www.maledatimes.com ይድረስ ለተክለሚካኤል አበበ፡ የነጻ ጋዜጣ መለኪያው ላንተ ምንድን ነው? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ይድረስ ለተክለሚካኤል አበበ፡ የነጻ ጋዜጣ መለኪያው ላንተ ምንድን ነው?

By   /   September 18, 2012  /   Comments Off on ይድረስ ለተክለሚካኤል አበበ፡ የነጻ ጋዜጣ መለኪያው ላንተ ምንድን ነው?

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 53 Second

ከሮቤል ሔኖክ ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ከሰሞኑ በኢሳት ራድዮ ላይ የምሰማው ማስታወቂያ እያስገረመኝ ነው። በቅድሚያ ለራሱ ለማስታወቂያው አንባቢው በግል ኢሜይሉ ልልክለት አሰብኩና በኋላ
ላይ ሳስበው ሕዝብ የሰማው ማስታወቂያ ስለሆነ የኔም ምላሽ በግልጽ ቢሆን መረጥኩኝ። በኢሳት ራድዮ ላይ ከሰሞኑ የሚሰማው ማስታወቂያ እንደ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ባልደረባነቴ የፈጠረብኝ ስሜት የሚያሸማቅቅ ነበር። ራድዮው የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነውን “ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣን” በሰሜን አሜሪካ የምትታተም ብቸኛዋ ነጻ ጋዜጣ ሲል ይገልጻታል። ብቸኛዋ ሲል እንግዲህ ሌላ ነጻ ጋዜጣ የለም ማለቱ ነው የማስታወቂያው አንባቢ ተክለሚካኤል አበበ።
በቅድሚያ “ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ” ምንም እንኳ “ሰፊ የሚድያ ሽፋን ያለው ኢሕአዴግ እንኳ በጋዜጣችን መልዕክት ላስተላልፍ ካለ እንፈቅዳለን” የሚል ቢሆንም የአንድነት ፓርቲ ልሳን መሆኑን ግን ጋዜጣው ራሱ ያምናል። አንድነትም ጋዜጣዬ ነው ይለዋል። ተክለሚካኤል ይህንን የፓርቲ ልሳን ጋዜጣ “በሰሜን አሜሪካ የሚሰራጨው ብቸኛው ነጻ” ሲል ይገልጸዋል። ይህ ጋዜጣ በፓርቲ ልሳንነቱ “ብቸኛው ነጻ ጋዜጣ” ከተባለ ላለፉት 5 ዓመታት የለፋንለት ዘ-ሐበሻ ጋዜጣስ? የግድ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ በአቶ ተክለሚካኤል አገላለጽ “በሰሜን አሜሪካ ብቸኛው ነጻ ጋዜጣ” ለመባል እርሱ የሚደግፈው የግንቦት 7 ወይም የሌላ ተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊ መሆን አለበት ወይ? እርግጥ ነው ተክለሚካኤልም ሆነ ይህንን ማስታወቂያ በራድዮው እንዲያስተላልፍ የፈቀደው ኢሳት ራሱ ነጻ ጋዜጠኝነትን ገደል ከተውታል። እነ እስክንድር ነጋ ዛሬ እስር ቤት የሚማቅቁት፤ 126ቱ ጋዜጠኞቻችን በስደት የሚንገላቱት የፓርቲ ጋዜጠኞች ሆነው ሳይሆን ነጻ ጋዜጠኞች ሆነው ነው። ተክለሚካኤል ‘ነጻ ጋዜጠኝነትን” ለፓርቲ ጋዜጠኞች ስለሰጣቸው  እነ እክንድርም ነጻ አይደሉም ተብለው ተደፍረዋል ማለት ነው።

አንድ ሚድያ ስለሚያስተላልፋቸው ማስታወቂያዎች ሃላፊነት ሊሰማው ይገባል። አንድነት ፓርቲ ለዚህ ጋዜጣ ማስታወቂያ ለኢሳት የከፈለው ገንዘብ ኖረም አልኖረም ኢሳት ማስታወቂያዎቹን ከኤዲቶሪያል ፖሊሲው ጋር በሚሄድ መልኩ ማስተላለፍ ይኖርበታል። ለምሳሌ አንዳንድ ሚዲያዎች የአልኮል መጠጦችን እና ሲጋራን ላለማስተዋወቅ ፖሊሲ ያላቸው አሉ። ኢሳትም አንዱን ለመካብ ሲባል የሌላውን ስሜት የሚጎዱ ነገሮችን፣ እውነት ያልሆኑ ማስታወቂያዎችን ገንዘብ ቢቀበል እንኳ ማስተላለፍ የለበትም።
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ በሰሜን አሜሪካ ከሚታተሙ ጋዜጦች መካከል አንዱ ነው። ይህን ጋዜጣ ከምናዘጋጀው ጋዜጠኞች መካከል አብዛኞቻችን በነጻ ጋዜጠኝነታችን የተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈልን፣ የታሰርን፣ የተደበደብን፣ የተንገላታን ነን። በተለይ ባለፉት 5 ዓመታት ከ7 በላይ ስቴቶች በመሰራጨት ተነባቢነት ያለው ትልቅ ጋዜጣ ነው። ጋዜጣው የማንንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊ አይደለም። በዌብ ሳይት ደረጃም፣ በፌስቡክም፣ በትዊተርም፣ በጎግል +ም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚነበብ በነጻ ጋዜጠኞች የሚዘጋጅ ጋዜጣ ነው። የግድ ዘ-ሐበሻ “ነጻ ጋዜጣ” ተብሎ እንዲገለጽ የግንቦት 7፣ ወይም የኢሕአዴግ፣ ወይም የአንድነት፣ ወይም የኦነግ ወይም የማንም መሆን የለበትም። የተክለሚካኤልም የነጻ ጋዜጣ መለኪያው በዚህ ከሆነ ያሳፍራል፤ ያሸማቅቃልም።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 18, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 18, 2012 @ 5:36 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar