www.maledatimes.com የሚዘጋባቸው ህጻናት – ዝግ ቤቶች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሚዘጋባቸው ህጻናት – ዝግ ቤቶች

By   /   September 20, 2012  /   Comments Off on የሚዘጋባቸው ህጻናት – ዝግ ቤቶች

    Print       Email
0 0
Read Time:19 Minute, 37 Second

(ቀጭኑ ዘ-ቄራ ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

“በሬ ለምኔ” የፍየል ቁርጥና ጥብስ መለያ ማስታወቂያ ነው። ከኦሎምፒያ ወደ መስቀልፍላወር በሚወስደው መንገድ ላፓሬዚን አለፍ እንዳሉ ወደ ግራ ሲታጠፉ ያገኙታል። ለጉዳዬ የሚመቸኝን በሬ ለምኔ ላመላክት እንጂ ብዙ “በሬ ለምኔ” ቤቶች አዲስ አበባ ተከፍተዋል። ያዲሳባ ቀምጣላ ካድሬዎች፣ ልማታዊ ባለሀብቶች፣ አቀባባዮችና ባለጊዜዎችና አጫፋሪዎቻቸው እድሜ ለማራዘም ፍየል ይመገቡና ማታ ልቅ የግብረ ስጋ ለማድራት አይጨነቁም።

እጠቆምኩት ቤት ስትገቡ ፍየል የሚያገላብጡት የሚታወቁ ባለሥልጣናትና ታዋቂ ካድሬዎች ናቸው። ፍየል ከገባ በኋላ መኪና ተረክ እያደረጉ እዛው ሰፈር፣ ብዙም ሳይርቅ ወይም ቦሌ መሃል፣ ዝግ ቤቶች ይሰየማሉ። አንዱን “ሮዚና” ዝግ ቤት ላስተዋውቃችሁ። ሮዚና ዝግ ቤት ማንም ዘው ብሎ አይገባም። ሮዚና ሲደርሱ እንደ መኖሪያ ቤት ጥሩምባ አሰምተው ከተንበሪውን የሚያስከፍቱ ደንበኞች ብቻ ናቸው። “ደንበኞች” ስል እንግባባለን ብዬ አስባለሁ።
ሮዚና ወገቧ ሸንቃጣ፣ አንጀት የሚባል ነገር ያልሰራባት፣ ዳሌዋ ሰፊና ክብ፣ ሽክ ያለች፣ አንገቷ ውድ ነገሮች የሚቀመጡበት፣ ሽታዋ የሚያውድ፣ ዓይነ ርግቧ በቀለም እንደ ስዕል የሚዋብ፣ ሳሳ ያለ ልብስ የምትለብስ፣ እንግዳዎቿን በምትዘጋባቸው ቤት እየተዘዋወረች የምትቀበል አራዳ ነች። አስተናጋጆቿ በጣም ትንንሽ ልጆች ሲሆኑ ጸሃይ አይነካቸውም። ስራቸው ለሮዚና እንግዶች መስተንግዶ ሳይስተጓጎል መስጠት ነው – የሚጠጣ  ያቀርባሉ፤ ፍም እሳት አዘጋጅተው ቡና ያፈላሉ፤ ለማሟሟቂያ የቡናው ስነ ስርዓት በየክፍሎቹ ከተከናወነ በኋላ የጫቱ ሙቀት እየጨመረ ሲሄድ ሺሻ ይለኮሳል። ህጻናቱ ሺሻ እያሞቁ ደንበኞቹን ለማስተናገድ ከቡና ማፍያው በርጩማ ተነስተው ፍራሹ ላይ ሲወርዱ ከአባታቸው ጋር በሰንበት የሚጫወቱ እንጂ የስራ ግንኙነት ያላቸው አይመስሉም። ጫት እየቀነጠሱ፣ ሺሻ እያሞቁ ደንበኛቸውን ባፍ ባፉ መከደም ዋና ስራቸው ስለሆነ ተክነውበታል።

ተጋብዤ የተመለከትኩት ክፍል የነበረችው ልጅ ሪታ ትባላለች። ንግግሯ የቀምጣላ ልጆች አይነት ነው። ስትስቅ አማርኛ አይመስልም። ጠይም ቀለሟ የጸዳ፣ ለጋ ነች። እንደ ጋባዤ አገላለጽ “ጥፍሯ ይበላል”፤ ዕድሜዋ ከአስራ አምስት አይበልጥም። ቡና እንደጨረሰች ስስ ነገር ለብሳ ደንበኛዬ ጎን ቁብ አለች። መቃም ትችልበታለች። ጫት ላኪዎች በትዕዛዝ የሚልኩትን ጫት ትጠጣዋለች። ያለ ምንም ማጋነን የቅጠል አበላሏን ፍየል ብታየው በቅናት ምላሷን ትቆርጠዋለች። ምን አደከማችሁ ቅማ ታቃቅማለች። አልፎ አልፎ ሮዚና ለጉብኝት ብቅ ብላ ስትመለስ ቤቱን ታውደዋለች።

ምርቃናው ሲጨምር ወዳጄ ቀስ በቀስ ከልጅቷ ጋር ተጣበቀ። እጆቹም ሁለመናውም እሷ ላይ ሆነ። በቃ ደረቱ ላይ ጣላት። ደረቱ ላይ አንጋሏት ሺሻውን ይምጋል። ብቸኝነቱ ሊውጠኝ ሲደርስ መሄድ አለብኝ ብዬ ተነሳሁ። ፒኮክ እንደምጠብቀው ነገርኩትና ተለየሁት። ህጻኗን ልጅ ደረቱ ላይ አንጋሏት ስመለከት ልጄን አቅፌ ሳስገሳው ትዝ አለኝ። የሚያስገሳት እንጂ የሚዳራት አይመስልም። እንዲህ ያሉትን ትውልድ አምካኝ ቤቶች ማጥፋት ቀላል ነው። ግን ተጠቃሚዎቹ ህግ አስከባሪና ህግ አወጪዎቹ በመሆናቸው አይታሰብም። አንዳንድ ዝግ ቤቶች በሲቪል ጠባቂዎች የሚጠበቁ ናቸው። አንዳንዴ ቤተመንግስቱንና ሟቹን የቤተመንግስት ነዋሪ ይጠብቁ የነበሩት በፈረቃ ይታደማሉ። ዝግ ቤቶች…

ፒኮክ አፕሬቲቩ ይጥማል። በጫት የጦዙ ማገዶ ላለመጨረስ አፕሬቲቭ ይወጋሉ። መኪና ውስጥ ሆነው የተጣመዱም ይወጋሉ። “ያራዳ ልጅ” በማለት ሳንቲም የሚለምኑ፣ ሎተሪ የሚያዞሩ የጎጃም ጉብሎች፣ የመንገድ ላይ ነዋሪዎች፣ ቀበሌና አድራሻ የሌላቸው ወንድምና እህቶች፣ ኑሮ ያዞራቸው የኑሮ ሰለባዎች ይታያሉ። አዲስ አበባ ሁሉን ተሸክማ  እየመሸላት ይነጋል።

አፕሬቲቬን እየቀነደብኩ ስለ ሮዚ ቤት እያሰብኩ ቆዘምኩ። ቤቱ ውስጥ ያሉት ህጻናት የተመረጡ ናቸው። መልምሎ የሚያመጣቸውና ስልጠና የሚሰጣቸው አለ። በህጻንነታቸው ተከትበው ሺሻ ስር ሲርመጠመጡ  በዛው ሱስ ይዟቸው ገደል የከተታቸው፣ ኖረውም ተስፋ ያጡ፣ ታመው የፈረደባት እናት እጅ የወደቁ አሉ። አገሩ እንዲህ ሆኗል። የኢትዮጵያ ህዳሴና የኢኮኖሚ እድገት ያተረፈው እንዲህ ያሉትን ዜጎች ነው። በርግጥ አገሪቱ ኢኮኖሚዋ አድጓል። ያደገው ግን ለዝግ ቤት ተጠቃሚዎች እንጂ ለሌሎች አይመስልም። እድገቱ የሚታያቸው በዝግ ቤትና ቤታቸውን ለሌሎች ዘግተው አገሪቱን እያለቡ ላሉት ይመስላል።

በሃሳብ እየቀባጠርኩ፣ አፕሬቲቬን እየሳብኩ ቆየሁ። ወዳጄ ተመችቶታል መሰል አልመለስ አለኝ። ፒኮክ ስለሰለቸኝ ደወልኩለትና እንስራ እንገናኝ አለኝ። ወደ እንስራ አመራሁ። እንስራ ደግሞ ሌላ ትዕይንት አለ።

እንደምን ከረማችሁ… ። አሁን እንስራ ነኝ። እንስራ ለማታውቁ ላስተዋውቃችሁ። እንስራ ቦሌ ቴሌ አካባቢ የሚገኝ የምሽት ንዳድ ቤት ነው። በመለስ ሞት ምክንያት ተፋዞ ከርሞ ነበር። እንስራ ሲገቡ በጡንቸኞች ይዳብሳሉ። ፍተሻ መሆኑ ነው። እንስራ በር ላይ ተዳብሰው ሲዘልቁ ቀለሙ አይን ይወጋል። የደም ጢስ የሚጨስበት ይመስላል። እንስራ ውስጡ በዲጄ ይናጋል፤ ይነዳል። በምድር ቤት ውስጥ የሚደለቀው ሙዚቃ ከተለያዩ አቅጣጫ ከሚፈሰው የተደበላለቀ ቀለም ጋር አንድ ላይ ተዳምሮ የሲኦል ቤተ ሙከራ ይመስላል። መድረኩ ላይ እየተገመዱ የሚላቀቁት ተዋንያኖች እንግዳ ያስደነግጣሉ። ቁመታቸው ረጃጅም የሆኑ እንስቶች የተጠና ዳንስ ይተውናሉ።

እርቃናቸውን ያለ ልብስ የሚናጡት እንስቶች ሃፍረታቸው ላይ የቻይና ማራገቢያ የምትመስል አነፍናፊት ከመለጠፋቸው ውጪ ሁሉም ነገር እንደ አዳምና ሄዋን እንደ ድሮው፣ እንደ ጥንቱ ነው። እርቃን!! ዳንሱ “ብልግና ተኮር” ይባላል። ወገብና መቀመጫን በማላመጥ ሲወዘውዙት ማየት ይመስጣል። “ኮረኮንች” የሚባለው ምንነቱ የማይታወቀውን አልኮል በሉት ዊስኪ እየተጋቱ አብረው የሚያውካኩትን ለተመለከተ አገራችን ውስጥ ችግር በቃል ደረጃም የሚታወቅ አይመስልም።
ከየአቅጣጫው የሚወርደው ባለቀለም ጨረር የሰውነታቸውን ቀለም እንደ እስስት ይቀያይረዋል። እየነደደ ወርዶ የሚቀንሰው ብርሃን ውስጥ ኮሮኮንች ያሳበዳቸው ይዘላሉ። አንዳንዶች መድረኩ ላይ ሳያስቡት ደርሰውበት ዓይናቸውን ከእምብርት በታች ቸክለው ይቅበዘበዛሉ። አንዳንዶች ጥንድ ሆነው መጥተው ብቻቸውን ያሉ ይመስል በሜዳ ላይ ወሲብ መሰል ዳንስ ተማርከው ዓይናቸው ሲቅበዘበዝ አለመስማማት የሚፈጠርበት አጋጣሚ አለ።

ስድስት የሚሆኑት ዳንሰኞች አጎንብሰው መቀመጫቸውን ሲወዘውዙት፣ ተሸብርከው “እንካ፣ አምጣ” ሲሉ፣ ሙዚቃው ሲያቃጥር “የኮረኮንቹ” ኮታ ሳይታወቅ ይበረታል። ከቦሌ አካባቢና ከዩኒቨርሲቲ መንደር የሚዝናኑ መስለው የሚነግዱ በተመሳሳይ ራቁታቸውን ከጊዜያዊ ጓደኞቻቸው ጋር ያስነኩታል። የዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ካነሳሁ አንዴ ወደ አንጋፋው የዝሙት ገበያ ናዝሬት ፔንሲዮን ላምራችሁ።

ናዝሬት ፔኒስዮን እንደ ዛሬው ሳይሆን “ሻሞ” የሚባልበት ለሞት መጣደፊያ አልኮል መቸርቸሪያ ባር ነው። ናዝሬት ፔንሲዮን አካባቢው የጫት መቃሚያና የድለላ ስራ እምብርት በመሆኑ ሰው ስፍሩ ነው። ናዝሬት ፔንሲዮን በብዛት የንግድ ስራ ኮሌጅ ተማሪዎች እንደሚታደሙበት አንድ ወቅት መረጃዎች በይፋ ተሰራጭተው ነበር።

በተለይ ከክፍለሃገር የሚመጡ ተማሪዎች ከመንግስት የሚሰጣቸው ወርሃዊ ድጎማ ለቀለብና ለማደሪያ ስለማይበቃቸው ናዝሬት ፔንሲዮን ለስራ መሰማራታቸው ያደባባይ ወሬ ነበር። “ይሞታል ወይ?” ያለች ተማሪም ነበረች። ውዱ መሪያችን፣ ነብሳቸውን ይማረውና፣ ስጋቸውን እየሸጡ የሚማሩ ተማሪዎችን አስተዋውቀውናል። እኚህ መሪያችን ናቸው “ልማታዊ ሴቶችን አፈሩ፣ ለሴቶች ልዩ ትኩረት አዘነቡ” የሚባሉት፣ እየተባሉ ያሉት። የኮሜርስ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይ ወደ ሀዋሳና አርባ ምንጭ ችግሩ ያስከተለው ቀውስ ቤተሰብን አንገት ማስደፋት የደረሰበት ደረጃ ደርሷል።

ቤተሰብ ልጄ ተምራ ተመረቀች ብለው ሲጠብቁ አጅሬው የቀሰፋቸው ጥቂት አይደሉም። ሃዋሳ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የቡና ቤት ኮማሪቶች በ”ገበያዬን” ወሰድሽብኝ ከፍተኛ ጸብ ውስጥ ሲገቡ ማየት የተለመደ እንደሆነ ሀዋሳ በነበርኩበት ወቅት ያስተዋልኩትና ያረጋገጥኩት ጉዳይ ነው። አንዴ እኔው ራሴ አብራኝ እንድትጠጣ ለጋበዝኳት ልጅ ይህንን ጥያቄ አቅርቤላት “ገበያችንን ዘጉት” በማለት የስድብ ናዳ እያወረደች ነበር ሁሉንም ያጫወተችኝ – ተማሪዎቹን ማለቷ ነበር። የሴቶች ተሳታፊነት አደገ ይሏል እንዲህ ነው። ነብስ ይማር።

ወደ እንስራ ልመልሳችሁ። እንስራ ጥቂት እንደቆየሁ ወዳጄ ያችኑ ልጅ አንጠልጥሎ መጣ። መጨለጥ ቀጠለ። አስቀድሞም ሲጠጣ ስለቆየ ለመስማት ጊዜ አልወሰደም። እንደውም እንደ አዲስ ጀበና መንተክተክ ጀመረ። ህጻኗን ከፊትለፊቱ ወትፏት በቁሙ እንደውሻ ይቀነዝራል። መብራቱ ስለሚመች ስጋት የለም። በቁሟ በዳንስ እያስመሰለ ፈትጎ ሊገላት ምንም አልቀረም። ይህ ሰው ያለውን ኃላፊነት እዚህ ከሚያደርገው ተግባሩ ጋር በማገናዘብ ሳስበው አመመኝ። እንዲህ ያሉ ብዙ “ትልልቅ ሰዎች” ይመሩናል። በችጋር ይጠብሱናል። ሲሞቱ በደቦ ያስለቀሱናል። በጀት ከልክለው በረሃብ ያቃጥሉናል። ሲሞቱ ደግሞ በጀት መድበው ደረት ያስመቱናል። “ያገራችሁን ህዳሴ ከእኛ ጠብቁ” እያሉ ያለ ሃፍረት ይሰብኩናል። አጽማቸውን እናመልክ ዘንድ ይመኛሉ። ከወዳጄ ጋር የትና እንዴት እንደተገናኘን አስታውቃለሁና ተረጋጉ። አሁን በፈጣሪ እጅ ላይ ሆኖ እየኖረ እንደሆነ፣ ከቤቱም እንደማይወጣ ሰምቻለሁ። ሮዚ አራዳዋ አለች እንዳማረባት። ህጻናቱ ግን … ። ሰላም እንሰንብትና ሳምንት እንገናኝ!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 20, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 20, 2012 @ 6:08 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar