www.maledatimes.com የሐሰት ድሪቶ የእውነትን ካባ አይሸፍንም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሐሰት ድሪቶ የእውነትን ካባ አይሸፍንም

By   /   June 1, 2014  /   Comments Off on የሐሰት ድሪቶ የእውነትን ካባ አይሸፍንም

    Print       Email
0 0
Read Time:13 Minute, 46 Second

የሺህ ኪሎ ሜትር መንገድ በአንድ እርምጃ ይጀመራል እንዲሉ በጥቂት ጔደኛሞች መሰረት የተጣለለት የስፖርት ፌደሬሽን አድጎ እና ገዝፎ የኢትዮጵውያን መገናኛ እና መሰባሰብያ ብርቅዬና ብቸኛ ድርጅት ለመሆን መብቃቱን በኩራት የምንዘክርለት፣ የምንመሰክርበት፣ የምንመካበትና እንደ አይናችን ብሌን የምንጠብቅለት ደረጃ
ላይ ለመድረሱ ታሪክ ምስክር ነው።
አንድ ድርጅት በሂደትና በእድገት ብዙ መሰናክሎችን እንደሚያልፍ፣ ሳንካዎች እንደሚያጋጥሙት፣ አስከፊ፣ አስደሳችና አሳዛኝ የእድገት ጎዳናዎችና መሰናክሎች እንደሚያልፍ ዕሙን ነው። ከአጭር እቅድ ተነስቶ ረጅም ግቦችን እንደሚያሳካ ሁሉ ፌደሬሽናችንም በእነዚህ ሂደቶች ውሰወት ሾልኮ ለማለፍ የረዱት የአያሌ ውድና ብርቅዬ ኢትዮጵያውያን አስተዋፅኦ ነው። በመሆኑም የተከፈለው ክቡር መሰዋእትነት በአብዛኛው ዜጋችን አንቱ የሚያሰኝውና የኢትጵያዊነት የፍክር ካባ ለመላበስ አብቅቶታል።
ፌዴሬሽናችን በረዝሙ ታሪኩ በውስጡ የነበሩትን ኢ-ዲሞክራሲያዊ አሠራሩን እንዲያሻሽል ከአምባገንነትና  የግለሰብ ግላዊ የበላይነት ተላቅቆ ውኃዳዊ አሠራርን እንዲላበስ ለረዥም ዓመታት የተካሄዱት ትግሎች በመጨረሻ ፍሬ አፍርቶ ሰፊውና ብዙሃኑ ኢትጵያዊ የኔ በሚለውና በሚያምንበት ሕዝባዊ አሠራር ሥር እንዲመራ እና
እንዲራመድ ባደረገው ወሳኝ ትግል ገንጣይና ከፋፋዮችን አግልሎ፣ አባሮ እና እርቃናቸውን አስቀርቶ፣ ገንዘብ ፍቅርንና ኢትዮጵየዊነትን እንዳማያሸንፍ በግላጥ አስመስክሮ፣ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት በአፍራሾችና በተገንጣዮች መቃብር ላይ የኢትዮጵያዊነትን የበላይነት ባንዲራ አውለብልቧል ዳግም እንዳይመለሱ መሰሪ ተግባራቸውን ብቻ
ሳይሆን አላማቸውንም ቀብሮ አፈር አልብሷል።
ለዚህ ምስክሩ ቀብራቸውን በዳላስ፣ ሙት አመታቸውን በሜሪላንድ በተካሄዱት አመታዊ ውድድሮች በነቂስ
በመውጣት ኢትዮጵያውን በአንድነታችን ላይ ምን ያህል ቀናዊ መሆናችንን በማስመስክር ሙሿቸውን አውርዶላቸው
በባዶ (ወና) ስታዲዮም ለቅሶ ቤት እንዲቀመጡ አድርጓቸዋል።
ይህ ድል የጥቂት ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ ወይንም የቡድን መሪዎችና ስፖርተኞች ሳይሆን፤ በዘር በሃይማኖት፤
በጎሳና በፆታ ሳይከፋፈልና አንድ አካልና አንድ አምሳል በመሆን እምቢ ለአፍራሾች፣ እምቢ ለከፋፋዮች እምቢኝ
ለገንጣዮች በማለት “ሆ” ብሎ ማንነቱን ያስመሰከረበት የመላው ኢትዮጵያ ድል ነው። የድሉም ባለቤት እርሱ ብቻ
ነው።
ይህ አደባባይ የወጣ ፀሓይ የሞቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ዘላለማዊ ታሪክ ሆኖ እያለ፤
ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ጥቂት ማንነታቸውን ደብቀው በድህረገፅና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የበሬ ወለደ
አሉባልታ ውዥንብሮች እና የስም ማጥፋትን የከፈቱ ግለሰቦች የሚረጩት በማር የተለወሰ መርዝ” ዘመቻ አበው
አባቶቻችን “ሳይቃጠል በቅጠል” እንደሚሉት ብሂል በአጭር ካልተስተካከሉ የሚያስከትለውን አፍራሽ ጉዞ በማጤን
የበኩሌን ጥቂት ለማለት ተገድቻለሁ።
አሁንም በፌዴሬሽኑ ውስጥ የሚተገበሩተንና በመከናወን ላይ የሚገኙትን ዲሞክራሳዊ የአሠራር ባህሎችንና
ውስጣዊ የአሠራር ውጣ ውረዶች “ሀ” ግዕዝ “ለ” ግዕዝ እያልኩ በመዘግዘክ ገበናቸውን አደባባይ በማውጣት
ሰድቦ ለሰዳቢ አሳልፎ እንደመስጠት ሰለሚቆጠርና ፍላጎቴም ባለመሆኑ አብይ በሆነው የውስጣዊ ትግሉ አንኳር
የዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ጥስት ላይ አስረግጬ ለመዘከር እወዳለሁ። ለብዙም አመት የፌደሬሽኑን የውስጥ
አሠራር በቅርብ ሰለማውቀው ይህቺ ፅሁፌ የእውነተኛ መንገድን የተከተለች ነች ብል አንባቢዬን ማሳጣት
አይሆንብኝም ብዬ አምናለሁ።
በመሰረቱ በፌዴሬሽኑ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ አሠራርን ለማስፈንና ማዕከላዊነትን ለማዳበር የተደረገው
ትግል ጥቂት የጠገቡ አንበሶችን አስወግዶ አዳዲስ የተራቡ አንበሶችን ለመተካት አይደለም አልነበርምም። ትግሉ
ጥቂቶች ለብዙሃን ውሳኔ ተገዢ የሚሆኑበትን የአሠራር ባህል ለማንገስ እንጂ የተደረገው ትግል እኔ የምለውን
“ስሙና ፈፅሙ” የሚሉ አምባገነኖችን ለመፍራት ሳይሆን የብዙሃኑ ኃሳብና ውሳኔ ተቀብለው ቃላችሁ ቃላችን
ውሳኔዎችን ውሳኔያችን የሚሉ አመራሮችን ለመትከል ነበር እንጂ።

ESFNA’S MORAL CRISIS
Consequence of Libel and
Slander on the future of ESFNA
አዲስ አለማየሁአለመታደል ሆኖ በየጊዜውና በየስርዓቱ በሃገራችን እንደታዩት የስርአት ለውጦች የደርጉ ስርዓት
ተቀናቃኞቹን የፔትሮ ዶላር ደላላ ተስፋ ለዘውድ የገንጣዮች ቅጥረኛ ወያኔ ተቀናቃኞችን ለማሸማቀቅ
ፀረ ልማትና አሸባሪ እንደሚለው ሁሉ በፌዴሬሽናችንም ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች አምባገነኖች
ስህተታቸውን አርሞ ከመቀበል ይልቅ ኃሳብና ጥያቄ አቅራቢዎችን ወያኔ የሚል ታፔላ ለመለጠፍና
ስም ማጥፋት ሲንደረደሩ ይስተዋላሉ ይህም በእኔ እምነት በመሸታ ቤት የተገዛ ጦር ቢወረውሩት
አድፍድፍ እንዲሉ አይነት ነው።
ወያኔ የሚለው ቃል በእኔ እምነት በራሱ ፀያፍ ነው ከፀያፍም በላይ ሊጠቀስለት የሚገባ ቃል
ቢኖር የሚያሳፍር ስምም ግብርም ነው ይህን የምንለው በኢትዮጵያ ሉአላዊነት ክብርና አንድነት
ላይ የፈፀመውን ግብር ውጤት በማስመልከት ነው ሰለሆነም ልመና ሳይሆን ሰርቶ መከበርን
መረሃቸው ላደረጉ በኢትዮጵያ አንድነትና ልዑላዊነት ለሚያምኑ ሰዎች ሊለጠፍ በታፔለነትም
ሊንጠለጠልላቸው የማይገባ ቃል ሰለሆነ ለፃሐፊዎች ማፈር ብቻ ሳይሆን ሰለነሱ እንሸማቀቅላቸዋለን
በጣም የሚየሳዝንነው ደግሞ የዚህ ፌዴሬሽን ዋልታና ምልስ የሆኑትን ክለቦች ነጥሎና አላማ
አድርጎ የተሰነዘረው ወቀሳ ነው።
አንዱን አኩሎ በማስዋብ ሌላውን አጨልሞና አጭርቆ በማቅረብ ከተዘረዘሩት የስም ማግደፍና
ማጥፋት ዘመቻዎች ላይ የተዘረዘሩት ከላይ በዝርዝር ለተጠቀሱት ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት
አሠራር የሚያምኑ ክለቦች በተጨማሪ በፌዴሬሽኑ የግንባር ስጋ የሆኑት ዋሽንግተን ዲሲ ስታርና
እና ሎስ አንጀለስ ስታርን በተናጥል አልሞ የተተከለው የጥላቱ ቃላት የፃሓፊዎች መሰሪና ከፋፋይ
ተግባር በግላጥ አደባባይ ያወጣ በመሆኑ “ኪራራላየሶን” ከማለት ሌላ ቃላት መደርደሩ አላስፈላጊ
ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
ባይሆን አፍርሶ መክፈልን ለርካሽ ድምፅ ፍለጋ አንዱን ክለብ በሌላ መሰረሰሩን አግላይነትንና
ቆረጦ ማጥፋትን ጀብደኞች ተወት አድርገው ለዘላቂው አንድነት አብሮ እድገት ብልፅግናና ለአንድ
ኢትዮጵያ የበላይነት በጋራ ለመስራት መተባበርን አንዲመርጡ ምክራችንን እንለግስላቸዋለን።
ለመሆኑ ፃሀፊዎቹ የሎሳንጀለስ እና የዲሲ ቡድን በአጠቃላይ ድምሩ 50% ወይንም
ለ 15 አመታት ያህል የፌዴሬሽኑ ዋንጫ ባለቤት ቡድኖች አንደሆኑ አንዴት ዘነጉት፡ እነዚህን
አብይና ዘውግ የፌዴሬሽን ግርማና ተስፋዎች በቀላሉ ስም ማጥፋት በውነቱ በኔ እምነት
(Morally reprehensible) ተግባር ነው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on June 1, 2014
  • By:
  • Last Modified: June 1, 2014 @ 5:55 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar