www.maledatimes.com ለህሌና እንደር - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ለህሌና እንደር

By   /   September 20, 2012  /   Comments Off on ለህሌና እንደር

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 6 Second

ለህሌና እንደር

እኔ ምን ቸገረኝ ምን ጊዜም አልደላኝ

ከእንግዲህ ተወልዶ ሰው ለሚሆን ይብላኝ::

እያልን እያዜምን ፀጥ ብለን እያየን

ህዝባችን በግፍ ሲያልቅ ሁአላ ከሚቆጨን

ወገን እንደሌለን አገር እንደሌለን ከምንቀር ተሰደን

ያገባኛል ብለን ካለንብት ሆነን

አምባገነን መንግስት ማስተናገድ ይብቃን::

“በቃ” እዚህ ላይ ያቁም ብለን ቃል እንግባ

ድምጻችን ከፍ ብሎ ለዓለም ያስተጋባ::

አይኑን በጨው አጥቦ ብቅ ብቅ የሚለው

ከእውነት ይለቅ ሁሌ ውሽት የሚቀናው

ተራብን ለሚሉ ጥይት የሚያቀርበው

ፍትህ የሚሹትን አሸባሪ ሚለው

ሳያድጉ ማደግን ለአለም ሚተርከው

ያልሆነን ሆነ ባይ አስምስሎ ፈጥሮ

ሰው እንዴት ይኖራል ለሆዱ ብቻ አድሮ::

ሆዳቸው ማሰቢያ ህሌናቸው እግር

ሆኖ እየመራቸው ሲመኙ ለመኖር

ምን አገባኝ ሳንል የአገራችን ችግር

መፍትሔ እስከሚያገኝ ሆነን በሰው ሀገር

ሆ! እንበል ያገሬ ሰው ለህሌና እንደር::

ያለፈውን ስራ ታሪክን መጥቀሱ

አይገባም ባልል ጀግናን ማወደሱ

ሁሌም በስም መኖር አይበቃም በራሱ::

እንደ አበበ ገላው ነጻነት እናውጅ

ጥሩ ስራ እንስራ ለሀገር የሚበጅ::

በ ይግዛው  እያሱ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 20, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 20, 2012 @ 5:07 am
  • Filed Under: Ethiopia, POEMS
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar