ወደብ ውይይት እንዲያደርጉ ይደረጋል። በአሜሪካን አገርም ተመሳሳይ ዝግጅቶች እንዲደረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 12, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 12, 2012 @ 5:32 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar