www.maledatimes.com ኢሕአዴግ የመንግሥት ኃላፊዎችን የሥልጣን ዘመን በአሥር ዓመት ገደበከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ የስልጣን ጭላንጭሉ የደከመበት ይመስላል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢሕአዴግ የመንግሥት ኃላፊዎችን የሥልጣን ዘመን በአሥር ዓመት ገደበ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ የስልጣን ጭላንጭሉ የደከመበት ይመስላል

By   /   September 19, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 45 Second

•    አቶ ኃይለ ማርያም ዓርብ በፓርላማ ሹመታቸው ይፀድቃል

በዘካሪያስ ስንታየሁ source  (reporter )

በኢሕአዴግ በወጣው የመተካካት ፖሊሲ መሠረት የመንግሥት ኃላፊዎች የሥልጣን ዘመን በአሥር ዓመት መገደቡ ተገለጸ፡፡

በመሆኑም ኢሕአዴግ ከሁለት ዓመት በፊት ይፋ ባደረገው የመተካካት ፖሊሲው የጠቅላይ ሚኒስትሩና የሚኒስትሮች የሥልጣን ዘመን ሁለት የምርጫ ዘመን መሆኑ ታውቋል፡፡

ባለፈው ቅዳሜ ምሽት የኢሕአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን እንዳስታወቁት፣ የመተካካቱን መርሆች መነሻ በማድረግ በኢሕአዴግ የተወሰኑ ውሳኔዎች አሉ፡፡ ‹‹የፓርቲ አመራር ሆኖ ለመቀጠል ዕድሜ ነው ከፍተኛ ጣሪያ የተደረገው፡፡ በፓርቲው ፖሊሲ መሠረት አንድ ሰው እስከ 65 ዓመት ድረስ ቢሠራ ብዙ ችግር የለም ብለን እንስማማለን፤›› ብለዋል፡፡

አንድ የመንግሥት ኃላፊ ሁለት የምርጫ ዘመን የማገልገል ዕድል ቢያገኝ ይጠቅማል ብለን እናምናለን ያሉት አቶ በረከት፣ በሕዝብ ቢመረጥም እንኳን ከሁለት የምርጫ ዘመን በላይ በሥልጣን ላይ መቆየት የለበትም የሚል የፓርቲ ውሳኔ መኖሩን አስታውቀዋል፡፡

በሕገ መንግሥቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ዘመን ገደብ ባይመቀጥለትም፣ ኢሕአዴግ በመተካካት ፖሊሲው መሠረት ለመንግሥት የሥልጣን ኃላፊነቶች የሥልጣን ዘመን አስቀምጧል፡፡ በተለይም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ዘመን ከአሥር ዓመት በላይ እንዳይዘል ኢሕአዴግ መስማማቱን አስታውቋል፡፡ ሆኖም ግን ስምምነቱ ወደፊት በሕግ ደረጃ ስለመውጣቱ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ አቶ በረከት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ዘመን በተጨማሪ የሌሎች ሚኒስትሮች የሥልጣን ዘመን በተመሳሳይ በአሥር ዓመት እንዲገደብ ኢሕአዴግ መስማማቱን ገልጸዋል፡፡

ኢሕአዴግ የመተካካት ሐሳቡን ሲጀምረው ብዙ ጥናት ማካሄዱንና አገሮች እንዴት መሪዎቻቸውን ይተካሉ የሚለውን ማየቱን የገለጹት አቶ በረከት፣ ‹‹ከበርካታ አገሮች የወሰድናቸው በጐ ተሞክሮዎች ቢኖሩም፣ በራሳችን የነደፍናቸው መርሆችም አሉ፤›› ብለዋል፡፡ በዚህም መሠረት ሌሎች አገሮች የመሪዎቻቸውን ዕድሜ የማይገድቡ ሲሆን፣ ኢሕአዴግ ለመሪዎች የዕድሜ ገደብ ማስመቀጡን አስታውቀዋል፡፡ ‹‹የመሪዎች የዕድሜ ጣሪያ የሃምሳዎቹ መጨረሻ ወይም የስልሳዎቹ መጀመርያ መሆን አለበት የሚል ፅኑ አቋም አለን፡፡ አንድ ሰው እስኪደክም ድረስ መጠበቅ የለብንም፡፡ አቶ መለስ በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ በስልሳ ዓመታቸው ሥልጣን ይለቁ ነበር፤›› ብለዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ባለፈው ቅዳሜ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር በመሆን በሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ ምትክ የተመረጡት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ በመጪው ዓርብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣናቸው በይፋ ይፀድቅላቸዋል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ሥልጣንን ለማፅደቅ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን ለሪፖርተር የገለጹት፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከማል ናቸው፡፡

የአቶ መለስ ሕልፈትን ተከትሎ ምክር ቤቱ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን በድረ ገጻችን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ለስብሰባው መራዘም ከመንግሥት የተሰጠው ምክንያት የአቡነ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ሥርዓት መሆኑ ይታወሳል፡፡ በቅርቡ በተካሄደው የኢሕአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ የግንባሩ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ኃይለ ማርያም፣ በድርጅቱ ልምድ መሠረት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ ተገልጾ ነበር፡፡ ሆኖም ሙሉ ሥልጣናቸውን ምክር ቤቱ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ያፀድቅላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዲሞክራሲያዊ መንግስታቶች ዘንድ የሚደረገውን የስልጣን ዝውውር እና ሽግግር የወያኔ መንግስት የማያምንበት እና እስከዛሬ ድረስ ለ21 አመታት ያልተመራበት እንደሆን ይፋ መሆኑ ይታወቃል ።ማንኛውም የዲሞክራሲያዊ ስርአት አራማጅ የሆኑ መንግስታቶች በየአራት አመታቱ መንግስታቸውን ሲመርጡ የወያኔ አስተዳደር መንግስት ግን ለ21 አመታት በአንድ ሰው በጫና እና በዘረኝነት አገዛዝ ተዳድሮ መቆየቱ ይታወሳል ። ይህን ያህል የዘመን ሂደት ከተጓዙ በኋላ የስልጣን ጊዜአቸውን ለመገደብ ወስነዋል ።ይህም የሆነበት ምክንያት የአቶ መለስ ዜናዊ የስልጣን ብልጣብልጥነት አብሮአቸው ስለተቀበረ ከዚህ በኋላ ኢሃዴግን ማንም እንደሳቸው አሳምሮ ሊመራላቸው የሚችል ሰው እንደሌለ ጠንቅቀው ያውቁታል ለዚያም ሲሉ በአዲስ የህግ ረቂቅ አዋጅ መሰረት ከአቶ መለስ ድህረ ሞት በኋላ ሊያረቁ በቅተዋል ።ይህ በመላው አለም የሚያሳፍር እንደሆነም አውቀውታል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 19, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 19, 2012 @ 11:12 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “ኢሕአዴግ የመንግሥት ኃላፊዎችን የሥልጣን ዘመን በአሥር ዓመት ገደበ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ የስልጣን ጭላንጭሉ የደከመበት ይመስላል

  1. I hope Mr. Bereket is seeing the light or I don’t know if there’s something else behind to his party decision. Sometimes it looks like TPLF is running a parallel tigray state because things are done differently in tigray compared to the rest of the country. Whether the decision is as 21 years a go when they first came to power it was said their question is to liberate tigray and possibly join eritrea. They will develop tigray and once they get as much as they can on the cost of the rest of Ethiopia, they will divide and instigate to flame civil war and say well we can no longer rule the country we need you take the governing of your country and leave and start greater tigray. If that is the case here I guess as long as we have our people and the rest of Ethiopia we’ll manage to recuperate and reorganize our country and learn from the past and move forward. As far as tigray will be gone it’s not much to lose.
    If that’s not the case I can’t see why they keep abusing our people they should calm down the people and guide with respect and love not force. If they do the right thing people will reelect them but the way they are abusing people it’s damaging it’s hard to watch.
    I hope Mr. Bereket have wise up and trying to sacrifice for the better of our country and build a path for a democratic Ethiopia through same system as European or American. An elected official can hold maximum only 2 term each being 4 years a total of 8 that would eliminate corruption and establish accountability.

    Please, stop the killing and abusing people it’s absolutly unnecessary don’t see that you have the control of power today you never know what the future will bring. To avoid future consequences this rowdy military who act un Ethiopian brutality they have to think about tomorrow. No one last forever watch and learn mengistus cadres who committed crime are convicted today in U.S.A for the crime they did in the past. This people have to realize there’ll be a judgment day coming for them to.

    God Bless Ethiopia and give us wisdom specisally for those who sit in power today!

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar