www.maledatimes.com የአላሙዲን ቀኝ እጃቸው መለስ ነበር ግራ እጃቸውን አፋልጉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአላሙዲን ቀኝ እጃቸው መለስ ነበር ግራ እጃቸውን አፋልጉ

By   /   September 17, 2012  /   Comments Off on የአላሙዲን ቀኝ እጃቸው መለስ ነበር ግራ እጃቸውን አፋልጉ

    Print       Email
0 0
Read Time:22 Minute, 34 Second

ፃፈ በወፉ

የጠቅላይ ሚንስትሩ አስክሬን ወደ ኢትዮጲያ አዲስ አበባ በገባ ጊዜ የመለስም፣ የወያኔም ፣የኢህአዴግም፣ የስርዓቱም ደጋፊ ምሰሶ የነበሩት ታላቅ ሰው በአካባቢው አለመታየታቸውያሳሰበው ታላቁ የኢትዮጲያ ህዝብ ሌላ እሬሳ ደግሞ ይመጣ ይሆን በማለት በፍርሃት አስክሬናቸው ይሆን የሚመጣው እያለ ሲጠብቅ ከብዙ ቀናት በኋላ በተሌቪዥን ብቅ ብለው የወንድማቸውን የመለስን ሞት ቀኝ እጄን ነው ያጣሁትበማለት በጉምጉምታ ከመለስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ሼሁ ገሃድ አወጡት፡፡
የሼሁ ጉልበት የትየለሌ ነው፡፡ ሼሁ በህይዎት አሉ ተብሎ ከተነገረ በኋላ ሞተዋል እየተባለ የሚናፈስውን ወሬ ለማምክን ይመስላል ኤርፖረት ድረስ ጋዜጠኛ ሄዶ የጠየቃቸው፡፡ የመንግስቱ ኃይለማሪያምን ንግግር አስታወሰኝ ኢህአፓ ተኩስ ከፍታ ልትገለው ከሞከረች በኋላ በተሌቪዥን ብቅ ብሎ  ሁሉ ነገሬ ደህና ነው ያለበት፡፡ ጋዜጠኛው ሼሁን ጥያቄ ጠየቃቸው ነገሩ ፐሮፖጋንዳ ነው፡፡ ጥያቄው አንድ አባ ብቻ ነው፡፡ ተፅፎ የተሰጠውን የሚያነብ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ወንድምዎትን መለስን ሲያጡ ምን ተሰማዎት? በአለም ቁጥር አንድ የጋዜጠኛ ጥያቄ ብንላትስ፡፡ እስኪ በመጀመሪያ ይህችን  ታስባ ፕሮፖጋንዳ የተሰራባትን አንድ አረፍተ ነገር እንቃኛትና ወደ አንዷ አረፍተ ነገር የሼሁ መልስ እናዘግማለን፡፡

በመጀመሪያ ጋዜጠኛው የወንድምዎት ማለቱ ምንድን ነው፡፡

  1. ጋዜጠኛው መለስና አላሙዲ ምንም የወንድማማችነት ግንኙነት እንደሌላቸው ያውቃል
  2. ጋዜጠኛው መለስና አላሙዲ የስጋም የሃይማኖትም ዝምድና እንደሌላቸው ያውቃል( ማወቅ አለበት ጋዜጠኛ እስከሆነ ድረስ)
  3. ጋዜጠኛው መለስና አላሙዲ የወንድማማች ግንኙነት ሲፈጥሩ አላየም ወይንም አልነበረም(ማንም አያስጠጋውም) ስለዚህ ወንድማማች እንደሆኑ እንዴት አወቀ?
  4. ጋዜጠኛው መለስና አላሙዲ ዝመድና እንዳለቸው ያውም የወንድማማችነት ደረጃ የደረሰ ከሆነ ጋዜጠኛው በል ተብሎ ተነግሮት ነግሮናልና ሃሰቡን ተቀብለን ብንሄድ እንኳን የሁለቱ ወንድማማችነት በሌላ ጉዳይ ነው ማለት ነው
  5. ጋዜጠኛው መለስና አላሙዲ ወንድማማችነት ለጋዜጠኛው ፅፎ ወይንም በል ብሎ ያዘዘው አካል የሁለቱን ግነኙነት ይህን ያህል አቅርቦ ካየው ገዥው ፓርቲ፣ኢህአዴግ፣ወያኔ፣አዜብ ያውቃሉ ማለት ነው፡፡ ጥያቄው ምን ወንድማማች አደረጋቸው የሚለው ነው፡፡
                  ለ‹ መለስ የኢትዮጲያ መሪ ነው ሲሉ ሼኩ ድንገተኛ ጥያቄ ስለሆነባቸው መሰለኝ መሪ ነበር ያላሉት አሊያም አገሪቱ በሙት መንፈስ እንደምተመራ ሊጠቁሙን ፈልገው ሊሆን ይችላል ወይንም የመለስ ሞት እንዳልተዋጠላቸው ያሳያል፡፡ አንድም ቁጭት የወለደው ንግግር ሊሆን ይችላል፡፡ ለማንኛውም ክቡር ሆይ መለስ የአገር መሪ ነበር፣ የማይፈልጉት ይበዙ ነበር የምትለዋ እንኳ ትቅርበዎ፡፡
በመቀጠል ሼሁ የተናገሩት ቃል የፕሮፐጋንዳ ማሳሰቢያን በስልክ ሆነው ተቀብለው እንደነበር የሚጠቁም ነው፡፡ሃያ አመት ሙሉ አሰተማሪያቸው እንደነበር መግለፅ ነው የተሰጣቸው ትዕዛዝ፡፡ የቁጥሩ ስህትት ይሁን አይሁን አላውቅም ፡፡ መለስ የገዛው ሃያ አንድ ዓመት ነው ምንአልባት ሼሁ ትምህርት የጀመሩት ከአንድ አመት በኋላ ነበር ማለት ነው ፡፡ይህ እንግዲህ ከመሸ ወያኔን የተቀላቀሉት ከመሸ የመጡት የድል አጥቢያ አርበኛ ያደርጋቸዋል፡፡ ለማንኛውም ሼሁ ከመለስ የተማሩት የመጀመሪያው ትምህርት የአገር መስዋትነት ነው፡፡ ሃተታው የሚከተለው ነው
በሁለተኛ ደረጃ የተማሩት የአገር ልማትን ነው፡፡ ከእሱ የተማርሁት ያሉትን ብናጤነው ሌላ መልስ አለው፡፡ መለስ የልማት ጀግና ነው የተባለው በርግጥ ልማት ወዶ ነው ወይስ የፖለቲካ ስልጣኑን ለማስጠበቅ የተጠቀመበት፡፡ እራሳቸው ሼሁ ይመልሱት፡፡ ዴሞከራሲ ወይስ ልማት ቅደም መለስ ከምርጫ 97 በፊት ልማት ሳይሆን ዴሞክራሲ ማወናበጃው ነበር እነበለውና መለስ ከ97 በፊት ትንሽ ቀድም ብሎ ሞቶ ቢሆን ኖሮ ሼኩ የተማረሁት ዴሞክራሲን ነው ይሉን ነበር፡፡ በነገራችን ላይ ሼሁን የሚያስመሰግናቸው ከመለስ ዴሞክራሲን ተምሬያለሁ አለማለታቸው ነው፡፡ በያንስ በዚህ ከወያኔ የተለዩ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡ ይህ የልማት ትምህርት ምንድን ነው?
ለ. መለስ የወያኔን ጉዙፍ ድርጅት ሌላውን እያጠፋ ሲገነባ የሼሁ ድርጅት እንዴት ሌሎች ነጋዴዎችን መዋጥ እንዳለበት አስተምሮቸዋል (የመዋጥ ጥበብ) ከዚሁ ጋር በሙስና፣ በጥገኛ ነጋዴነት ብዙዎች ሲታሰሩ እሳቸው በአስተማሪያቸው ጥላ ውስጥ ስላሉ ዝምባቸውን እሽ ያለም የለም( ለነገሩ ዝምብ ፈታቸው መች ይኖርና)፡፡ ምክንያቱም ልማታዊ ተናጋሪዎች፣አልቃሾች፣አድናቂዎች፣ወንድማማቾችን ማን ይነካቸዋል ብላችሁ ነው፡፡ ለነሱ የተመደበ ዝምብ የለም፡፡
1ኛ. ቀኝ እጅ በጥንት ሥነፅሁፋዊ መረጃ  መሰረት ሥልጣን (authority) ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሄር በቀኘ ተቀመጥ አለው ሲል ሥልጣን ሰጠው( የነበረውን ስልጣን ማለት ነው)፡፡ ሌላው ምሳሌ ሶስት የስልጣን አካላት መግለጫ ሲሰጡ ወይንም ስብሰባ ሲመሩ መሃል ላይ የሚቀመጠው ዋና ባለስልጣን በቀኝ በኩል የሚቀመጠው ሁለተኛ በግራ በኩል የሚቀመጠው ሶስተኛው ሰው ይሆናል ማለት ነው፡፡
2ኛ. ቀኝ እጅ በድሮ ሥነፅሁፋዊ መረጃ መሰረት ፈቃድ መስጠት (licensed ) ማለት ነው፡፡ ቀኝ እጃቸውን ሰጡኝ ከተባለ ፈቀዱልኝ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አላሙዲ አጣሁት የሚሉት መለስ የተባለውን ቀኝ እጄን ማለት ስልጣኔንና ፈቃድ ለጋሼን ተነጠቅሁ ማለት ይሆናል፡፡በአገሪቱ በወርዳና በስፋት እየነቀሉ እየተከሉ እየቆፈሩ እየሸጡ እየበሉ እያባሉ ኢትዮጲያን አሳልፎ የሰጣቸው ሰው ነው፡፡ መለስ ብሎ ለተመለከተው ከንግግራቸው እንዳጣሁ ይሰማኛል ብለዋል፡፡ ይህ ንግግር ሦስት ነገር ያሳያል
ወደ ዋናው ጥያቄ ልምጣና ቀኝ እጃቸው መለስ ነበር ግራ እጃቸውስ ማነው? ግራ እጃቸውን ፈልጎ ማግኘት በጣም ይከብዳል፡፡ ማግኘት ግን አለብን፡፡ ግራ እጃቸው ሲሞት ግራ እጄን አጣሁ (እንዳጣሁ እቆጥረዋለሁ) እንዳይሉን፡፡ ፈልጌ አስፈልጌ የሚለው ዘፈን እዚህ ጋ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በነገራችን ላይ መለስ የሼሁ ቀኝ እጅ ብቻ አይደለም ሼሁም የመለስ ቀኝ እጅ ነበሩ እነ ሰለሞን ተካልኝ እነ ነዋይ ደበበ እንዲሁም የኢትዮጲያውያን  እግር ካስ ለሁለት የከፈሉት ሼሁ ናቸው ተብሎ ይገመታል፡፡
የትምህርት ሚነስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ግራ እጅ ሊሆን አይችልም ቦጅባጃ እና አዲስ ሰው ነው፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሊሆናቸው አይችልም ምክንያቱም በልምድም፣በሃይማኖትም፣ በአቅምም የግራ ክንፉን ወስዶ መጫዎት አይችልም ባይሆን የአቶ አብነት ዕጩ ሊሆን ይችላል፡፡ አባዱላ ገመዳ ግራውን ይዘው መጫዎት ይከብዳቸዋል የፓርላማ መዶሻ ይዘውበታልና፡፡ አዲሱ ለገስም ቢሆን የፊውዳል ልጅ ስለነበር በቀላሉ ግራ ለመጫዎት አቅም የለውም ደግሞም ከመለስ ጋር ያጣላኛል ብሎ ስለሚፈራና ከነፈሰው ጋር ሰለማይነፍስ ለዚህ አይመችም፡፡ ቄሱ ተፈራ ዋልዋ በሽተኛም ደካማም ሰለሆነ እና የሰራው በአብዛኛው የአቅም ግንባታ ሚንስቲር ስለነበረ አላሙዲ ደግሞ አቅም የገነቡ ስለሆን የተፈራን ግራ ዕጅነት አይሹም፡፡ጓድ በረከት ስምዖን ግራ እጅ ሊሆን አይችልም፡፡ የሼሁ የቁልፍ መያዢያ ነው፡፡ በረከትን አንጠልጥየ ደቡብ አፈሪካ ለህክምና የላኩሁት እኔ ነኝ ብለዋል አንድ ወቅት፡፡ የበረከትን መፅሃፍ ያሳተሙለት እሳቸው ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ በረከት መፅሃፍ እንዲያሳትሙለት እንዴት ነገራቸው፡፡ በረከት የማስታወቂያ ሚኒስቴር ስለነበር ከልምዱ ተነስቶ በዜዴ ነግራቸው ወይንም በሰው በኩል እንዲሰሙ አድርጎ ቢሆንስ እርግጠኛ ነኝ በቀጥታ አይነግራቸውም፡፡  በረከት መጣጣ ድሃ ይመስለኛል የእኔ ግምት ነው፡፡ ማጣራት ትችላላችሁ፡፡ ጄኔራል ሳሞራ የነሱም ሆነ ሌሎች ጄኔራሎች የሼሁ መጫዎታዎች ናቸው ሲባል ስለሰማሁ ግራ እጃቸው ሊሆኑ አይችሉም ባይሆን የግራ እጃቸው ትንሻ ጣት እነ አማረ አረጋዊን የመሳሰሉትን ለመኮርኮም ያክል የሚያገለግሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አርከበም መልክ ብቻ ናቸው ሼሁ በቁመና እና ባለባበስ ይቀናሉ ይህ እውነተኛ መረጃ ነው፡፡ የቁመና ነገር ከተነሳ መለስም ችግር አለባቸው መለስ አርከብንም ታምራትን በቁመናቸው ምክንያት አይወዳቸውም ነበር፡፡ የሲቪል ሰርቪሱ ጁነዴን ሳዶን አላሙዲ አያስጠጓቸውም በሁለት ምክንያት (ግምት) ነው፡፡ ጁነዲን ሳዶ ሲቪል ሰርቪስ ውስጥ ስለሆነ  የሚሰራው ሼሁ ከሲቪል ሰርቪስ ጋር የሚያገናኛቸው ምንም ነገር የለም ሁለተኛ እንኳን ሚስታቸው በዕስልምና አክራሪነት ተጠርጥረው ታስረው ቀርቶ ስለዚህም ግራውን ሊይዝ አይችልም፡፡
ስለዚህም ግራውን ከነዚህ ውስጥ ፈልጉ፡፡ ሥዩም መስፍንን አባይ ፀሃይን በቀላሉ ጠርጥሩ በተለይ የስካር ልማት ተጠሪውን አባይን፡፡ አቶ ስብሃት ግራውን ይዘው እንደቆየ አያጠራጥርም ሰውየው ከኤፈርት ጋር ይሰራሉ ሲባል ይሰማልና አቶ ስብሃት ደግሞ የኤፈርት ሊቀመንበር ነበረ፡፡ የእንዱስትሪው ሚኒስተሩ ግርማ ብሩ በቀጭኑ የግራ ክንፍ ሳይጫወቱ አሊያም ከአደም ዘር የጎደለችውን የግራ አጥንት ሲሞሉ የኖሩ ይመስለኛል (መሰለኝ ነው) ፡፡ ወያኔ ሙሉ በሙሉ የሼሁ እጅ ነው፡፡ እኔ ግን ወ/ሮ አዜብ ግራ እጃቸው ሳይሆኑ የቀሩ አይመስለኝም ምን አለፋችሁ በባልና በሚሰት በቀኝና በግራ ተጠፍረው ነበር የሰሩት ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም አቶ አብነትን ጨምሮ ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች በሙሉ የሼሁ እግሮች ወይም ትናንሽ የሰውነት ክፍሎች እንጂ የቀኝና የግራ ዕጅ የሆኑ አይመስለኝም፡፡ ግራውን ፈልጉ ቀኙ ሂዳልና፡፡
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 17, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 17, 2012 @ 10:40 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar