www.maledatimes.com እናቱ መፀዳጃ ቤት ጉድጓድ ውስጥ የከተተችው ህፃን ከሞት ተረፈ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እናቱ መፀዳጃ ቤት ጉድጓድ ውስጥ የከተተችው ህፃን ከሞት ተረፈ

By   /   June 2, 2014  /   Comments Off on እናቱ መፀዳጃ ቤት ጉድጓድ ውስጥ የከተተችው ህፃን ከሞት ተረፈ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 34 Second

በሐረር ከተማ “ማሳደግ አልችልም” በሚል ሰበብ የወለደችውን ህፃን በፌስታል አድርጋ መፀዳጃ ቤት ጉድጓድ ውስጥ የከተተች እናት በቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን ህፃኑ ከ6 ሰዓት በኋላ ከጉድጓዲ ወጥቶ ህይወቱ ተርፏል፡፡

በሐረሪ ክልል በቀበሌ 19 ልዩ ስሙ አማሪሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆነችው የ20 ዓመቷ ወጣት፤ ባለፈው ሐሙስ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ የተገላገለችውን ህፃን በፌስታል አድርጋ መፀዳጃ ቤት ጉድጓድ ውስጥ እንደከተተችው የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ጣሰው ቻለው ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡

ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ ወደ ሽንት ቤት ያመራ ጎረቤት የህፃኑን ለቅሶ ሰምቶ ለፖሊስ መጠቆሙንና ህፃኑ በመፀዳጃ ቤቱ ጉድጓድ ውስጥ ተንሳፎ በህይወት መገኘቱን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

በቀን ሥራ የምትተዳደረው እናት ቤቷ ውስጥ ተኝታ መገኘቷን የገለፀው ፖሊስ፤ ህፃኑን መፀዳጃ ቤት ውስጥ የከተተችው የማሳደግ አቅም ስለሌላት እንደሆነ በመናገር ድርጊቱን መፈፀሟን አምናለች ብሏል፡፡ህፃኑ በሐረር ከተማ በሚገኘው የህይወት ፋና ሆስፒታል በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ፖሊስ ጠቁሞ፤ እናትየው ምርመራ እየተደረገባት እንደሆነ ገልጿል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar