www.maledatimes.com ኦህዴድ በኢሕአዴግ ሹመት ላይ ቁልፍ ቦታዎችን አጥቷል የሚለውን ለማጥራት በአዲስ አበባ ዝግ ስብሰባ ተቀምጧል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኦህዴድ በኢሕአዴግ ሹመት ላይ ቁልፍ ቦታዎችን አጥቷል የሚለውን ለማጥራት በአዲስ አበባ ዝግ ስብሰባ ተቀምጧል

By   /   September 19, 2012  /   Comments Off on ኦህዴድ በኢሕአዴግ ሹመት ላይ ቁልፍ ቦታዎችን አጥቷል የሚለውን ለማጥራት በአዲስ አበባ ዝግ ስብሰባ ተቀምጧል

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 21 Second

በዘሪሁን ሙሉጌታ (ሰንደቅ ጋዜጣ)
የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የስራ አስፈፃሚ አባላት በአዲስ አበባ ዝግ ስብሰባ ማካሄድ ላይ ናቸው። የኦህዴድ የስራ አስፈፃሚ አባላት ስብሰባ ከኢህአዴግ የም/ቤት ስብሰባ በኋላ ወዲያውኑ እንዲካሄድ መደረጉ የተለያዩ ወገኖችን ትኩረት ስቧል።
ኢህአዴግ መስከረም 4 እና 5 ቀን 2005 ዓ.ም ባካሄደው የም/ቤት ስብሰባው በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ምትክ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝንና አቶ ደመቀ መኮንንን በሊቀመንበርነትና በምክትል ሊቀመንበርነት ከመረጠ በኋላ
የኦህዴድ የሥራ አስፈፃሚ ስብሰባ ተጀምሯል። የስብሰባው ትኩረት ምን እንደሆነ በዝርዝር በይፋ ባይገለፅም በቀጣይ የድርጅቱ አቅጣጫና በኢህአዴግ የከፍተኛ አመራር መተካካት እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ዙሪያበተለይም በኦሮምያ ከተሞች የኪራይ ሰብሳቢነት ችግርን እንዴት መቅረፍ ይቻላል በሚሉ ጉዳዮች ሊሆን እንደሚችል ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
ስብሰባው ከኢህአዴግ የከፍተኛ አመራር መተካካት ጋር በተያያዘም በግንባሩ ውስጥ ኦህዴድ ተገቢውን ቦታ አላገኘም የሚሉ ብዥታዎችን ለማጥራት፣ አሁን ከላይ የተጀመረው መተካካት በቀጣይ ወደታች በሚወርድበት ጉዳይ እንዲሁም ሕዝቡ በግንባሩ የጋራ አመራር ፅኑ እምነት ይዞ እንዲቀጥልና አመራሩም በዚህ አግባብ ትግሉን እንዲያስቀጥል የማድረግ ዓላማ እንዳለው ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል።
ኢህአዴግ የአመራር መተካካቱን ካከናወነ በኋላ ኦህዴድ በግንባሩ ውስጥ ተገቢውን ቦታ አላገኘም በሚል የተሳሳቱ ስሜቶች መፈጠራቸው እንደማይቀር ታምኖበት በአስቸኳይ ሥራ አስፈፃሚው ስብሰባ መቀመጡን የሚጠቅሱት ምንጮች ይህ አስተሳሰብ በቀጣይ የድርጅቱን ጥንካሬና የክልሉን ልማት እንዳይጎዳና አሉባልታውን ለመስበር ታስቦ የሚደረግ ስብሰባ መሆኑንም የሰንደቅ ምንጮች ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት የስልጣን መተካካት እንጂ የስልጣን መቀማማት እንዳልተከናወነ አባሉም ሆነ ሕዝቡ አውቆ በቀጣይም የመተካካቱ ሂደት በተለያዩ የአመራር እርከኖች እንደሚቀጥልና የተጀመረው ልማት ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ጉዳይ ዙሪያ እንደሚመክር ታውቋል።
የክልሉ ፕሬዝዳንት ቀደም ሲል የጤና መጓደል ቢገጥማቸውም በአሁኑ ወቅት የጤናቸው ሁኔታ መሻሻል በማሳየቱ ሌላ ምደባ እንደማይኖር ምንጮቻችን ጠቁመዋል። በዚሁ ከኦህዴድ የሰራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ ከመልካም አስተዳደር ጋር የተያያዙ ጉዳዮችና በክልል ደረጃ የአምስት ዓመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ግምገማ ይካሄዳል። እንደምንጮቻችን ገለፃ የስራ አስፈፃሚው የሚያስቀምጣቸው አቅጣጫዎች በቀጣይ በተዋረድ ለተለያዩ የአመራር እርከኖች ወርዶ ሕዝቡ እንዲወያይበትና የጋራ አቋም እንደሚያዝም ተገልጿል።
እንደ ኦህዴድ ሁሉ ሌሎቹ የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ተመሳሳይ ስብሰባ ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተለይ ህወሓት ሊቀመንበር ከመሾሙም በተጨማሪ በሌሎች ድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ስብሰባውን ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 19, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 19, 2012 @ 10:27 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar