www.maledatimes.com ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ የሥልጣን መልቀቂያ አስገቡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ የሥልጣን መልቀቂያ አስገቡ

By   /   September 20, 2012  /   Comments Off on ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ የሥልጣን መልቀቂያ አስገቡ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 23 Second

(ዘ-ሐበሻ)የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም የሆኑት ጄነራል ሳሞራ የኑስ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን የኢሳት ቴሌቭዥን ዛሬ ዘገበ። አቶ መለስ ዜናዊ ከሌሉ ሳሞራ የኑስ መቆየት አይችሉም እየተባለ በሰፊው ሲነገርላቸው የቆዩት እኚሁ የመከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም ለስልጣን መልቀቂያው ያቀረቡት ምክንያት “በቃኝ! ደከመኝ” የሚል ነው ሲል ኢሳት ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።

samora

መንግስት ሰሞኑን ለጀነራሎች ሹመት ሲሰጥ በሕወሓት ክፍፍል ወቅት ከነስዬ አብርሃ ጋር አብረው ከተባረሩት ጀነራሎች መካከል የአየር ኃይሉ አዛዥ አበበ ተክለሃይማኖት ባለቤትና ለአድዋ ተወላጅ ለሆኑት ለኮለኔል አስካለ ብርሃነ የመጀምሪያዋ ሴት የብርጋዴር ጀነራልነት ሹመት መሰጠቱን ዘ-ሐበሻ ከቀናት በፊት መዘገቧ አይዘነጋም። ከሰሞኑ ለ37 ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ሹመት ከተሰጠ በኋላ በመከላከያ ውስጥ ያለው ውጥረት እያየለ ከመምጣቱም በላይ ከነስዬ ጋር አብረው ተባረው የነበሩት ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ከራያ ቢራ ፋብሪካ ፕሮጀክት ውጭ በጦሩ ውስጥ ያሉ
ደጋፊዎቻቸውን በማሰባሰብ ከፍተኛ የሆነ ምስጢራዊ የማደራጀት ሥራ እየሰሩ መሆኑን በጦር ሰራዊቱ አካባቢ ያሉ የዘ- ሐበሻ ምንጮች ተናግረዋል።
ወትሮም ቢሆን ሰራዊቱን የመምራት ብቃት የሌለው ሳሞራ የኑስ ስልጣኑን ያገኘው የመለስ ቡድን ስላሸነፈና መለስ ስልጣን ላይ ስለነበረ እንደሆነ የሚገልጹት የሕወሓት የውስጥ አዋቂዎች አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ “ደከመኝ ወይም በቃኝ” ብለው የስልጣን መልቀቂያ ማስገባታቸው እንደማያስገርም ተናግረዋል።

የቀድሞው ኢታማዦር ሹም፤
የአሁኑ የራያ ቢራ ፋብሪካ
መሥራች ጀነራል ጻድቃን
ገ/ትንሣኤ

በከፍተኛ ሕመም ላይ እንዳሉ የሚነገርላቸውና በተከታታይም ወደ ውጭ ሃገር እየወጡ በመመላለስ በመታከም ላይ የሚገኙት ሳሞራ የኑስ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን የዘገበው ኢሳት የሥራ መልቀቂያቸው ተቀባይነት ስለማግኘቱ ግን ያለው ነገር የለም። የዘ-ሐበሻ የቅርብ ምንጮች እንደሚሉት ደግሞ ሳሙራ በተሰናባቹ ጀነራል ጻድቃን ገ/ትንሣኤ የውስጥ
ለውስጥ ጣልቃ ገብነት ደስተኛ አይደሉም። ሁሌም የሚያስጨንቃቸው የጻድቃን ጉዳይ ነው ይላሉ።
ከመከላከያ ተሰናብተው የነበሩት የቀድሞው ኢታማዦር ሹም ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሣኤና የቀድሞው የአየር ኃይል ዋና አዛዥ አበበ ተክለሃይማኖት በምርጫ 97 ወቅት ሕወሓት ችግር ውስጥ ገብቷል፤ በምርጫ ተሸንፎ ቦታውን ሊያጣ ነው በሚል ተሰባስበው እንደነበር የሚታወስ ነው።

የአየር ኃይል ዋና አዛዥ አበበ ተክለሃይማኖት

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 20, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 20, 2012 @ 2:39 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar