www.maledatimes.com እውነትን ፍለጋ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እውነትን ፍለጋ

By   /   September 20, 2012  /   Comments Off on እውነትን ፍለጋ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 47 Second

እውነትን ፍለጋ

ሳይኖሩ መኖርን ለራሳችው መርጠው

ለህዝብ ድምፅ ባሰሙ እውነትን ፈልገው

ስም ይሰጣቸዋል አሸባሪ ተብለው::

የሚዲያ ትርጉሙን ፍች ማን ይንገረን

እነሱ እንደሚሉት “ውሸት”እውነት ይሆን::?

ያልሰሩትን ሰራን ሆኖ ነገራቸው

በ ETV ቻናል ሁሌ መጮሃቸው

ለነሱ እውነት አለው ውሸት ማውራታቸው::

መቸ ተነግሮ ያውቃል በኢህአዴግ ልሳን

እውነት ላያወሩ ገብተዋል ቃል-ኪዳን::

ሚያወራም ከመጣ ድምጹን እንዳይሰሙ

በውሸት የሚፈርድ ዳኛ ስለሾሙ

ዓቃቢ ህግ ነኝ ባይ የኢህአዴግ ቡችላ

ከስሰው ያቀርባሉ ተፈልጎ መላ::

ከዛም ዳኛ ሆዬ በበላበት ጯሂው

ህሌናውን ሽጦ በሆድ ብቻ አዳሪው

ክሶችን ዘርዝሮ ያሰማና በቃል

መንግስት ለመገልበጥ ህዝብን አነሳስቷል

ደግሞም ለመበጥበጥ እቅድም አቅዷል

ከተቃዋሚ ጋር መልእክት ይላላካል

በማለት አትተው እውነትን አፈና

ብይን ያነባሉ የተጻፈ ዜና::

መቸም የነሱ አይደል ይህ ሁሉ ሴራ

መንግስት ያለውን ነው ዳኛውም ሚሰራ::

ይህም በመሆኑ እውነት በመናገር

ለህሌናው ሊያድር ጋዜጠኛ እስክንድር

ለማንም ሳይወግን እውነት በመጻፉ

አሸባሪ ብለው አስረውት አረፉ::

መስሏቸው ነው እንጂ በሀይል ሁሉ ነገር

እውነተኛን ቢያስሩ እውነት አትታስር::

በአጻጻፍ ብቃቱ በዓለም የታወቀን

አሸባሪ ማለት አቶ እስክንድር ነጋን

በጣም ሞኝነት ነው የዋህነት ጭምር

ራስን ሳያውቁ ዝም ብሎ መኖር::

ከ  ይግዛው አያሱ 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 20, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 20, 2012 @ 5:19 am
  • Filed Under: Ethiopia, POEMS
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar