www.maledatimes.com በአማራ ክልሉ ተመራጭ እና በደቡቡ እምነት የላቸውምን?ኢህአዴግ በጥር ወር እንደገና የሊቃነ-መናብርት ምርጫ ያደርጋል ተባለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በአማራ ክልሉ ተመራጭ እና በደቡቡ እምነት የላቸውምን?ኢህአዴግ በጥር ወር እንደገና የሊቃነ-መናብርት ምርጫ ያደርጋል ተባለ

By   /   September 19, 2012  /   Comments Off on በአማራ ክልሉ ተመራጭ እና በደቡቡ እምነት የላቸውምን?ኢህአዴግ በጥር ወር እንደገና የሊቃነ-መናብርት ምርጫ ያደርጋል ተባለ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 30 Second

የኢትዮጽያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ዘጠነኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን በመጪው ጥር ወር እንደሚያካሂድ ተጠቆመ። በዚሁ ጉባዔ ላይ የድርጅቱን ሊቀመንበር ጨምሮ የሥራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ የሚያካሄድ ሲሆን ሰሞኑን የተመረጡት የግንባሩ ሊቃነመናብርት በድጋሚ ከተመረጡ እንደሚቀጥሉ ታውቋል።
ግንባሩ ሰምንተኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን በአዳማ በመስከረም ወር መጀመሪያ 2003 ዓ.ም ያካሄደ ሲሆን ከግንባሩ ጉባዔ አስቀድሞ አራቱ አባል ድርጅቶች በተናጠል ባካሄዱት ጉባዔ በመተካካት ዕቅዱ መሰረት ጎምቶዎቹ ባለሥልጣናት መሸኘታቸው የሚታወስ ነው። በዚሁ መሰረት ህወሃት አቶ ሥዩም መስፍንን፣ አቶ አባይ ጸሐዬን፣ አቶ አርከበ ዕቁባይን ከስራ አስፈፃሚነት ያሰናበተ ሲሆን ብአዴን በበኩሉ አቶ አዲሱ ለገሰን፣ አቶ ተፈራ ዋልዋን፣ አቶ ታደሰ ካሳን አሰናብቷል። ደኢህዴን አቶ ብርሃኑ አዴሎን፣ ኦህዴድ፤ አቶ ጁኔይዲን ሳዶን ጨምሮ ብቸኛ ሴት የስራ አስፈጻሚ አባል የነበሩትን ወ/ሮ አስቴር ማሞን ከስራ አስፈፃሚነት መሸኘቱ የሚታወስ ነው።
በመቀሌ ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ቀጣዩ ጉባዔም በዚሁ የመተካካት መንፈስ በዕድሜና በሥራ አፈጻጸም የደከሙትን ቅድሚያ በመስጠት በክብር በማሰናበት በአዲስ ኃይል እንደሚተካ ምንጫችን ጠቁሟል።
ለመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ሰሞኑን መግለጫ የሰጡት የግንባሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን በቀጣዩ ጉባዔ በሚካሄደው ምርጫ አዲሶቹ የግንባሩ ሊቀመናብርት ከተመረጡ ብቻ እንደሚቀጥሉ መናገራቸው ይታወሳል።
የኢህአዴግ ጉባዔ ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ የሚካሄድ ሲሆን የአመራር አባላቱም ምርጫም በዚሁ ጊዜ ሲያከናውን ቆይቷል። ግንባሩ በየሁለት ዓመቱ የስራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ ቢያካሄድም ለረዥም ጊዜ ነባሮቹ አመራሮች በተደጋጋሚ እየተመረጡ በኃላፊነት ላይ መቆየታቸው አይዘነጋም።
ኢህአዴግ ከአራቱ አባል ፓርቲዎች ዘጠኝ የሥራ አስፈጻሚ አባላት በድምሩ 36 አባላቱ የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚ ሲሆኑ ከእያንዳንዱ ፓርቲ 45 ሰዎች የተወከሉበት በድምሩ 180 አባላት የያዘ ምክርቤት እንዲሁም ስምንት አባላት ያሉት የቁጥጥር ኮሚሸን አባላት አሉት።
180 አባላት ያሉት የኢህአዴግ ም/ቤት ባለፈው ዓርብ እና ቅዳሜ ዕለት ባካሄደው ስብሰባ የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ ድንገተኛ ሞት ጋር ተያይዞ እስከመጪው ጉባዔ ድረስ የሚያገለግሉ አመራሮችን መርጧል። በዚሁ መሠረት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን በሊቀመንበርነት፣ አቶ ደመቀ መኮንንን በምክትል ሊቀመንበርነት መምረጡ የሚታወስ ነው። (ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ) 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 19, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 19, 2012 @ 10:32 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar