www.maledatimes.com የሊቀመንበርነት ምርጫው ተጠናቋል አቶ ሃይለማርያም የግንባሩ መሪ ሆኑ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሊቀመንበርነት ምርጫው ተጠናቋል አቶ ሃይለማርያም የግንባሩ መሪ ሆኑ

By   /   September 15, 2012  /   Comments Off on የሊቀመንበርነት ምርጫው ተጠናቋል አቶ ሃይለማርያም የግንባሩ መሪ ሆኑ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 57 Second

በትላንትናው እለት ተቋርጦ ለሁለተኛ ቀን የተላለፈው የኢህአዴግ የሊቀመንበርነት ምርጫ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል በዚህ ውሎው ስብሰባውን ያካሄደው የኢህአዴግ ሊቀመንበርን የመረጠ ሲሆን ሃይለማርያም ደሳለኝ የሊቀመንበርነቱን ቦታ ተክተው መያዛቸውን የኢህአዴግ የስብሰባ ካውንስል ባደረገው መግለጫ መሰረት የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ያደረሰን ሪፖርት ያስረዳል።አዲሱ ሊቀመንበር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በአሁኑ ሰአት የጠ/ሚንስትሩን ቦታ ቢቆናጠጡ የተሻለ ነገር ይመጣል ብለው የሚያስቡት የኢትዮጵያ ህዝቦች አይንቸውን ወደ እሳቸው ማዞራቸው ይብልጡኑ ስልጣኑን ሊያሳጣቸው እንደሚችልም አንዳንድ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይገልጻሉ ምክንያቱንም ሲያስረዱ ወያኔ /ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ህዝብ ተወዳጅ የሆነ ሰው ለድርጅታቸው እንደማያስፈልግ ያስረዳሉ ይሄንንም ጠንቅቀው ያውቁታል ።ለዚህም እንደምሳሌ የምንገልጽላችሁ አቶ አርከበ እቁባይ የከተማችን ከንቲባ በነበሩበት ወቅት በሰሩት ስራ ሲወደሱ እና ሲመሰገኑ መንግስት አንስቶ ወደ ታች አውርዶ ነው የወረወራቸው ስለዚህ አሁንም መጠበቅ አይገባንም ሲሉ አክለዋል። በም/ሊቀመነበርነት የተመረጡት አቶ ደመቀ መኮንን ሲሆኑ በአሁን ሰአት የትምህርት ሚንስትር በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙ ናቸው ።እንደማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ከሆነ ወያኔ ኢህአዴግ 180 ካውንስል ያሉት አባላቶቹን በማሰባሰብ ስብሰባውን በትላንትናው እለት ቢጀምርም በአቋም እና በሃሳብ ልዩነት በትላንትናው እለት መበተኑን መዘገባችን ይታወሳል ።ሆኖም ተጀምሮ የነበረውን አጀንዳው የማጽደቁ እቅድ ይቀጥላል በማለት የጀመሩት አባላቶቹ እና የስብሰባው መሪዎች  የድርጅቱን ወስጣዊ እና ውጫዊ ገጽታ ጠንቅቀን ማንጥናት እና በአዲስ መልክ ማዋቀር ግዴታችን ነው ይህም በውስጣችን ለሚገኘው አለመተማመን እና መፍረክረክ ጠቀሜታ ይኖረዋል ሲሉ የድርጅቱ የስብሰባ ካውንስል መሪ የገለጹ መሆኑን የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ አክሎ  ምርጫችን የተሳካ እንዲሆን በቀድሞው የአመራር ህገ ደንብ መሰረት ሁሉንም የመረጥናቸው አባሎቻችን ቃለመሃላቸውን በመፈጸም ወደየስራ ገበታቸው እንዲገቡልን እንፈልጋለን በማለት ግልጦአል ።በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር በኩል ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ስራዎች ስላሉብን እሱን የመጨረስ ግዴታም ሃላፊነትም አለብን በማለት ማሳሰቢያውንም አክሎ ገልጧል ሲል ዘጋቢያችን ከስፍራው አትቷል።

hailemariam dessalegn

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 15, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 15, 2012 @ 7:59 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With: ,

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar