www.maledatimes.com የዳኛ ውሳኔ ኢትዮጵያን አስደናቂ ውጤት ከማግኘት አገዳት http://www.total433.com By Fisseha Tegegn - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የዳኛ ውሳኔ ኢትዮጵያን አስደናቂ ውጤት ከማግኘት አገዳት http://www.total433.com By Fisseha Tegegn

By   /   September 14, 2012  /   Comments Off on የዳኛ ውሳኔ ኢትዮጵያን አስደናቂ ውጤት ከማግኘት አገዳት http://www.total433.com By Fisseha Tegegn

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 43 Second

ለሱዳን የተሰጡትን ሁለት የፍጹም ቅጣት ምት ውሳኔዎች በመቃወም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች ለጨዋታው ዳኞች ቅሬታቸውን ሲያሰሙ

በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ካርቱም ላይ ከሱዳን አቻው ጋር የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መደበኛው 90 ደቂቃ የጨዋታ ጊዜ ሊጠናቀቅ አምስት ደቂቃዎች ሲቀሩት ካሜሩናዊው የጨዋታው ዳኛ ለሱዳን የሰጧቸው አጨቃጫቂ ሁለት የፍጹም ቅጣት ምቶች ገብተውበት 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸነፈ።

ጨዋታውን ባለሜዳዎቹ ሱዳኖች ፈጣን ጫናን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ላይ በመሰንዘር የጀመሩ ሲሆን ገና ጨዋታው በተጀመረ በስምንተኛው ደቂቃ ሙድታር አልታይብ ካሪካ ከመረብ ባሳረፋት ጎል 1 ለ 0 በሆነ ውጤት መምራት ቻሉ። ከዚህ በኋላም ሌሎች ግብ ለመሆን የሚችሉ እድሎችን ለመፍጠር ቢችሉም ጎል ያስቆጠረው ግን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ነበር። ጌታነህ ከበደ በግሩም ሁኔታ በ14ኛው ደቂቃ ከመረብ ያሳረፋት ጎል ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ብርታትን፣ ለሱዳን ደግሞ ድንጋጤን ትፈጥራለች ተብሎ ሲጠበቅ ከደቂቃ  በኋላ ግብ ጠባቂው ሲሳይ ባጫ በቀላሉ መያዝ የሚችለውን ኳስ ባልተጠበቀ ሁኔታ በመትፋቱ ቀድሞ የደረሰው ሞሀመድ ባሽር ባስቆጠራት ጎል ሱዳን መሪነቱን እንደገና ወሰደች።

እስከመጀመሪያው ግማሽ የጨዋታ ክፍለ-ጊዜ ማብቂያ ድረስ የሱዳን ብሄራዊ ቡድን በፍጹም የበላይነት ጨዋታውን ከመቆጣጠሩ በተጨማሪ በአዲስ ህንጻ የሚመራውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመሀል ክፍል ጨዋታው ውስጥ ያልነበረ እንዲመስል አድርጎታል ማለት ይቻላል። ጨዋታውን ካርቱም ላይ መጨረስ የፈለጉ የሚመስሉት የሱዳን ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች ተጋጣሚያቸው ላይ የፈጠሩት ተደጋጋሚ የማጥቃት ጫና ተሳክቶላቸው ሙሳብ ኡማር ከቅጣት ምት ያስቆጠራት ግሩም ጎል ጨዋታውን 3 ለ 1 እየመሩ ለእረፍት እንዲወጡ አስቻለቻቸው።

ሁለተኛው ግማሽ የጨዋታ ክፍል-ጊዜ ለኢትዮጵያዊያኑ ፍጹም ከመጀመሪያው ግማሽ የተሻለ ነበር። በአል-ሂላል ክለብ ስታዲዬም ተገኝቶ ጨዋታውን ይከታተል የነበሩት ሱዳናዊያን ደጋፊዎችን በሚያስደነግጥ ሁኔታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአዳነ ግርማ አማካኝነት ሁለተኛውን ጎል አገኘ። ከዚች ጎል መገኘት 15 ደቂቃዎች ቆይታ በኋላ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ስዩም ተስፋዬ ከመረብ ባሳረፋት ጎል በአስደናቂ ሁኔታ አቻ ያደረገውን ጎል አገኘ።

ሱዳን አሸንፎ ለመውጣት፣ እንግዳው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደግሞ ይሄንን ውጤት አስጠብቆ ለመውጣትና አጋጣሚዎች ከተገኙ በመልሶ ማጥቃት ጎል አግብቶ ለመውጣት ያደረጉት እንቅስቃሴ 85 ደቂቃዎች ያህል እንደተጓዘ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት የመሩት ካሜሩናዊው ዳኛ በአስገራሚ ሁኔታ ሁለት አከራካሪ የሆኑ ፍጹም ቅጣት ምቶችን ለሱዳን ሰጥተው ሙሃናድ ኤል-ታሂር አስቆጠረና ጨዋታው በሱዳን 5 ለ 3 አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

ምንም እንኳን በዳኛው ውሳኔ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች እና የቡድን አባላት ቢበሳጩም አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ቡድናቸው በመልሱ ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ የተቻለውን ጥረት ሁሉ አድርጎ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ እንደሚታገል ተናግረዋል።

እ.አ.አ ከ2005 ዓ.ም በኋላ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሱዳን ጋር አምስት ጨዋታዎችን አድርጎ ሲሸነፍ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የመልሱ ጨዋታ የፊታችን ጥቅምት ወር አዲስ አበባ ላይ የሚካሄድ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እ.አ.አ ከ1982 ዓ.ም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የሚያሳትፈውን እድል ለማግኘት ቢያንስ በሁለት ጎሎች ልዩነት ማሸነፍ ይጠበቅበታል።

በጨዋታው ላይ የተመዘገቡትን ስምንት ጎሎች ቀጣዩን ሊንክ በመጫን ማየት ይችላሉ። http://www.youtube.com/watch?v=hjQzYegR2ao&feature=player_embedded#!

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 14, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 14, 2012 @ 5:46 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar